ከቲቪ ይልቅ በቦታው ሆኖ የሚታይ የሙዚቃ ስሜት ዳኝነት ፈታኝ የሆነበት ከፍፃሜው ቀድሞ የሙዚቃ ውድድር ፋና ላምሮት አንዱ ድምቀት ስሜቶችን ሲመጡ እንደ እየ ስሜቶቹ መቀበል ዛሬ በታየው አስደናቂ ውድድር የእለት ዝግጅት ከ እለት ጉዞ ዛሬ እና ዛሬ የሚለካ ነው ደስታ ፣ ሰቅሶ ፣ ንዴት ፣ ቁጭት የተንፀባረቀበት መድረክ ነበር ፡፡
በስምንተኛ ሳምንት በአስራ አራተኛው ምዕራፍ በፋና ላምሮት ቤት በታሪክ ሶስት ሴት ተወዳዳሪ ለፍፃሜ ጉዞ ቀርቦ አያውቅም ፡፡
በዛሬ የታየው ማንነትን ፍለጋ ፣ ራስን መሆን ፣ የራስ መተማመን ፣ የማይክ አጠቃቀም ፣ ቫልዩ አድ ፣ ጥንቅቅ ያለ ዝግጅት አቀራረብ ፣ ቅኝት ፣ ትንፋሽ አያያዝ መቆጠብ ፣ ትልቁ የተሰነሳው የሙዚቃ ምርጫ ፣ ውበት ፣ ዳይናሚክ ፣ ጆሮ ያዝ ዝግጅት ፣ አስገራሚ ትንቅንቅ ፣ ከ ባንድ ጋር ውህደት የመሳሰሉት ቀርበዋል ፡፡
ከሌሎቹ ሳምንታት የሚለየው የተጋባዥ ዳኛ ሌላ አራተኛ ዳኛ መቅረቡ ነው የእለቱ ዳኛ የሆነው ሙዚቀኛ አብይ መንበሩ ነው አብይ ሁለ ገብ የሙዚቃ ሰው ነው አቀናባሪ፣ የቡድን መሪ፣ የባንድ መሪ ሆኖ እና በአሰልጣኝነት ሰመርቷል ፡፡
በትያትር ቤት ፣ ማስታወቅያ እና ፊልም ሙዚቃዎችን አቀናብሮሯል ፡፡ የሙዚቃ ባንድ ያዋቀረው የቤኒሻንጉል እና የአፋር ክልል ሙዚቃ ቡድኖችን ተጠቃሽ ነው ፡፡
በፊልም ላይ ከአቀናበራቸው መካከል የአማላይ ፊልም ፣ የብርሀን መንገድ የሙዚቃ ድራማ ፣ ለሕንኬ ቴያትር ፣ የ13 ወር ፀጋን ሙዚቃዊ ትያትር ሰርቷል ፡፡
በዛሬ እለት ተጋባዥ ሆኖ ለሁሉም ተወዳዳሪዎች ምክርም ነጥብ ሰቷል ፡፡
ዛይን ባንድ ከተወዳዳሪዎች ጋር በመሆን ወደ 10 የሚጠጉ ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል ፍቅርአዲል ነቃጥበብ /ዝም እላለሁ/፣ በዛወርቅአስፋው /ወዳጅ ያጣ ጎጆ/ ፣ ሙሉቀን መለሰ / አንቺን መሳይ ቆንጆ/ ፣ ፀጋዬ እሸቱ /ሰላም/ ፣ ትዕግስት ፋታሁን /ሐያል ፍቅር/ ፣ የአበበ ተካ /ሰው ጥሩ / የመሳሰሉት በመድረክ ላይ ተዚመዋል ፡፡
ዳኞች ለ ሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት አስተያየታቸውን በጥቂቱ …
* አቤል ሙሉጌታ :- እየጠረብን እየጠረብን እዚህ ደርሰናል እዚህ መብቃታችሁ ደስ ብሎኛል / አፀደ ማርያም ያረጋል – ዝም እላለሁ
* ብሌን ዮሴፍ :– ራስን ማሸነፍ ከውድድር በላይ ነው ለ አፀደ ማርያም ያረጋል -ዝም እላለሁ
* ብሩክ አሰፋ :- ሙዚቃ ስልትም አርትም ጥበብም ነው በቃ ይህ ታይቷል ፡፡ / ለባምላክ ቢያድግልኝ
አጠቃላይ ውጤት ለተወዳዳሪዎች የተሰጣቸው …
*አፀደማርያም ያረጋል
* በአምላክ ቢያድግልኝ
* ትንሳኤ ስለሺ
* ትዕግስት አስማረ
የዛሬው ተሰናባች ለማመን የሚከብድ ሁሌም ፋና ላምሮት በጉዞ ላይ እንዲህ አይነት የተለመደ በምታቀርበው ልክ ይለካል ይሆናል ፡፡ በየዙሮቹ ድንቅ ተወዳዳሪ የሆነችሁ የሴትም የወንድም ሙዚቃን ጥንቅቅ አርጋ የምታቀርበው ከ ዳኞች ጭብጨባ ፣ ከተየልካች አድናቆትን ያገኘችሁ ድምፃዊት ራሄል ተሬሳ ናት ፡፡
ዛሬ ያቀረበችሁ የፍቅር አዲስንን እና የአብነትን ሙዚቃ አቀረበች ድንቅ ነበር የሙዚቃ ምርጫ ትልቅ አቅም አለሁ ያ ነው ሳያሳልፋት የቀረው ግን በድምፃዊነቷ ምንም ጥርጥር እንከንም የለውም ፡፡
ፋና ሁሌ ከጎንዋ ሆኖ ከ30000 ሺህ ብር ጋር ከመልካም እድል ጋር ሸኝቷል ፡፡
በእርግጠኝነት ፋና ቤት ሁሌም ቀና ነው የአሸናፊዎች አሸናፊ ላይ መልሰን የምናያት ይመስላል ከዚህ በፊትም ዮርዳኖስ ደስይበለውን በዚህ ስሜት በሚነካ መልኩ ነበር የተሰናበተችው ኃላ ተመልሳ መጣች ፡፡
የሚቀጥለው ፍፃሜ ዉድድር እንገኛኝ …
እዛው በቦታው ሆነን እናቀርባለን
ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት