* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት እንጠቁማችሁ …- ድምፃዊት ኤልሳቤጥ ተሾመ( ልጁን ያያችሁ) ድምፃዊቷ በአጠ…

Reading Time: 2 minutes
* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት እንጠቁማችሁ

– ድምፃዊት ኤልሳቤጥ ተሾመ( ልጁን ያያችሁ) ድምፃዊቷ በአጠቃላይ ወደ አራት የሚጠበቁ አልበሞች ለህዝብ አድርሳለች፡፡ የግጥም ዜማ ደራሲ ኤልሳቤጥ ተሾመ በይበልጥ  ከ ህዝብ ጋር ያስተዋወቃት(ልጁን ያያችሁ) በተጨማሪም ”ማልኩኝ እንዳልጠላህ” ሙዚቃዎቿ ትታወቃለች የጨረሰችሁ አልበም አለ ያንን ከዳር ማድረስ ትፈልጋለች በእሁድን በኢቢኤስ እንግዳ ሆና  እንዲህ ስትልም ተደምጣለች ” እኔ የሚያሰራኝ ሰው ካለ እሰራለሁ ፣ እድሉ ከተመቻቸ እሰራለሁ” ስትል ተደምጣለች ፡፡ የኔ ቫይብ የሙዚቃ ዝግጅት ክፍል ኢቢኤስ ቲቪን አንጋፋ ድምፃዊያንን ከጠፉበት የሚያሳየን በተጨማሪም ድምፃዊቷን ያመሰግናል ፡፡



– የመጀመርያ የኢትዮጲያ የተወዛዋዦች የጥበብ ማህበር ጉባኤ በፍንድቃ ባህል ማዕከል ተከናውኗል፡፡ ሰኞ ግንቦት 5/2016 ዓ.ም ለተከታታይ ስድስት ቀን እያካሄደ ነበር ይህ ጉባኤ ዩኔስኮ ከ አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ጋር በመተባበር ከውጭ በመጡ የዘርፉ ባለሞያዎች ውዝዋዜ ጥበብ የመጀመርያ ዲግሪ በደረጃ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እንዲንካተት ጥረት እየተደረገ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡



– ድምፃዊ እና የዜማ ግጥም ደራሲ አቤል ሙሉጌታ እና ድምፃዊ የሙዚቃ ባለሞያ ብሌን ዮሴፍ ከፋና ላምሮት የዳኝነት መንበራቸውን ሌላ የፋና ላምሮት ዳኞች አስረክበዋል ብሌን ዮሴፍ ከምዕራፍ ሁለት እስከ ምዕራፍ አስራ ስድስት ድረስ በዳኝነት ሰርታለች  አቤል ሙሉጌታ ከምዕራፍ አምስት እስከ አስራ ስድተኛው ምዕራፍ ድረስ መርተዋል የዳኝነት መንበሩን የተረከቡት የፋሉት ተጫዋች የሹምነሽ ታዬ እና አቀናባሪ አማኑኤል ይልማ ናችው፡፡የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ክፍል ከልብ ያመሰግናችኃል፡፡



-ተወዳጁ ድምፃዊ ሮፋናን ኑሪ ሀያ አራተኛ ምሽት በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ባህል ማዕከል የኪነጥበብ መርሀ ግብር ግንቦት 14/2016 ዓ.ም ተከናውኖ ነበር፡፡ እውቁ የሙዚቃ አቀናባሪ እና ግጥም ዜማ ደራሲ ሮፍናን ኑሪ ነፀብራቅ እና ስድስት በመቀጠል ሰጠኝ ሲል አልበሞችን አርሷል፡፡



– የክብር ሽልማት የሽልማት ስነስርዓት በሳለፍነው ሳምንት ግንቦት 9/2016 ዓ.ም ተከናውኖ ነበር፡፡ የክብር ሽልማት አስራ ስድስት(16) ዘርፍ የተወጣጡ አምስት አምስት እጩዎችን አወዳድሮ ነበር ፡፡ በምርጥ የዘፈን ግጥም -ዳና አድማሉ ላይነኩሉ የክብር ሽልማት የስነፅሁፍ የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ኃይለ መለኮት መዋል በምርጥ ተውኔት በሀይሉ ግርማ ቤርሙዳ(ውድነህ ክፍል) የአመቱ የቴሌቪዥን ዝግጅት (አስካል ተስፋዬ) ተፅኖ ፈጣሪ መዝናኛ ትዮብ(ዶንኪ ትዮብ) እና የመሳለሱት በመድረኩ ሽልማታቸውን ተቀብለዋል፡፡



* በዚህ ሳምንት የመረጥንላችሁ የሙዚቃ አልበም…

በዚህ ዘመን በዚህ ትውልድ ዳር ድረስ ተደርሶ የተሰራ አልበም እንጋብዛችሁ የድምፃዊ ዳዊት ፅጌ አልበም ”የኔዜማ” የተሰኘውን የበኩር አልበሙን ነው በውስጡ ወደ 14 የሚጠጉ ሙዚቃዎች ሲኖሩት ባላገሩ ቁጥር ሁለት ፣ ባየው ፣ደሀ አይጣላ ከውሀ ፣የኔ የኔ ፣ አስችሎስ፣ አስመሪኖ እና የመሳሰሉት ናቸው በግጥም እና ዜማ የተሳተፉት ናትናኤል ግርማቸው ፣ አበበ ብርሀኔ ፣ ይልማ፣ ሐብተማርያም መንግስቴ ቅንብር አበጋዝ ፣ ሚኪ ጃኖ ፣ አቤል ጳውሎስ የመሳሰሉት ናቸው ፡፡



@yenevibe @biggrs
136780cookie-check* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት እንጠቁማችሁ …- ድምፃዊት ኤልሳቤጥ ተሾመ( ልጁን ያያችሁ) ድምፃዊቷ በአጠ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE