የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራ ለቀቁ

Reading Time: < 1 minute

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራቸውን በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋ አስታውቀዋል፡፡በጤና ምክንያት የረጅም ጊዜ እረፍት የሚያስፈልገኝ ሆኖ በመገኘቱ ከነሀሴ 1/2015 ጀምሮ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቦርድ ሰብሳቢነቴ በገዛ ፍቃዴ መልቀቄን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ጽህፈት ቤት ሰኔ 5/2015 አሳውቄያለሁ ብለዋል። ሰብሳቢዋ ሥራ እሰከሚያቆሙበት ቀን ድረስ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን የማጠናቀቅ እና አስተዳደራዊ ሽግግር ሥራዎችን ለመሥራት ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡም አስታውቀዋል፡፡ በ2011 ታህሳስ ወር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ በመሆን ከተሾሙበት ቀን ጀምሮ፤ ቦርዱ ራሱን ችሎ ምርጫን ማከናወን የሚችል ተቋም ለማድረግ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደተወጡም ኃላፊዋ ጠቁመዋል፡፡ ሰብሳቢዋ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ባለፉት አራት ዓመት ከስድስት ወራት ሦስት ህዝበ ውሳኔዎችን እና አገራዊ ምርጫን በማካሄድ እና ፓለቲካ ፓርቲዎችን በማስተዳደር የተሰጡኝን ኃላፊነቶች ህጋዊነት ፍትሀዊነት እና ቅንነትን በተከተለ ሁኔታ ለማከናወን ስጥር ቆይቻለሁ” ብለዋል።
55160cookie-checkየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ሥራ ለቀቁ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE