ባሌ አስታዋሽ ምትኩን ሰጥቶኛል የምትለው እናት በምን ተአምር ህይወቱ ካለፈ ባሏ ልትወልድ እንደቻለች ትናገራለች።
ጃሰንና ሲያን የተባሉት አውስትራሊያውያኑ ጥንዶች የረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ሲሆኑ፤ በ 2017 ጃሰን በፍቅርን ክንፍ ላለላት ስያን የታገቢኛለሽ ጥያቄ አቅርቦ ይሁንታዋን ባገኘ በስድተኛው ቀን ለቀላል ህክምና ባመራበት ሆስፒታል ደረጃ 4 የጉበት ካንሰር እንዳለበትና ከቀናት በኋላም ህይወቱ እንደምታልፍ ይነገረዋል።
በሞት አፋፍ ላይ የነበረው ጃሰን ለፍቅረኛው እሱ ቢሞትም ህይወት ስለሚቀጥል ሌላ አግብታ እንድትኖር ቢመክራትም ሲያን ግን “ሌላ አላገባም” በሚል አቋም ጸናች፤ ሀኪሞችን ስታማክር የባሏ የዘር ፍሬ ከመሞቱ በፊት ቢወሰድ ለረጅም ጊዜ ሊቀመጥ እንደሚችልና በቤተሙከራ ጽንስ ሊፈጠር እንደሚችል ተነገራት። እናም የጃሰን የዘር ፍሬ ተወስዶ በቀዝቃዛ ስፍራ ተቀመጠ።
ከዚያም የዘር ፍሬው ከሲያን እንቁላል ጋር በላቦራቶሪ ተዋህዶና ጽንስ ሆኖ በሰው ሰራሽ ማህጸን ወይም ሽል እንዲቆይ ተደረገ። ይህ ጽንስም በቀዶ ህክምና ወደ ማሕጸኗ እንዲገባ ተደርጎ ከስድስት ወራት በኋላ በታህሳስ 2022 (ባሏ ህይወቱ ካለፈ ከሶስት አመት በኋላ) ማቲልዳ የተሰኘች ልጅ ወልዳለች ብሏል ዴይሊ ሜል በዘገባው።
573600cookie-checkከ3 አመት በፊት ከሞተ ባሏ የመጀመሪያ ልጇን በቅርቡ የወለደችው እናት መነጋገሪያ ሆናለችno
ጃሰንና ሲያን የተባሉት አውስትራሊያውያኑ ጥንዶች የረጅም ጊዜ ፍቅረኛሞች ሲሆኑ፤ በ 2017 ጃሰን በፍቅርን ክንፍ ላለላት ስያን የታገቢኛለሽ ጥያቄ አቅርቦ ይሁንታዋን ባገኘ በስድተኛው ቀን ለቀላል ህክምና ባመራበት ሆስፒታል ደረጃ 4 የጉበት ካንሰር እንዳለበትና ከቀናት በኋላም ህይወቱ እንደምታልፍ ይነገረዋል።
በሞት አፋፍ ላይ የነበረው ጃሰን ለፍቅረኛው እሱ ቢሞትም ህይወት ስለሚቀጥል ሌላ አግብታ እንድትኖር ቢመክራትም ሲያን ግን “ሌላ አላገባም” በሚል አቋም ጸናች፤ ሀኪሞችን ስታማክር የባሏ የዘር ፍሬ ከመሞቱ በፊት ቢወሰድ ለረጅም ጊዜ ሊቀመጥ እንደሚችልና በቤተሙከራ ጽንስ ሊፈጠር እንደሚችል ተነገራት። እናም የጃሰን የዘር ፍሬ ተወስዶ በቀዝቃዛ ስፍራ ተቀመጠ።
ከዚያም የዘር ፍሬው ከሲያን እንቁላል ጋር በላቦራቶሪ ተዋህዶና ጽንስ ሆኖ በሰው ሰራሽ ማህጸን ወይም ሽል እንዲቆይ ተደረገ። ይህ ጽንስም በቀዶ ህክምና ወደ ማሕጸኗ እንዲገባ ተደርጎ ከስድስት ወራት በኋላ በታህሳስ 2022 (ባሏ ህይወቱ ካለፈ ከሶስት አመት በኋላ) ማቲልዳ የተሰኘች ልጅ ወልዳለች ብሏል ዴይሊ ሜል በዘገባው።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ