ዳኞች በተወዳዳሪዎች አቀራረብ ደስተኛ ነበሩ…ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው(17) ምዕራፍ ሁለተኛ ሳምንት ሁለተ…

Reading Time: < 1 minute
ዳኞች በተወዳዳሪዎች አቀራረብ ደስተኛ ነበሩ…

ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው(17) ምዕራፍ ሁለተኛ ሳምንት ሁለተኛው ምድብ ስምንት የሙዚቃ ተወዳዳሪዎች ከዛየን ባንድ ጋር ስራዎቻቸውን አቅርበዋል ፡፡



*ምን አዲስ ነገር ታየ

– ከምንጊዜው በላይ ዳኝነት እስከ እንጥፍጣፊው ድረስ ለተወዳዳሪዎች ገንቢ የሆነ አስተያየት ሰተዋል፡፡



– ተወዳዳሪዎች በዘመን ልክ የተሰሩ ህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያላቸውን ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል፡፡



– ተመልካቾች ቦታው ድረስ በመታደም የሙዚቃ ስራዎችን በሙሉ ተከታትለዋል ስሜታቸውንም በሙዚቃው ልክ በእንቅስቃሴ ሲገልፁ ውለዋል፡፡

* ዛይት ባንድ ከ ተወዳዳሪዎች ጋር ሆነው አስ ስድስት (16) ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል ፡፡



የማዲንጎ አፈወርቅ/ሰውየለኝም/ ፣አቦነሽ አድነው/ራያ ሙኔ/ ፣ ፀጋዬ እሸቱ/ያያለ/ ፣ ቴዲ አፍሮ ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቀዘባ/ ፣ ፀደንያ ገብረማርቆስ/በር በር/ ፣ ሚኒልክ ወስናቸው/ ትኩራ/ ፣ ጋሽ ጥላሁን ገሰሰ/የዘንባባ ማርነሽ / ፣ ዘሪቱ ከበደ / አትሂድብኝ/ እና የመሳሰሉት ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል፡፡

* ዳኞች ከስልትም ከስሜትም ሐሳብ ሰተዋል፡፡

የሙዚቃ አረዳድ፣ የዜማ ሐረጋትን መረዳት፣ የድምፅ ጉልበት መጠቀም ፣ የሙዚቃ ምርጫ ፣ የዜማ እጥፍት መረዳት፣ ሪትም መረዳት ፣ ቫይብራቶ / የመንቀጥቀጥ ድምፅ/ ፣ ድምፅን መቆጣጠር፣ ቃላት አጠቃቀም ፣ መድረክ መጠቀም፣ አክሰንት( የፊደል ቃላት አጠቃቀም በድምፅ መረዳት) ፣ ናዛል ቮይስ፣(key)( ኪ) መረጣ ፣ ስልተ ምትን መረዳት ፣ ቅኝት ችግር  ፣ በራስ ሙዚቃን አርጎ ማቅረብ ፣ የተለየ ነገርን ማቅረብ እና ማሰብ ፣ ፎክ /ባህላዊ ሙዚቃን/ ፣ ከልክ በላይ ስሜታዊ መሆን፣ የመሳሰሉት ተጠቅሰዋል ፡፡

* ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት ሰተውናል፡፡

– ብሩክ አሰፋ :- ጮሆ መዝፈን እንደ ብቃት ይለካል ጮሆ መዝፈን ሳይሆን ዋናው ውበትን ላይ መጨነቅ ያስፈልጋል፡፡



– የሹምነሽ ታዬ:-  የድምፅ ቀለም ላይ እና ውበት ላይ በይበልጥ ብንሰራበት የራስን ቀለም እናገኛለን፡፡



– አማኑኤል ይልማ :- ሙዚቃ ስንሰራ በብዙ መንገድ እራሳችንን ማሳደግ እንችላለን ምክንያቱም የተፈጥሮ ድምፅ ስላለ፡



* ያለፉ ተወዳዳሪዎች እና ተሰናባችሁን እንጠቁም፡፡

-አብርሀም ማርልኝ-59277 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ሄኖክ አለሙ-59020 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ስንታየሁ ኃይሌ-58738 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ሱራፌል ደረጄ- 58164 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ቢንያም ዘውዱ-57902 አጠቃላይ ነጥብ፡፡
-ጌታሁን ተረፈ-57453 አጠቃላይ ነጥብ፡፡

የእለቱ ተሰናባች አትናሲያ ዳኜ -56862



አጠቃላይ በማምጣት ተወዳዳሪዋ የሰጠችሁ አስተያየት”ውድድር በጣም ከባድ ግን ጥሩ ነገር ሰቶኛል” ብላለች፡፡

ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት የሳምንት ሰው ይበለን ፡፡

137190cookie-checkዳኞች በተወዳዳሪዎች አቀራረብ ደስተኛ ነበሩ…ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው(17) ምዕራፍ ሁለተኛ ሳምንት ሁለተ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE