ደራሲ ሀይሉ ፀጋዬ- በ ውድነህ ክፍሌ የተፃፈውን እንኳችሁ እንዲህ እያስታወስህ ለምታመሰግናቸው ሁሉ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት እጅግ ከልብ ያመሰግንሀል ፡፡
በአንድ ድምጽ ለደራሲ ኃይሉ ጸጋይ በ”የማዕበል ዋናተኞች” የሬድዮ ድራማ አጨብጭበናል። ድምጻውያን ሳይቀሩ ለዋናዋ ገጸባህሪ ‘እፁብ’ አንጎራጉረውላት አስደምመውናል።
ሀይሊሽና የሬድዮ ድራማ እጅና ጓንት ናቸው። ዋጋም ከፍሎበታል።
አስቡት የማዕበል ዋናተኞችን የሚያህል ድራማ ለአመት ያህል ጽፎ፣አዘጋጅቶና ተውኖ ለ52 ክፍል ከ10 ሺህ ብር በታች ብቻ ነበር የተከፈለው። የኃይሉ የሬድዮ ድራማ ጉዞ ብቻውን ሙያተኞች የከፈሉትን ዋጋ የሚያሳይ ነው።
ለነገሩ ቅዳሜ መዝናኛ ላይ ለሚጽፈው በርካታ ተወዳጅ ድራማዎቹ ለትወና በደቂቃ አንድ ብርና ለድርሰት ሁለት ብር አልነበር እንዴ የሚከፈለው። ምን ይደንቃል።
“ወደ ሀብት ጉዞ” ለኃይሊሽ የመጀመሪያው ተከታታይ የሬድዮ ድራማው ነው። በነገራችን ላይ ወደሀብት ጉዞ ፋና ሬድዮ ገብቶ ነበር።
ሲሽኮረመሙ የኢትዮጵያ ሬድዮ ቀደማቸው። ደግነቱ በ”የደወል ድምጾች” አግኝተውታል።
“የደወል ድምጾች” በሬድዮ ፋና ከሁለት አመት በላይ ሲተላለፍ የነበረ ተወዳጅ ድራማ ነበር።
ኃይሉ ግሩም ብዕር አለው። ልምድና እውቀቱ ሰፊ ነው።
ከሬድዮ ድራማ ባሻገር የመድረክ ተውኔት ጽፏል፣አዘጋጅቷል። ‘ከራስ በላይ ራስ’ ‘ለእረፍት የመጣ ፍቅር’ ፣ ‘ቤተሰቡ’ ፣ ‘ቅድስተ ካናዳ’ን ማንሳት ይቻላል።
የቲቪ ድራማም ‘ሞጋቾች’ን እሰከ 48ተኛው ክፍል የጻፈው ኃይሉ ጸጋዬ ነው። እንደእድል ሆኖ ከኃይሉ ተረክቤ የሞጋቾችን 143 ክፍልን በመጻፌም ያስደስተኛል። ብዙም የተማርኩበት ልምድም ያገኘሁበት ነው።
ኃይሉ “አፈራረሰችው” የተሰኘ መጽሐፍም ለህትመት አብቅቶ ነበር።
በአጠቃላይ ኃይሉ ሁለገብ ነው። ከእሱ ብዙ እንጠብቃለን። የማይነጥፍ አቅም አለውና።
“ወደፊት በሬድዮም በቲቪም ተከታታይ ስራ ይዤ ብቅ እላለሁም!”ብሎኛል።
በእዚህ አጋጣሚ ኃይሉ ጸጋዬ ለከፈለው ዋጋ እውቅና ሊሰጠው ይገባል። እሱ ከጉዳይ ባይጥፈውም ሌሎችን ያበረታታልና።
እድሜና ጤና ይስጥልን ኃይልሽ።
በግሌ አክብሮቴ የትየሌ ነው። ክብረት ይስጥልን።
@yenevibe