የቴሌግራም መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ በ5 ሚሊየን ዩሮ ዋስ ተፈታ
ዱሮቭ በግል ጄት ከአዘርባጃን ተነስቶ ፓሪስ ባረፈበት ወቅት በፈረንሳይ መንግስት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከአራት ቀናት የእስር ጊዜ በኋላ ትናንት ምሽት ፍርድ ቤት ቀርቧል፡፡
በፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረትም ዱሮቭ በ5 ሚሊየን ዩሮ ዋስ የተፈታ ቢሆንም የተጠረጠረበት የቴሌግራም የመረጃ ደህንነት ወንጀል ተጣርቶ እስከሚረጋገጥ ከፈረንሳይ እንዳይወጣ መከልከሉ ነው የተገለፀው፡፡
በድሮቭ ላይ ከቀረቡ ክሶች መካከል ህገ ወጥ ግብይት፣ ህገ ወጥ ግለሰቦች ቴግራምን ለወንጀል እንዲጠቀሙመተባበር፣ አስተማማኝ ያልሆነ የቴሌግራም አስተዳደር፣ የእፅ ዝውውር እና ለህፃናት ያልተፈቀድ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን መልቀቅ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በተጨማሪም በቴሌግራም መተግበሪያ ላይ ምርመራ እንዲደረግ አለመፍቀድ የሚል ክስም ቀርቦበታል ሲል አር ቲ ዘግቧል፡፡