መንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራልን ለማጠናቀቅ 90 ሚሊየን ብር ያስፈልጋል ተባለ
እንድ እገር ፡ ሃይማኖት ፣ ታሪክ እና ቅርስ ከሌለው ማንነቱ በሌሎች ዘንድ ሊታወቅ አይችልም ::
ቅርሶች ያለፈውን፣ነባሩንና ተተኪውን ትውልድ የሚያገናኙ የነብረ ትውልድ ድልድዮች ናቸው፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም ንዋይ ሊተምነው የማይችል ቅርሶች ግምጃ ቤት ናት፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሀዶ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ብዙ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ቅርሶችን ይዛ በሀገር በቀል
ዕውቀቶቿም ለኢትዮጵያ የሥልጣኔ አሻራዋ መሆኗ የሚታወቅ ነው፡፡ ለእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ቅርስና ልዕልና መነሻ በመሆን ትልቁን አስተዋጽኦ ያበረከቱት ከኢ/ኦ/ተ/ ቤ/ ቤተ ክርስቲያን የፈለቁት ሀብቶች መሆናቸውም ህያው ምስክሮች ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ አገልግሎትና ትርጉም ያላቸውን ቅዱሳት መካናትና ንዋያተ ቅዱሳትን ፣ ቅዱሳት ሥዕላትንና ቅዱሳት መጻሕፍትን ብቻ ሳይሆን የነገሥታቱን የመሰፍንቱን የሥርዓተ መንግሥት ማድረሻ ንዋያት እልባሳትና የወግ ዕቃዎችን በዕቃ ቤቷ ሸክፋ የያዘች ባለውለታ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለራሷና ለሃይማኖቷ ለአገልግሎት ብላ በጠበቀቻቸውና ባስቀመጠቻቸው ቅርሶች ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም የቱሪዝም መስክ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክታለች።
በመሆኑም በቀደሙት አባቶቻችን ጥረት የቆዩልንና አገራችን በዓለም መድረክ በበጎ መልኳ እንድትታወቅ ያደረጉ ቅርሶቻችንን ትላንት በነበሩበት ሁኔታ ልንጠብቃቸውና ልንከባከባቸው ይገባል፡፡ ከእነዚህ ቅርሶቻችን መካከል አንዱ የሆነው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ነው፡፡
የዚህ ታላቅ ካቴድራል የመሠረት ድንጋይ የተጣለው በ1924 ዓ.ም ሲሆን ሥራው ተጀምሮ ሳለ ጣልያን አገራችንን በመውረሩ ምክንያት ለ5 ዓመት ያሀል ተቋርጦ ቆይቷል፡፡ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ከድል በኋላ ወደ አገር ቤት በገቡ በ2ኛው ዓመት በ1935 ዓ.ም ሥራው እንደገና ተጀምሮ በከንቲባ ከበደ ተሰማ ተቆጣጣሪነት እና አሠረነት ተፈጽሞ የቅዳሴ ቤቱ በዓል በ1936 ዓ.ም ተጠናቆ ተከብሯል፡፡ ካቴድራሉ አሁን ባለበት ሁኔታ እሰኪጠናቀቅ ድረስ ሙሉ ወጪው የተሸፈነው በንጉሰ ነገስት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ነበር።
ይህ ታላቅ ታሪካዊ እና አለም አቀፋዊ ካተድራል በእድሜ እርዝማኔ ምክንያት እድሳት ሳይደረግለት በመቆየቱ ውስጣዊና ውጫዊ የህንጻው አካል ላይ እየደረሰ ያለው ጉዳት ቅርሱን ለችግር የሚያጋልጠው ሆኖ በመገኘቱ ለቀጣዩ ትውልድ ሁለንተናዊ ውበቱን፣ቅርጹን እና ይዘቱን እንደጠበቀ ለማስተላለፍ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነበር፡፡ ይሀንንም ታሳቢ በማድረግ በቅዱስ ሲኖዶስ መልካም ፍቃድ ፣ በካቴድራሉ አስተዳደር አስተባባሪነት እና በቅርስና ጥበቃ ባለስልጣን እገዛ በአገራችን አሉ ከሚባሉ ታዋቂ የቅርስ ጥናት ባለሞያዎች አማካይነት ሰፊና ጥልቅ ጥናት ለ16 ወር ያሀል ሲደረግ ቆይቷል፡፡ የጥናቱን ግኝት ታሳቢ ባደረገ መልኩም በአሁኑ ሰዓት የእድሳቱ ሥራ መሰራት ተጀምሮ በጥሩ ሂደት ላይ ይገኛል። ካቴድራሉ በርካታ ቅርጻ ቅርጾች ያሉት እና ውድ ከሆኑ የተለያዩ ቁሳቁሶች የተገነባ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እድሳቱን ለማከናወን በቅርስ እድሳት የካበተ ልምድ ካለው ቫርኔሮ ከተባለ ድርጅት ጋር በ172 ሚሊዮን ብር የሥራ ውል ሥምምነት ተፈጸሞ ሥራው በጥሩ እና በተፋጠነ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ዛሬ በቅርሱ እና በታረኩ የማይደራደረው በአገር ወስጥ እና አገር ውጪ ላሉ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ይህ ዕምቅ ታሪክ የያዘውን ካቴድራል የደረሰበትን የዕድሳት ደረጃ ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ በተለይም በገንዘብ ማሰባሰብ ሂደቱ ላይ እየገጠመን ያለውን ዕጥረት እና በእድሳቱ ፍጥነት ላይ ሊያስከትልብን የሚችለውን አሉታዊ ተጽዕኖ አስመልክቶ በዚህ የዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ግንዛቤ ለመስጠት ጥሪ አድርገናል፡፡
እስካሁን የተሰሩ ሥራዎች፡-
- የዕድሳትና ጥገና ሥራ
ከካቴድራሉ ሀንጻ ዶም መስዋል አንስቶ እስከ መሰረት ማጠናከር ድረስ ባሉ ሥራዎች የተከናወኑት –
1.1. ከመዋቅር እድሳት ሥራዎች (Structural Renovation)
በምድር ቤት ውስጥ በሚገኙ ምሰሶዎች የመዋቅር ማጠናከር (Jaketing) ሥራ፤ የሜዛኒን ወለል ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መሥራት ፣ የሀንጻው መካከለኛ ክፍል ላይ ከፍብሎ የሚገኘው ስፍራ (Nave) የውጪ ግድግዳ ዕድሳት የልስን ሥራ ፣ የዶም ውስጣዊ ክፍል ሥዕል ዕድሳት እንዲሁም ሌሎች
1.2. የሥነ ሕንፃ እድሳት
ሁለት የደውል ቤት መስቀሎች እድሳት፤ የትልቂ ዶም መስቀል እድሳት፤ የመሀከለኛውና ትልቁ ዶም ጣራ የመዳብ ጥገና፤ የድንጋይ ጌጦች የመጀመሪያ አጠባ፤ የወንጌላውያንና የመላእክት የሐውልት ቅርጻ ቅርጾች ጽዳት
1.3 የስዕል ጥገና ሥራ
1.4 የፍሳሽ መሥመር ጥገና
1.5 የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ሥራ
1.6 የአውደ ምህረት የባዞላ ንጣፍ በተመሳሳይ የመቀየር ሥራ የመሳሰሉት
እነዚህ ባለፉት 18 ወራት ውስጥ የተከናወኑ መሰረታዊ የሆኑ የዕድሳት ሥራዎች ዋና ዋናዎቹ ክፍሎች ሲሆኑ በቀጣይ ሥራው በየጊዜው በባለሙያዎች ክትትል እየተደረገለት እስከ ፍጻሜው ለማድረስ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከእነዚሀ ሁሉ ስራዎች በኃላ በአጠቃላይ የሕንጻ ጥገና ሥራው 65% ያህል ደርሷል፡፡
በእድሳቱ ሥራ ያጋጠሙ ችግሮች
በውሉ መሠረት ሥራው ተጠናቆ የሚያልቅበት የጊዜ ገደብ መጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ/ም የነበረ ሲሆን የዶም ኮፐር ቀለምና የውጪያዊ ግድግዳ ቀለም፣ሞዛይኮች ፣ መብራቶችና ጀነሬተር ከውጪ ሀገር የሚመጡ በመሆኑ እነዚሀንም ለማስገባት በውጪ ምንዛሬ የሚገዙ በመሆናቸው የውጪ ምንዛሪ የጠየቅን ቢሆንም ለማግኘት ስለተቸገርን የ3 ወር የጊዜ ገደብ ለኮንትራክተሩ እንዲጨመር ተደርጓል።
2ኛ. ለካቴድራሉ የዕድሳት ሥራ የሚውል የመዋዕለ ነዋይ ማሰባሰብ ሥራን በተመለከተ፡-
የካቴድራሉ የገንዘብ አስባሳቢ ኮሚቴ ለዚህ ዕድሳት የሚሆን ገንዘብ ለማሰባሰብ የተለያዩ ስልቶችን ተጠቅሟል፡፡ ከነዚህም ውስጥ በአውደ ምህረት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጥና የገንዘብ ማሰባሰብ ቅስቀሳ ሥራ፤ በሚዲያዎችና በማህበራዊ ድህረ ገጽ የጥገናውን ሥራ ሂደት መረጃ መስጠት ፤ ለተለያዩ መንግስታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ገለጻ መስጠት ፤ በታዋቂ አርቲስቶች መንፈሳዊ ቴያትር ተዘጋጅቶ ለምዕመናን እንዲቀርብ ፣ ከአዲስ አበባ ባህል ፣ቱሪዝም እና ኪነጥበብ ቢሮ ጋር በመተባበር የገንዘብ ማሰባስብ ሥራ በስካይ ላይት ሆቴል ፣ ከጠቅላይ ቤተክህነት Thመንግሥታዊ ተቋማት፣ከግል ድርጅቶች፣ከምዕመናን በማሰባሰብ እስካሁን 90 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
ከዚህ በኃላም ሚያዝያ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል የገንዘብ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡ በዚህ መርሀ ግብር ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ስልክ በመደወል ለዕድሳቱ እገልግሎት የሚውል የገንዘብ አስተዋጽዋችሁን እንድታበረክቱ ስንል በአክብሮት ጥያቄአችንን እናቀርባለን። እንዲሁም ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም የቀጥታ ሥርDት ገንዘብ ማሰባሰብ መርሐ ግብር ተይዟል። በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ ያላችሁ በዚህ መርሐ ግብር በመሳተፍ የበኩላችሁን አስቷጾ : በማድረግ ቅርሳችንን እና ታሪካችንን በጋራ እንጠብቅ።
በእድሳቱ የገንዘብ አሰባሰብ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችዛሬ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ትኩረት ከምናደርገበት ዋና ርዕሰ ጉዳይ አንዱ በገንዘብ ማሰባሰብ ሂደት ወቅት እየገጠመን ያለውን ከፍተኛ ተግዳሮት ነው፡፡ አብዛኛው ማሀበረሰባችን ካቴድራሉ ከፍተኛ የገንዘብ አቅም ያለው እንደሆነ እና ምንም አይነት እርዳታ የሚያስፈልገው እንዳልሆነ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃ በዚህ መልክ መረዳታቸው እና ድጋፍ ለማድረግ ፍቃደኛ አለመሆናቸው የገንዘብ ማሰባሰብ ሂደቱን ከምናስበው በላይ እጅግ ውስብስብ እና ፈታኝ አድርጎብናል፡፡ ካቴድራሉ ዙሪያ ያሉትን ሀንጻዎች የካቴድራሉ ንብረት አድርጎ የመቁጠር ፣ ብዙ ባለኃብቶች የሚረዱት አድርጎ ማሰብ ወዘተ . ። ስለሆነም በአገር ውስጥም ያሉ ከአገር ውጪም ያሉ ኢትዮጵያውያን ካቴድራሉ በዙሪያው ምንም አይነት የሚያከራየውና ገቢ የሚያገኝበት ህንጻ እንደሌለው ፣ ዙሪያውን ያሉ ነዋሪዎች በልማት ምክንያት በመነሳታቸው ከሌሎች ከተማ ዳር አካባቢ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ያነሰ ገቢ እንዳለው እንዲረዱልን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ይህንንም ከግንዛቤ በማስገባት ከ3 ወር በኃላ ሙሉ ለሙሉ ዕድሳቱ የሚጠናቀቅ በመሆኑ በዚያን ጊዜ የሚከፈል ጠፍቶ ያልተገባ እና ያልተፈለገ ችግር ላይ እንዳንወድቅ ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ ሁሉም የማሀበረሰብ ክፍል የከተማችን ታላቅ ቅርስ በመሆኑ ተረባርበን የቀረውን 85 ሚሊዮን ብር እንድንሰበስብ እንድታግዙን በአጋዕዝት አለም ሥላሴ ስም እንጠይቃለን።
ማጠቃለያ
በመሆኑም በዛሬው ዕለት የካቴድራሉን የሕንጻ ጥገና የደረሰበትን የሥራ ደረጃ ለህዝብ ለማሳወቅና የገንዘብ ማሰባሰቡን ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ይሀንን ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠት አስፈላጊ በመሆኑ በእለቱ ተገኝታችሁ የሚዲያ ሽፋን በመስጠታችሁ የካቴድራሉ አስተዳደር ፣ ሰበካ ጉባኤ እና የልማት ዐቢይ ኮሚቴው ምስጋናውን እያቀረበ ማብራሪያ በምትፈልጉባቸው ጉዳዮች ላይ ጥያቄ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት
እንገልጻለን::
ስለዚህም የሁላችንም ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡
ለዚህም የሚከተሉት አካውንቶች ተለፍተዋል፡፡
1000003778634 (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
53431186 (አቢሲኒያ)
7000022333386 (ንብ ባንክ)
01308414050300 (አዋሽ ባንክ)
{} Wegenfund
www.wegenfund.com/causes/holytrinity/
የካቴድራሉ ድረ ገጽ
www.eotehic.org
Donate
*gofundme
cofundme.com/f/wkn6c4