/ሙያን ከቬሮኒካ አዳነ ጋር / በቅርቡ…
*ቬሮኒካ ማለት ምን ማለት ይሁን ቬሮኒካ ማለት በጣልያንኛ ” ማሸነፍ” ነው ብላናለች::
በተጨዋሪም ስትናገር ” እኔ ደሞ አድጌ መፅሐፍ ቅዱስ ታምረ እየሱስ ላይ ስፈልግ ጌታች መዳኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ ከተሰቀለበት ሲወርድ ደሙ የጠረገችለት የመጀመርያዋ ሴት ስምዋ ቬሮኒካ ትባላለች ” ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ፡፡
በመቀሌ ዩንቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት / በንቨስትጌት ጆርናል / የምርመራ ጋዜጠኛ ተምራ ተመርቃለች ከተመረቀችም በኃላ ለ አንድ አመት በጋዜጠኝነት ዘርፍ /በኮሚኒኬሽን እና ጋዜጠኝነት/ ስራ ቆይታለች፡፡
የሙዚቃ ፍቅር ያደረባት በልጅነቷ ቢሆንም ድምጿን ሟሟሸት የጀመረችው በመቀሌ ዩንቨርሲቲ ነው ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅማ ተስዕጦዋን ስታወጣ ነበር በኢንስታ ግራም ፣በዩትብ ብዙ ተከታዮችን አፈራች በምትሰራበት መስርያ ቤት ሙዚቃ ለመስራት እድል ተመቻችቶላት ሰርታለች ፡፡
የታዋቂ ድምፃዊያን ሙዚቃ የአስቴር አወቀ ፣ ቴዎድሮስታ ታደሰ፣ የተሾመ ምትኩ የመሳሰሉትን ትጫወታለች፡፡
በይበልጥ የተሰማችው በተሾመ ምትኩ / ሰማይ ሲላወስ/ የወንድን ዘፈን ወደ ራስዋ ቀለም አምጥታ ስትዘፍን በይበልጥ ወደ ህዝቡ ተስባለች እንዲህ እንዲህ እያለች በከቨር ሙዚቃዎችን መስራት የጀመረችው ቬሮኒካ አዳነ ተካ ወደ የራስዋን ሙዚቃ በመምጣት ናልኝ፣ ተዉ ፣አበባዬ ፣ ጥፍጥ አለኝ ፣ ኩርፍያ ፣ ከ አክስዮን ባንድ ጋር ዘመዴ ሙዚቃ ቅንብሩን ዳግማዊ አሊ የሰራው፣ አባይ ማዶ ከ ከነገስታት ጋር ከተወዳጅ ዜማ ግጥም ደራሲ እና አቀናባሪዎች ጋር ሰርታለች ፡፡
አሁን ደሞ በተማረችበት የሞያ መስክ በጋዜጠኝነት ለመስራት ብቅ ለማለት እየተሰናዳች ትገኛለች /ሞያን ከ ቬሮኒካ አዳነጋር/ ፕሮግራሙ ይዘት ከምግብ አብሳዮች ጋር ያለው አዝናኝ ቆይታ ነው ፡፡
በቅርቡም በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ እንደምትል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ገልፃለች ፡፡