አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ክስተቶች በተጨማሪም ሙዚቃ እንድትሰሰሙ የመረጥልላችሁ አልበም እናደርሳቹሀ…

Reading Time: 2 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ክስተቶች በተጨማሪም ሙዚቃ እንድትሰሰሙ የመረጥልላችሁ አልበም እናደርሳቹሀለን ፡፡

መታሰብያነቱ የዛሬ ስድት አመት ላጣነው ለ #ታምራት #ደስታ ይሆናል ፡፡

-ማሪቱ ለገሰ- ማን ያኮራኛል ? የአንባሰልዋ ንግስት ማሪቱ በቅርቡ ማን ያኮራኛል? የተሰኘ ሙዚቃ ይዛ ትመጣለች ከዚህ ቀደም በሰዋሰው በኩል ''እያገማሸረ'' የተሰኘ ሙዚቃ ማድረሷ አይዘነጋም በምነው ሸዋ በኩል አዲሱ ሙዚቃዋ ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል::

-ፋሲካ አምሳሉ -ሳላይህ የተሰኘ ሙዚቃ በዚህ ሳምንት ታደርሰናለች  ግጥም እና ዜማ ኢንጅነር ፋንታ ወጨፎ ቅንብር እስከ ማስተሪንግ ኪዲ አድማሱ ነው ፡፡

-የአብስራ ገዛኸኝ- በአንቺ እና በአይኔ የተሰኘ ሙዚቃ ይዞ ሲወጣ ግጥሙን ታደለ ገለታ ዜማ ባቢ ሰሌ ቅንብር እዮብ ባልቻ ሙዚቃውን ለመስራት ሶስት አመት ከስምንት ወር የፈጀ ሲሆን የሙዚቃው ሐሳብ በሀገር እና በሚስት ቀልድ እንደ ሌለ ሁሉ ይሄም የዛ ይዘት አለው ብሏል ፡፡ በጋሜ ፊልም ፕሮዳክሽን በኩል በቅርብ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡

-ሊያ ግርማ- በቅርቡ አዲስ አልበምዋን ይዛ ትመጣለች አልበሙ ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን ቀንም እየጠበኩ ነው ስትል ገልፃለች ፡፡ አልበሙን አብረው የሰሩት ድምፃዊ ፕሮዲውሰር እንዲሁም ግጥም ዜማ ደራሲ ከሆነው ደሳለኝ አበጀ( ደስ) ጋር መሆኑን ጨምራ ገልፃለች ፡፡ እስከዛው በነጠላ ሙዚቃ የአልበም መዳረሻ ይሆን ዘንድ ሰታናለች'' ፍቅር ይዞኛል'' ይንን ሙዚቃ ደሳለኝ አበጀ (ደስ) ሙሉ በሙሉ ሰርቶላታል ፡፡

* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት

- ጣሰው ወንድም ዋሽንት ዝግጅት "የትንፋሽ ውበት '' የተሰኘውን አልበም የማስደመጥ ፕሮግራም አከናውኗል ፕሮግራሙ የተከናወነው በመሶብ ሙዚቃ ማዕከል እሁድ ሚያዝያ 6/2016 ታላላቅ የኪነ ጥበብ ቤተሰቦች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመገኘት አልበም የማሰማት ( የአልበም ድምጫ) ድግስ ተከናውኗል በቀጣይም አልበሙ በዋሽንት(በፍልሉት) የተቀነባበረም ይደርሳ ተብሎ ሲገለፅም ነበር ፡፡

-በኢትዮጲያ የጃዝ ቀን የተከበረበት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር በርካታ እንግዶች በመገኘት የሙዚቃ ባለሞያዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ሚያዝያ 6/2016 ተከብሮ ውሏል ፡፡ ከዚህ ቀደም 120 የዓለም ሀገራት በዓሉን ለማክበር ሙከራዊ እንቅስቃሴም ተደርጎ እንደ ነበር በመድረኩ የተገለፀበት ነበር ፡፡

-ፋና ላምሮት አራተኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ በድምቀት ሁኔታ የተጠናቀቀበት ሳምንት ነበር በርካታ እንግዶች በቦታው በመገኘት የሙዚቃ ድግሱን ተመልከተዋል ፡፡

16 ተወዳዳሪዎች በአሸናፊዎች አሸናፊ የተመለመሉ ሲሆን በአስራ ሁለት ሳምንት ትንቅንቅ ፈጥረው በስተ መጨረሻ አራት ደርሰው ፍፃሜን አስመልክተውናል ፡፡ በአምላክ ቢያድግል አንደኛ በመውጣት ፣ ሐብታሙ ይሄነው ሁለተኛ በመውጣት ፣ሄኖክ ብርሀኑ ሶስተኛ በመውጣት ፣  ትዕግስት አስማረ አራተኛ በመውጣት እያንዳንዳቸው የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡

- ባሳለፍነው ሳምንት ተወዳጁን #ታምራት #ደስታን ያጣንበት ሳምንት ነበር የግጥም እና ዜማ ደራሲ ታምራት ደስታ ካረፈ ስድት አመት ተቆጥረዋል ለሙዚቃ ከ ሐዋሳ እስከ አዲስ አበባ ዋጋ ከፍሏል ውድ የሆኑ አልበሞችም አድርሶልናል 1994 አኪሜነሽ ፣ 1996 አንለያይም ፣ 2000 ከ አንቺ አይበልጥም ፣ 2006 ከዚያ ሰፈር አልሞች አድርሶናል ፡፡

የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ስለ ሰጠኸን ሙዚቃዊ ስራዎች እናመሰግንሀለን ፡፡

* በዚህ ሳምንት በየኔ ቫይብ ቆየት ካሉ የምንጋብዛችሁ አልበም

- 1978 ዓም የወጣ አልበም የድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰ ሙዚቃ መረጥን፡፡  ይንን አልበም ሮሀ ባንድ በአማረ መልኩ ያቀናበሩት ሲሆን ግጥም ይልማ ገብረ አብ ዜማ አበበ መለሰ እና ደረጄ ተፈራ ናቸው ፡፡ በውስጡ አስር ሙዚቃዎች ሲሆሩት ጉድሮዬ ፣ፍቅር ነው ፣ የኔ ዓለም ፣ ለጉብል ልጅ የመሳሰሉት በአልበሙ ተካተዋል ፡፡

@biggrs @yenevibe
ስለ ምትከታተሉን እናመሰግናለን፡፡
126650cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሙዚቃዊ ክስተቶች በተጨማሪም ሙዚቃ እንድትሰሰሙ የመረጥልላችሁ አልበም እናደርሳቹሀ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE