አዳማ ለአዕምሮ እድገት ውስንነት ተማሪዎች ማዕከል ሊገነባ ነው
የራዕይ የህፃናት ድጋፍ ድርጅት በአዳማ ከተማ በሚገኘው ሌተናል ኮሎኔል ደጀኔ ስሜ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ፣ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናት የእንክብካቤ ማዕከል ለመገንባት በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የራዕይ የህፃናት ድርጅት መስራች ዶ/ር ጽጌ ጥበቡ እንደገለጹት “የአዕምሮ እድገት ውስንነት ችግር ያለባቸው ህፃናት ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እና ትምህርት እንዲማሩ እንዲሁም በያዙት ሙያ ራሳቸውን እንዲለውጡ ለማስቻል መሆኑን” ገልጸዋል።
የራዕይ የህፃናት ድርጅት የበጎ ፍቃድ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር፥ ማዕከሉ ህፃናቱ የመማርና የመለማመድ ዕድል እንዲያገኙ፣ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውም እረፍት እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል።
የአዳማ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ዮሐንስ መለሰ ጽሕፈት ቤቱ በአምስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለነዚህ ተማሪዎች ትምህርት እየሰጠ መሆኑን ገልጸው፣ ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲኖር ማዕከሉ መስፋፋት እንዳለበት አሳስበዋል።
የሌተናል ኮለኔል ደጀኔ ሰሚ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ አስናቀች ደኑሳ፥ በመሰረት ድንጋይ ማስቀመጡ መደሰታቸውን ገልጸው፣ መምህራንንና ቤተሰቦችን በማሳተፍ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።
በአዳማ ከተማ የሚገኘው የሌተናል ኮለኔል ደጀኔ ሰሚ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ3ሺህ በላይ ተማሪዎችን በሁለት ፈረቃ በማስተማር ላይ ሲገኝ ከ30 በላይ ለሚሆኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ላለባቸው ህፃናትን ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ማዕከሉ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የተማሪዎቹን ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።