በመቱ ከተማ የተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ተሰማ!

Reading Time: < 1 minute

በኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን መቱ ከተማ ከምሽቱ 11 ሰዓት ተኩል በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ማንኛውንምተሸከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ መታገዱን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል።እገዳው የተጣለው ከባለፈው ሰኞ ሰኔ 12/2015 ጀምሮ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ በዞኑ ሥር በሚገኘው አሌ ወረዳ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሸከርካሪ እንዳይንቀሳቀስ ከታደገ ቀናት ማስቆጠሩ ተጠቁሟል። የእገዳው ምክንያት በአካባቢው የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በሰፊው እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ተከትሎ፤ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት እና የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎቹን አድኖ ለመያዝ በሚል መሆኑም ነዋሪዎቹ አመላክተዋል። በዚህም ሳቢያ ማህበረሰቡ ከቦታ ቦታ ለመስቀሳቀስ በእጅጉ እየተቸገረ ነው የተባለ ሲሆን፤ በተለይም ከመኖሪያቸው ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደው የሚሰሩ ሰዎች በሰዓት ሥራ ቦታቸው ለመድረስም ሆነ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡በተለይ በከተማው ሰፊ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ባለሦስት እግር ተሸከርካሪዎች መሆናቸውን በመጥቀስ፣ ከእገዳው ጋር ተያይዞ ባለንብረቶች ለችግር መዳረጋቸው ነው የተገለጸው።
55140cookie-checkበመቱ ከተማ የተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ መጣሉ ተሰማ!

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE