''
ትዝታ ሙዚቃ ብዙ አመለካከት አለኝ ብዙ ጊዜ ስለ ፍቅር ስንገልፅ ትዝታ አለሁ '' ግጥም ዜማ ደራሲ ሙዚቀኛ ጋሽ ሙሉቀን መለሰ (ሙሉቀን ተዓምር ጥሩነህ) 1946-2016 (71አመት ቆይታ)
ለየት ባለ ሙዚቃዊ ቀለም የሚታወቀው ተወዳጁ አንጋፋ የቀድሞ ድምፃዊ የአሁን ዘማሪ ሙሉቀን መለሰ ወይም (መሉቀን ተዓምር ጥሩነህ) ማረፉን የተሰማንበት ሳምንት ነበር፡፡
አንጋፋው ሙዚቀኛ የተወለደው በጎጃም ክፍለ ሀገር አነዳድ ወረዳ ውስጥ ኪዳነ ምህረት በምትባል መንደር በ 1946 ዓ.ም ሲሆን እስከ 10 አመቱ በዚያው ከ ቆየ በኃላ በአጎቱ አማካኝነት ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትምህርቱን በጳውሎስ ትምህርት ቤት ተማረ በትምህርት ብዙም አልገፋም ኑሮን ለማሸነፍ ሙዚቃው ዓለም ገና በለጋ እድሜው በ ፋብሊስ ሙሉንባ( በአሰገች ካሳ ) የምሽት ክለብ ተቀላቀለ በዛም በወር 80 ብር እየተከፈለው አገለገለ ፡፡
በመቀጠል ለሁለት ዓመት ካገለገለ በኃላ ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ በመቀላቀል ከ ጋሽ ተስፋዬ አበበ፣ ሻምበል አፈወርቅ መርሻ ፣ ጋሽ ተስፋዬ ለሜሳ ሙሉቀን መለሰን ይዘው ያ ልጅነት ፣ እናቴ ስትወልደኝ ፣ የዘላለም እንቅልፍ የመሳሰሉ ሙዚቃዎች ሰርተው ለ ሶስት አመት አብረው ዘልቀዋል ፡፡
ያ ልጅነት የተሰኘው ሙዚቃ በልጅነቱ ከ ፖሊስ ኦርኬስት ጋር የጋሽ ተስፋዬ አበበ ግጥም እና ዜማ የሰዎች ቀልብ ይስብ ነበር ፡፡
ያ ልጅነት በጊዜአቱ
ደስ ማለቱ …
በሸክላ ሙዚቃ ስራ ካበረከተልን መሀከል ከኢኪዌተርስ ባንድ ጋር ሁለት ሙዚቃዌችን አበርክቷል በሚስጥር ቅበሪኝ እና እንታረቅ ወይ የተሰኙ ስራዎች አበርክቷል ፡፡
''
ቢቻዬን ስለሆንኩ ምቀቱ ይጎዳኛል
ሳጥን አትጊዢልኝ አፈር ይበቃኛል
መጀመርያ ወደሽ አሁን ከተጠላሽን
ሰዎች እንዳይሰሙ በሚስጥ ቅበሪኝ''…
ተወዳጁ ሙሉቀን መለሰ ከ በርካታ ባንድ ጋር ሰርቷል ኢትዮ ስታር ባንድ ፣ ዳህላክ ባንድ ፣ ሮሀ ባንድ ፣ ኢኳቶር ባንድ ፣ ፈጣን ኦርኬስትራ ባንድ ፣ ኢኪዌቴርስ ባንድ ከመሳሰሉት ጋር ሰርቷል ፡፡
ግጥም ዜማ ያገዙት ተስፋዬ ለሜሳ ፣ የሸዋ ልዑል መንግስቱ ፣ ተስፋዬ አበበ (ፋዘር) ፣ ሻንበል መኮንን መርሻ ፣ ሰለሞን ተሰማ ፣ አለም ፀሐይ ወዳጆ ፣ ይልማ ገብረዓብ ኮከብ ፀሐፍት ጋር አብሮ ሰርቷል ፡፡
በቅንብሩ አብሯቸው ከሰራው መካከል ጀረጄ መኮንን ፣ ግርማ በየነ ፣ ጥላዬ ገብሬ ፣ ዳዊት ይፍሩ ፣ ሙላቱ አስታጥቄ ፣ አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሽዎታ እና የመሳሰሉት ሰርቷል ፡፡
ከዳህላክ ባንድ ጋር አብሮ ሰራው መካከል ጥቂቱን በእርግጥ አገኘሽ ወይ ፣ ዓይኔማ ወዳጄ፣ ገላዬዋ ፣ ናኑ ናኑ ናዬ ፣ የመሳሰሉት አብሮ ሰርቷል ፡፡
በሙዚቃ በዘፈን ዓለም 1958-1980 አመተምረት መገባጃ በ22 አመት ቆይታ ዘመን የማሽራቸው ሙዚቃዎች አበርክቷል ፡፡
ወደ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ከተቀላቀለ በኃላ የመጀመርያ አልበሙ ሀሌሎያ የተሰኘ በመቀጠል አቤነዘር የእግዚሐብሔር እርዳታ ፣ ስለ ምሕረትህ ፣የየሱስወታደር ነኝ በርካታ ሙዚቃ እስከ ሕልፈተ ሕይወቱ ድረስ አርሶናል ፡፡
በኢትዮጲያ ታሪክ ወስጥ ጉልህ አሻራ ያለው ተወዳጁ ድምፃዊ ሙሉቀን መለሰ በሰባ አንድ አመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል ፡፡
ለወዳጅ ዘመድ ፣ ለ አድናቂዎቹ ፣ ለቤተሰቡ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ክፍል ይመኛል ፡፡
"
ቀኑ ሲረዝምብሽ እኔ ካላየሺኝ
ጭንቀት ሲበዛብሽ ለኔ ካልነገርሺኝ
ይንን የሚያዋየኝ ያ ሁሉ አንደበት
ዛሬ ለይቅርታ ምነው ረፈደብሽ" ሮባ ባንድ ሙሉቀን መለሰ ፡፡
ነፍስ ይማር ሙዚቃ…
@biggrs @yenevibe