በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የውጭ ወራሪ ጠላትን ከመመከት ታላቅ ታሪኮች ውስጥ የሚመደበው የኢትዮ-ሶማሊያ( የኦጋዴን ) ጦርነት የተጀመረው በዛሬዋ እለት ሃምሌ 6 1969 ዓ.ም ነበር።
ፕሬዝደንት አብዲራሺድ አሊ ሸርማርኬን በመንፈቅለ-መንግሥት ፈንግሎ ሥልጣን የጨበጠው የሜጀር ጀነራል ዚያድ ባሬ መንግስት በ1966 የ አረብ ሊግን ከተቀላቀለ ሁሃላ መስፋፋትን እና ታላቋ ሶማሊያ ብሎ የሰየማትን ግዛት የመመስረት ሃሳብን ዋና አላማው አደረገ።ለዚህ መስፋፋት ዋና ነጥብ እና ትኩረት የነበረችው ደግሞ የኢትዮጵያ ሶማሌ ግዛት ኦጋዴን ነበረች።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
ወቅቱ ኢትዮጵያ ከ ንጉሳዊ ወደ ወታደራዊው የደርግ አገዛዝ የተቀየረችበት ጊዜ ነበር።የዚያድ ባሬ ጦር ጥቃቱን እያጠናከረ ወደ ጅግጅጋ ድንበር ደረሰ። ፡ድንበሩንም አልፎ በዋርዴር፣ቀብሪድሃር እና ሌሎች ከተሞች ላይ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ጨረሰ።አልፎ ወደ ሃረር መገስገስ ሲጀምር ግን ኮሎኔል መንግስቱ ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር ብለው ሃገራዊ የ ክተት አዋጅ አስተላለፉ። እጅግ ባጭር ጊዜ ውስጥ የተሰበሰበ እና የሰለጠነ ከ40 ሺ በላይ ጦር ወደ ሃረር ተመመ።በወቅቱ የኩባ መሪ በነበሩት ፊደል ካስትሮ የተላከ ወደ 10ሺ የሚቆጠር የኩባ ሰራዊትም አብሮ ነበር።
10% የማይሞላ የኦጋዴንን መሬት ተቆጣጥሮ የነበርው የኢትዮጵያ ሰራዊት በብዙ መስዋትነት ወራሪውን ጦር እየገፋ እየገፋ ወደ ካራማራ ተራሮች ድረስ መለሰው።ጦርነቱ ካራማራ ተራሮች ላይ የካቲት 26 1970 ፍፃሜውን ሲያገኝ ኢትዮጵያ ኦጋዴንን መልሳ ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥራ ነበር።
የጦርነቱ ውጤት ዚያድ ባሬ ተቀባይነት እንዲያጣ ሶማሊያም ወደለየለት መታመስ እንድትገባ መንገዱን ጠረገ። ጀነራሉ በ 1983 ከስልጣን ተወግዶ ወደ ናይጀሪያ ሸሸ።የህይወቱ ፍፃሜም ከ4 አመታት ቡሃላ እዛው ናይጀሪያ ውስጥ ሆነ።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ