ዳኞች በበኩላቸው ድርጊቱን የፈጸምነው ተወዳዳሪዎች ሰውነታቸው ለውድድር ብቁ መሆኑን ለመገምገም ነዉ ቢሉም የቁንጅና ተወዳዳሪዎቹ ጉዳዩን ወደ ህግ መውሰዳቸውን አስታውቀዋል
በኢንዶኔዢያዋ መዲና ጃካርታ በየዓመቱ የሚካሄደው የሚስ ዩንቨርስ የቁንጅና ውድድር ዘንድሮ ትችቶች እየተሰነዘሩበት ይገኛሉ።
በዚህ ውድድር ላይ የተለያዩ ሀገራት ቆነጃጅት በመወዳደር አሸናፊ የሆኑት በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነትን አትርፈውበታል።
በየዓመቱ በሚካሄደው በዚህ ውድድር ላይ ዳኞች የተወዳዳሪዎችን ሰውነት ለማየት በሚል ራቁታቸውን እንዲሆኑ እንደጠየቁ ተወዳዳሪዎቹ ለፖሊስ ተናግረዋል ሲል ቢቢሲ ነዉ የዘገበዉ።
ባሳለፍነው ሳምንት በተካሄደው በዚህ የፍጻሜ ውድድር ላይ ያለፉ ቆነጃጅቶች ወንዶች በተገኙበት ክፍል ውስጥ ልብሳችንን እንድናወልቅ ተደርገናል ይህ ደግሞ መብታችንን መጋፋት ነው ሲሉ ክስ መመስረታቸዉ ተሰምቷል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ