በአሜሪካ አንዲት እናት የሰባት ወር ልጇን ለቅሶ ለማስቆም ስትል የአልኮል መጠጥ በጡጦ በመስጠቷ ክስ ተመሰርቶባታል

Reading Time: < 1 minute

አሜሪካዊቷ ግለስብ የሰባት ወር እድሜ ያለው ልጇ ማልቀሱን አላቆም ሲላት የአልኮል መጠጥ በጡጦ ሰጥታዋለች። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃኖች እንደዘገቡት ከሆነ ይህቺ የ37 አመት እናት ህጻን ልጇን ማልቀሱን ለማስቆም በጡጦ ውስጥ መጠጡን መስጠቷን ተግበዋል።

ድርጊቱ ከሎስ አንጀለስ በስተምስራቃዊ ክፍል ወጣ ብሎ በሚገኝ አካባቢ የተፈፀመ ሲሆን ህፃኑ ማልቀስ እንዲያቆም መጠጥ ብትሰጠውም የስካር ምልክት እንደታየበት ተገልጿል።

በስተመጨረሻም ድርጊቱ እንደታወቀ በልጆች ላይ አደጋ በማድረስ በሚል ወንጀል ክስ እንደተመሰረተባት ታውቋል።
57810cookie-checkበአሜሪካ አንዲት እናት የሰባት ወር ልጇን ለቅሶ ለማስቆም ስትል የአልኮል መጠጥ በጡጦ በመስጠቷ ክስ ተመሰርቶባታል

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE