የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 27ኛ ዓመቱን ሊከበር ነውየጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር የፊታችን ቅዳሜ ነሐ…

Reading Time: < 1 minute
*
የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 27ኛ ዓመቱን ሊከበር ነው

የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በገርጂ አንበሳ ጋራጅ አካባቢ በሚገኘው ኔክሰስ ሆቴል፣ የተመሰረተበትን 27ኛ ዓመት “በእኛ ሐብት፣ በእኛ እውቀትና በእኛ ጉልበት ወባን እናጠፋለን!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ፕሮግራሞች በድምቀት ያከብራል።

የማኅበሩ መስራችና ዋና ዳይሬክተር የክብር ዶክተር አበረ ምህረቴ በዓሉን አከባበር አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለጹት፣ ማኅበሩ በ1989 እና 1990 ዓ.ም በሀገራችን ተከስቶ በነበረው የወባ ወረርሽኝ ምክንያት የሚያልቀው ሕዝብ እረፍት የነሳቸው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን አማካኝነች ነሐሴ 17 ቀን 1990 ዓ.ም በይፋ በፀረ ወባ ማኅበር መጠሪያ እንደተመሰረተ አስታውሰዋል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የማኅበሩ የበጎ ፈቃደኛ አባላትና ባለሙያዎች የችግሩን መንስኤ በመለየት ገንዘብና መድኃኒት በመሰብሰብ ወረርሽኙ በከፋባቸው አካባቢዎች ዘመቻ ማካሄድ እንደጀመሩ ተናግረዋል። ይህ ጥረት በሕዝብና በመንግሥት ዘንድ ትልቅ እውቅናን እንዳስገኘም አክለዋል።

ማኅበሩ በመጀመሪያ በጎጃም አካባቢ በጀመረው የፀረ ወባ እንቅስቃሴ አድማሱን በማስፋት ሶስት ድርጅቶችን በማቀፍ በአስር ክልሎች ውስጥ በተለያዩ የጤና ፕሮጀክቶች ላይ እየሰራ ይገኛል።

የክብር ዶክተር አበረ ምህረቴ በዚሁ ዝግጅት ላይ ማኅበሩ ላለፉት 27 ዓመታት የተጓዘበትን የሕይወት ጉዞ የሚያሳይ “ፈጥኖ ደራሹ ማኅበር” የተሰኘ መጽሐፍ እንደሚመረቅ ተናግረዋል።

በመጨረሻም፣ ማኅበሩ ወባን ለመከላከልና ህብረተሰቡ እንዳይዘናጋ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማበረታታት፣ ሁሉም ሰው በዓመት 1,200 ብር በማዋጣት የማኅበሩ አባል በመሆን ወባን በጋራ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።
195520cookie-checkየጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር 27ኛ ዓመቱን ሊከበር ነውየጤና ልማትና ፀረ ወባ ማኅበር የፊታችን ቅዳሜ ነሐ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE