በአዲስ አበባ የኮንዶም እጥረት መኖሩ ተገለፀ

Reading Time: < 1 minute



መድኃኒት ቤቶቹ በፊት ከሚረከቡት ዲኬቲ ኢትዮጵያ የሚፈልጉትን ያህል ኮንዶም ማግኘት ባለመቻላቸው ምክንያት፤ ከዲኬቲ ኢትዮጵያ ገዝተው ካከማቹ ሻጮች እየገዙ እንደሚገኙ ነው የጠቆሙት።በዲኬቲ ኢትዮጵያ በ768 ብር የሚሸጥ አንዱ እሽግ ህይወት ትረስት ኮንዶም፤ ከጥቁር ገበያ በ864 ብር እንደሚሸጥም ተመላክቷል። እንዲሁም ከዲኬቲ በ1 ሺሕ 56 ብር የሚገዛው ሰንሴሽን ኮንዶም፤ በጥቁር ገበያ በ1 ሺሕ 200 ብር እንደሚገዛ ነው የተገለጸው።በጤና ሚኒስቴር በኩል መሸታ ቤቶችና ፔንሲዮኖች ኮንዶም የማስቀመጥ ግዴታ የተጣለባቸው በመሆኑ፣ በውድ ዋጋ እንደሚገዙም ተመላክቷል። የመድኃኒት ቤት ባለቤቶች ሰንሴሽን ኮንዶም ከጠፋ መቆየቱን ጠቅሰው፤ በዚህ ወቅትም “ሴንሴሽንን ጨምሮ ሕይወት ትረስት ኮንዶም ለማግኘት ዲኬቲ ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም “ሳምንት ይገባሉ” ከማለት በስተቀር እስከአሁን ምንም ነገር አልተሰጠንም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል።ይህን ተከትሎም በተለይ በመሸታ ቤቶች የሚሰሩ ሴቶችን ለኤች አይ ቪ፣ የአባላዘር በሽታዎች እና ላልተፈለገ እርግዝና ተጋላጭ አድርጓቸዋል ነው የተባለው።
56570cookie-checkበአዲስ አበባ የኮንዶም እጥረት መኖሩ ተገለፀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE