ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ የሰሜኑ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቱ እና በወቅቱ በትግራይ ክልል ተገኝቶ ሕዝቡን ባለመጠየቁና ባለማጽናናቱ ይቅርታ ጠየቀ

Reading Time: < 1 minute

የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመታቸዉ ይከናወናል ተብሏልቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ልዩ ጉባኤ ማጠናቀቁን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያዎች በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በሁለት ዐበይት አጀንዳዎች መወያየቱን ገልጾ የኤጲስ ቆጶሳትን ሹመት በተመለከተ የተመረጡ ቆሞሳትን ይፋ በማድረግ የፊታችን ሐምሌ ዘጠኝ ሢመቱ እንደሚፈጸም አስታውቋል።በሌላ በኩል በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣ በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንንና መላው ሕዝበ ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣ ጦርነቱ ቁሞ በሀገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ መጠየቁን በንባብ ከተሰማው የቅዱስ ሲኖዶሱ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
55310cookie-checkቅዱስ ሲኖዶስ ፤ የሰሜኑ ጦርነት በተካሄደበት ወቅት ጦርነቱ እንዲቆም መግለጫ ባለመስጠቱ እና በወቅቱ በትግራይ ክልል ተገኝቶ ሕዝቡን ባለመጠየቁና ባለማጽናናቱ ይቅርታ ጠየቀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE