የዋጋ ንረትን የሚያረጋጋ ለግብይት ተመጣጣኝ  አዘጋጅተዋል ፡፡ማህበረሰቡ በአል በመጣ ቁጥር ከሚገጥመው የዋጋ…

Reading Time: < 1 minute
የዋጋ ንረትን የሚያረጋጋ ለግብይት ተመጣጣኝ  አዘጋጅተዋል ፡፡

ማህበረሰቡ በአል በመጣ ቁጥር ከሚገጥመው የዋጋ ንረት ለመታደግ ፋሲካን በሚኒሊየም አዳራሽ ኤክስፖና ባዛር  ሊደረግ እንደሆነ   አዘጋጁ ባሮክ ኢቨንት ኦርጋይነዘር  ዛሬ መጋቢት 26/2016  በሚኒሊየም አዳራሽ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ  በሀገራችን የተለያዩ ሁነቶችን (ኢቨንቶችን) በማዘጋጀት ሕጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ነው።የዘንድሮውን የ2016 ዓም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አስመጪዎች እና አምራቾች ከሸማች ማህብረተሰቡ ክፍል ጋር እየተዝናና የሚገበያይበትን የፋሲካ ባዛር ና ኤክስፖ ከሐሙስ ሚያዚያ 10 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ቅዳሜ ሚያዚያ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ ለነጋዴዎች እና ለሸማቾች ለትራንስፖርት አመቺ እንዲሁም በተንጣለለ ብዙ መኪናዎችን ማቆም በሚችለው እና አስተማማኝ ጥበቃ ባለው በታላቁ ሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡

በዚህም የፋሲካ ባዛር እና ኤክስፖ ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል በአልን ምክንያት አድርጎ ከሚገጥመው የዋጋ ንረት በተመጣጣኝ እና በቅናሽ ዋጋ ከራሱ ከአምራቹና ከአስመጪው የሚገበይበት ሲሆን አምራች ከሸማቹ
ከፍተኛ  የገበያ ሽያጭ በማግኘት ተጠቃሚ የሚሆንበት ነው።

ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ  የመዝናኛ ፣የምግብ እና የመጠጥ ፕሮግራሞች የሚገኝበት ባዛር እና ኤክስፖ ነው።

ይህ ልዩና ደማቅ የሆነ ባዛር እና ኤክስፖ የፊታችን

ሚያዚያ 12 ቀን 2016
ዓ.ም:-
👉 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት
👉ሚኒስትሮች
👉 ባለሀብቶች
👉የሚዲያ ባለሙያ እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት በይፋ ይከፈታል።

በዚሁ የፋሲካ ኤክስፖ ላይ  ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ከመወጣት አንፃር ለበጎ አድራጎት ተቋማት በነፃ ስራዎቻቸውን ለህብረተሰቡ እንዲያስተዋውቁ ከማድረግ ባለፈ  እጅ ያጠረባቸውን ወገኖች በዓልን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲውሉ
ድጋፍ ያደርጋል።

በዝግጅቱም ላይ አልባሳት ፣የስጦታ እቃዎች ፣ አቅራቢና አስመጪ ፣ የምግብና መጠጥ ሻጮች፣የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት ሲሆን በአጠቃላይ ከ2000 በላይ አስመጪና ሻጮች የሚሳተፉበት ሲሆን በዚህም ዝግጅት በቀን ከ7 ሺህ -10 ሺ ሸማቾች ተብሎ ይገመታል።

ከዚህም በተጨማሪ በየቀኑ ለሃገራችን የሚገኙ ባህላዊ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ባለሙያዎች በየቀኑ ተወዳጅ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን በተወዳጅ ባንዶቻቸው በመታጀብ ያቀርባሉ ፣በዚህ ዝግጅት የባሮክ ኢቨንት ኦርጋናይዘር  የዘወትር አጋር የሆነው እናት ባንክ ሌሎች አጋሮች ይገኙበታል ።
86340cookie-checkየዋጋ ንረትን የሚያረጋጋ ለግብይት ተመጣጣኝ  አዘጋጅተዋል ፡፡ማህበረሰቡ በአል በመጣ ቁጥር ከሚገጥመው የዋጋ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE