የካሜሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆነው ኤቶ የአገሩን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያስተዳድርበት መንገድ ጥያቄ ውስጥ በመግባቱ ምርምራ ተከፍቶበታል።
ባለፈው ወር የተወሰኑ የካሜሩን ክለቦች ኤቶ በሙስና ከታችኛው ዲቪዝዮን ክለብ አሳድጓል በሚልና መሰል ክሶች ሥልጣን እንዲለቅ በጉዳዩ ፊፋ ጣልቃ እንዲገባ ጥያቄ በማቅረባቸው አዲስ ምርመራ ተከፍቶበታል ነው የተባለው።
ኤቶ ኳታር ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጨ ወቅት አንድ ግለሰብ መትቷል ተብሎ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።