“የክብር ሽልማት”

Reading Time: < 1 minute
የክብር ሽልማት
የመጨረሻ ቀን የተቆረጠለት አርብ ግንቦት 9 2016 ዓ.ም በግዮን ግሮቭ ጋርደን በሚከናወን  ታላቅ ሥነ ስርዓት አሸናፊዎች ይታወቃሉ ።የክብር  ሽልማት  ከ 16ቱም ዘርፍ የተውጣጡ  ዕጩዎች  በዕለቱ ከ 11 ሰዓት ጀምሮ በግሮቭ ጋርደን ይታደማሉ።በቃል መልቲሚዲያ አማካይነት ‹‹ክብር ሽልማት›› በሚል ሀሳብ ለደራሲዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች ሽልማት ለመስጠት ታላቅ ሀገራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፣ የክብር ሽልማት አዘጋጆች ካለፈው ዓመት አንስቶ ባለሙያዎች፣ በድረገጽ እና በሌሎች የመገናኛ አውታሮች እንዲጠቆሙ ሲያደርጉ ነበር።በሚዲያና በድርሰት ዘርፍ የተጠቆሙ ሰዎችን በድረገጽ ላይ በማውጣት ባለፉት  ቀናት ዳኞችና ህዝብ እንዲመርጡ መደረጉ  ይታወሳል፡፡

አጠቃላይ በ16 ዘርፎች በባለሙያዎችና በሕዝብ ድምጽ ሲሰጥባቸው የቆየ ሲሆን  ከ300 በላይ ሰዎችም ተወዳድረው ከየዘርፉ 77 ሰዎች ወደ ፍጻሜው  ዙር  አልፈው ድምፅ ሲሰጥበት ነበር።

ከእያንዳንዱ ዘርፍ ከተጠቆሙ ሥራ እና ሠራተኞች ውስጥ ምርጥ 5ቱን ለመምረጥ ከህዝብ የተገኘን 40 ከመቶ ድምጽ እንዲሁም በዳኞች የተሰጠን 60 ከመቶ አንድ ላይ በማድረግ ክብር ሽልማት በ16 ዘርፎች ምርጥ አምስት ያላቸውን  ባለሙያዎች  ሚያዝያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።ተወዳዳሪዎች በ2015 ባለው የሥራ ውጤታቸው እንዲዳኙ ተደርጓል፡፡ ይህንንም ዕውን ለማድረግ በክብር ሽልማት ስር የተዋቀረው የጥናት ምርምር ክፍል የባለሙያዎችን የህይወት ታሪክ እንዲሁም ናሙና ስራዎችን በቋት ውስጥ በማጠራቀም ለዳኝነቱ ስራ ተገቢ መላ ዘይዶ የማወዳደሩን ስራ በተገቢው መልኩ አከናውኗል፡፡

የዳኝነት ሥራውም ፍጹም ምስጢራዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን ባለሙያዎችን ከሥራቸው አንጻር ብቻ በማየት ወደ ውድድሩ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ግንቦት 9 አርብ ዕለት ዝግጅታቸውን ጨርሰው በእለቱ ክቡራን እጩ ተወዳዳሪዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው ባለሥልጣናት እና እንግዶች በተገኙበት አንደኛውን የክብር ሽልማት መርሐ ግብር  ያከናውናሉ ዝግጅቱም በሀገሬ ቲቪ በአራዳ ሬድዮ ይተላለፋል ተብሏል ፡፡

event @yenevibe Yenevibe.com
136140cookie-check“የክብር ሽልማት”

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE