አሚጎስ በኅብረት ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ 52 በመቶ ለአባላቶቹ ትርፍ አከፋፈለ። አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድ…

Reading Time: < 1 minute
*
አሚጎስ በኅብረት ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ 52 በመቶ ለአባላቶቹ ትርፍ አከፋፈለ።

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር በዛሬው 10ኛ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች መደበኛ ጉባኤው የህብረት ሥራ ማህበሩ የ2015 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ቀርቦ በጠቅላላ ጉባዔ ተወካይ አባላት የፀደቀ ሲሆን የኦዲት ሪፖርቱም ነጻ እና ገለልተኛ በሆነ መንገድ መከናወኑን እንዲሁም በባለፈው በጀት ዓመት (ከሀምሌ 1 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም) የስራ አፈጻጸም በአጠቃላይ 68.3 ሚሊዮን ብር ዓመታዊ ትርፍ ማስመዘገቡን የአዲስ አበባ አስተዳደር አራዳ ክፍለ ከተማ ኅብረት ሥራ ፅህፈት ቤት የማህበራት የኦዲት ቡድን ኦዲተሮች ለጉባዔው ገልፀዋል፡፡

በዚህም መሰረት የህብረት ሥራ ማህበሩ የ2015 በጀት ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ክፍፍል 51.84 ⁒ መሆኑ ተገልጾ ለአባላቱ እንዲከፋፈል በህብረት ሥራ ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች ፀድቋል፡፡ በተጨማሪም አሚጎስ ካተረፈው ዓመታዊ ትርፍ ውስጥ 30 በመቶ የሚሆነው ለህብረት ስራ ማህበሩ መጠባበቂያ ተቀማጭ የሚሆን ሲሆን ከመጠባበቂያ ተቀማጭ ውጪ የሆነው 70 በመቶ ትርፍ ለአባላት ባላቸው የሼር መጠን እንደሚከፋፈል ጉባኤው በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

አባላት ኅብረት ሥራ ማህበራቸው ከተለያዩ የመኪና አስመጪና መኪና መገጣጠሚያ ተቋማት ጋር በሚያደርጋቸው ስምምንቶች በቀላሉ መኪናዎችን እንዲያገኙ በማስቻል ላይ መገኙቱና በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል እንዳለበት በጉባኤው ላይ ተገልጿል፡፡
135430cookie-checkአሚጎስ በኅብረት ሥራ ለመጀመሪያ ጊዜ 52 በመቶ ለአባላቶቹ ትርፍ አከፋፈለ። አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE