ከሚሊዮኖች ወደ ቢሊዮኖች በሁለት አመት ብቻ ቃልን በተግባር

Reading Time: 2 minutes
ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዓመት የምስረታ በዓል ትናንት ሐምሌ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ” ከሚሊዮኖች ወደ ቢሊዮኖች በሁለት አመት ብቻ ቃልን በተግባር” በሚል መሪ ሐሳብ በሚሊኒየም አዳራሽ በታላቅ ድምቀት አከበረ ።

ቴክኖሎጂን በመጠቀም በዓለም ላይ በኢኮኖሚ የዳበረ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና የተከበረ ጥቁር ማኅበረሰብ መፍጠርን ተልዕኮው ያደረገው ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ የምሥረታውን 2ኛ ዓመት ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ባከበረበት ወቅት”ከገበሬው ቲቪ” (ኬቲቪ) የተሰኘው የኩባንያው ቴሌቪዥን ጣቢያ፣ የሙከራ ሥርጭቱን በይፋ የጀመረ ሲሆን ጣቢያው ትኩረቱን በግብርናና ኢኮኖሚ ላይ አድርጎ ለ24 ሰዓት እንደሚሰራጭም በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

በ1 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተመሰረተው ኩባንያው፤ በ2 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ካፒታሉን ወደ 2 ቢሊዮን ብር ማሳደግ መቻሉን የፐርፐዝ ብላክ መሥራችና ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ በክብረ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር አስታውቀዋል፡፡

እስካሁን በ10ሺ የሚሰሉ አርሶአደሮችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን፣ የፐርፐዝብላክ ባለአክሲዮኖች መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ኩባንያው ባለፉት ሁለት ዓመታት፣ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል ምርቶችን በቀጥታ ከገበሬው በማምጣት፣ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ሲያከፋፍል ቆይቷል፡፡

ፐርፐዝብላክ፣ በከተማዋ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የመኖርያ ቤት ችግር ለማቅለል በማለምም፣ በቅርቡ ፊቱን ወደ ሪልእስቴት ግንባታ ያዞረ ሲሆን፤ ዜጎች በተመጣጣኝ ዋጋ መኖሪያ ቤት የሚያገኙበት ፕሮጀክት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም፣ የዩኒቲ ኮሌጅ መሥራችና ባለቤት በነበሩት ዶ/ር ፍስሃ እሸቱ፣ጠንሳሽነት የተቋቋመው ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ፤ የጥቁርን ህዝብ የኢኮኖሚ የበላይነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በሥራ ለማዋል እየተጋ የሚገኝ ኩባንያ ሲሆን፤ በቅርቡ አዲስ ሁለገብ የበይነመረብ መገበያያ መድረክ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

56800cookie-checkከሚሊዮኖች ወደ ቢሊዮኖች በሁለት አመት ብቻ ቃልን በተግባር

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE