አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ሳምንታዊ ሙዚቃዊ ጉዳይ በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ነው፡፡h…

Reading Time: 3 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ሳምንታዊ ሙዚቃዊ ጉዳይ በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ነው፡፡



– ሳሙኤል ብርሀኑ (ሳሚ ዳን) – ቅፅበት በተሰኘው አራተኛ አልበሙ ስር የተካተተው ”አምሳያ” የተሰኘ ሙዚቃ በቪድዮ ሰርቶ ወደ ህዝብ ሊያደርስ መሆኑ ተሰምቷል ፡፡ ይህ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ በራሱ ሳሚ ዳን ሲሰራው ቅንብሩን አንዱዓለም ቤተ(ኤንዲ ቤተ ዜማ) ሰርቶታል በቅርቡ ሙዚቃው ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡



– መላኩ ቢረዳ – “ሶሎ ላና” የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን የሙዚቃው ዳይሬክትር ራኬብ በቀለ ግጥም እና ዜማ በመላኩ ቢረዳ ሲሰራ ማሲንቆ ታረቀኝ ሀይሌ(ቻፒ)  ሙዚቃው አርብ ምሽት ድምፃዊ መላኩ ቢረዳ ዮትዮብ ቻናል ይለቀቃል ተብሏል፡፡



-ጊልዶ ካሳ እና ዳጊ ዲ- “ቀን ሙሉ” የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን ግጥሙን እዮብ እና ዳዊት መንግስቱ ሲሰሩት ዜማ እና ቅንብር ጊልዶ ካሳ ሚክስ እና ማስተሪንግ ፍሬዘር ታዬ በምነው ሸዋ በኩል በቅርቡ ይደርሳል ተብሏል ፡፡



– ብዛየሁ ክፍሌ(buze man) -”ሌቦ” የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን ግጥም እና ዜማ ቡዜ ማን የጉራግኛ ጭማሪ ግጥም ደሳለኝ መርሻ የሙዚቃ ቅንብር ዮሐንስ ጌታነህ ሚክስ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ኃ/ማርያም ሰርቶታል ፡፡



-ኤርሚያስ ፍቃዱ- ”ሽሙንሙኔ”  የተሰኘ ሙዚቃ ሲሆን ግጥም እና ዜማ ኤርሚያስ ፍቃዱ ቅንብር ኤርሚያስ ፍቃዱ (ዳንኪራ ሪከርድስ) በዚህ ሙዚቃ ላይ የተወነው ቲክቶከሩ በረከት ታደሰ(4 ኪሎ ኢንተርቴመንት) በዋልያስ ኢንተርቴመንት በኩል ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡



-ዲጄ ሙሴ – ”ትዝታ” የተሰኘ ዝነኞች የሙዚቃ ስራ በዲጄ አቀነባብሮ ለህዝብ አድርሷል ለመጥቀስ ያህል የብስራት ሱራፌል ፣ እጅጋየሁ ሽባባው ፣ ተሾመ ምትኩ ፣ ፍቅሩ ሰማ (ካስ ማሰ) እና የመሳሰሉት ሰርቷል ዲጄ ሙሴ ዩትብ ቻናል ገብታችሁ አጣጥሙለት ፡፡



– ደሳለኝ መርሻ- በቅርቡ አዲስ አልበም ሊያደርሰን መሆኑ ተሰምቷል ደሳለኝ መርሻ ”ኑድኒያ” የተሰኘ አልበም በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን የተሳተፉበት በግጥም እና በዜማ ፈለቀ ማሩ ፣ ናቲ ሀይሌ ፣ ዘነበ መርሃባ የመሳሰሉት በቅንብር አሌክስ ይለፍ ፣ ስማገኘሁ ሳሙኤል ፣ ፍሬዘር ታዬ ሚክስ እና ማስተሪንግ ሰለሞን ኃ/ ይለማርያም ግንቦት 16 2016 ዓ.ም ለህዝብ ይደርሳል ተብሏል ፡፡



– ፋና ላምሮት ከ አንድ ወር ቆይታ በኃላ በአስራ ሰባተኛው ምዕራፍ ተመልሷል ፡፡ በውስጡ አስራ ስድስት ተወዳዳሪዎች ይዞ በዘጠኝ ሳምንት ለማፋለም ቅዳሜ 10/9/2016 ዓ.ም ከ ቀኑ ስድስት ሰዓት በቀጥታ ስርጭት  ጅማሮውን ያደርጋል መከታተል ትችላላችሁ ፡፡



-ደሞ አዲስ የባለ ተስዖጦ ውድድር ወደ መጠናቀቁ እየቀረበ ይገኛል የመጀመርያ ምዕራፉን ወደ 21 የሚጠጉ ሙዚቀኞችን ያሳተፈ ሲሆን በስተ መጨረሻም አራት ምርጥ ሙዚቀኞች አስቀርተዋል ደሞ አዲስ የባለ ተስዕጦ ውድድር አንደኛ ለወጣ ተወዳዳሪ አንድ ሚልየን ብር እንዳዘጋጀ ከዚህ ቀደም ገልፆ ነበር ፡፡

* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት እናንሳ



– ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ ይሁን የተሰኘ አልበሙን በዚህ ሳምንት ግንቦት 2/2016 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል አልበሙን አስመርቋል ፡፡ድምፃዊ ካሳሁን እሸቱ በመድረኩ ስራዎች ሲያቀርብ ታላላቅ የሙዚቃ ወዳጆች በቦታው በመገኘት ስራዎቻቸውን አቅርበዋል ድምፃዊው አንድ አስገራሚ አነጋጋሪ ክስተት አድርጎ ነበር ወደ ሚያስመርቅበት ቦታ ወደ ሸራተን አዲስ ሆቴል ሲያመራ ህዝብ በሚሳፈርበት ታክሲ በመግባት ”ረዳት ” ሆኖ ቦታው ድረስ ሄዷል ፡፡ ጋዜጠኞች ተገርመው ሲጠይቁት እንዲህ አለ ”ሰው ሁሉ የኃላውን  መነሻውን መርሳት የለበትም” ብሏል፡፡



– የግጥም እና ዜማ ደራሲ መፅሐፍ ፀሐፊ አለማየሁ ደመቀ የሃያ አምስት (25) ዓመታት የሙዚቃ ጉዞ ሲዘከርለት መሆኑን የሰማንበት ሳምንት ነበር ፡፡ የግጥም እና ዜማ ደራሲ ዓለማየሁ ደመቀ 120 በላይ ግጥም ዜማ ስራዎች ለበርካታ ድምፃዊያን ሰቷል በጥቂት ለመጥቀስ ያህል ለ ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ሀሊማ አብራህማን ፣ አለማየሁ ሂርጶ ፣ብርሀኑ ተዘራ ፣ ሀይልዬ ታደሰ የመሳሰሉት በተዘጋጀው እሱን የማስታወስ ስራዎቹን በሚዘከርበት ወቅት ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡



– የድምፃዊት ለምለም ኃ/ሚካኤል ማያዬ የተሰኘ አልበም ለህዝብ እንደ ምታደርስ የሰማንበት ሳምንት ነበር በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን የተሳተፉበት  በናሆም ሪከርድስ በኩል ግንቦት 9/2016 ዓ.ም ይወጣል ተብሎ ይጠቃል ፡፡



– የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል እና የቬሮኒካ አዳነ ጥምረት ሰኞ እለት ግንቦት 5/2016 ዓም በባትያም ከተማ ሆሎፒያ አዳራሽ በእስራኤል ሀገር የሙዙቃ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡



– በሂልተን ሆቴል በተዘጋጀው የኢቨንት ዝግጅት የግጥም ዜማ ደራሲ የፋና ላምሮት ዳኛ ብሌን ዮሴፍ በፍሉት (በዋሽንት ) ስራዎቿን አቅርባለች በቦታውን ኮሜዲያን ፍራኦል በዳዳ ፣ ሕይወት እምሻውን ጨምሮ እግግር አድርገዋል ፡፡

በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ ሙዚቃ



– የዳዊት መሰሰ አልበም “አንቺን ነው” የተሰኘውን ሲሆን የሙዚቃ ፕሮዲውሰር በራሱ   በዳዊት መለሰ ሲሆን ቅንብሩ ኤክስፕረስ ባንድ በአጃቢነት እና አበጋዝ ክብረወርቅ ሰርተውታል ግጥም ዜማ ዓለምፀሐይ ወዳጆ ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ ቢኒያሚር አህመድ ፣ ዮናስ ሙላት ሞገስ ተካ ናቸው ቁንጅና ፣ ውቤ ከርሜላ ፣ ምን ይልሻል ፣የሀገሬ ልጅ ፣ አይሰማሽም ይገኝበታል ፡፡
@biggrs @yenevibe

Musics, New Releases, Music Videos
135820cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ሳምንታዊ ሙዚቃዊ ጉዳይ በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ነው፡፡h…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE