የዛሬ ስምንት ዓመት የተመሰረተው ሕብረት ለበጎ ወደ ስራ ገብቷል

Reading Time: < 1 minute

ህብረት ለበጎ የበጎ አድራጎት ድርጅት በለገጣፎ በአራት ሺህ ሄክታር ላይ የተቀመጠው እጅግ በጣም ዘመናዊ ሆስፒታል አሀዱ ብሎ የመጀመርያ  ምዕራፍ ግንባታ ማስጀመሪያ በሚያስገነባበት በለገጣፎ ተካሄደ።

ጓደኞቹ ጋር ተባብሮ የመሰረተው የአርቲስት ሰለሞን ቦጋለ  ከ ተመሰረተ 8 ዓመት ያስቆጠረው “ህብረት ለበጎ የበጎ”  የበጎ አድራጎት ድርጅት አርቲስቶችን ፣ ከሕጻናትን እስከ ወጣቶችን ወደ ውጭ ሐገር በመላክ ሲያሳክም ቆይቶ ነበር።ሁል ጊዜ ታማሚዎችን ውጪ ሐገር ልኮ ከማሳከም ለምን ተመሳሳይ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ የሪፈራል ሆስፒታል በሐገር ውስጥ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ሆኜ መገንባት እችላለሁ ብሎ ተነሳ ወደ ውጪ ከመሄድ እዚሁ መታከም የሚችሉበትን ሆስፒታል ማመቻቸት ነው።

ከአመታት በፊትም ይህንን የሰለሞንን ርዕይ ለማሳካት የለገጣፎ አስተዳደር ስድስት ሄክታር ማለትም 60ሺህ ካሬ ሜትር ሰጠው። ይሁንና አስተደደሩ ሁለቱን ሄክታር ለተመሳሳይ ልማት ይሆን ዘንድ ቀንሶ ዛሬ ይህ ዘመናዊ የሪፈራል ሆስፒታል በአራት ሄክታር 40 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ሆስፒታሉ ግንባታውን ለመጀመር ዛሬ የመጀመሪያውን የግንባታውን ምዕራፍ የማስጀመሪያ መርሐግብር ሰኔ 1/2015 ዓ. አካሂዶአል።

ይህ ሆስፒታል ለማስገንባት ወደ አራት ቢልየን ብር የሚጠጋ ይፈጃል ብለዋል ።

በቦታው ላይ የተገኙት የተለያዩየስራ ሀላፊዎች የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣ አርቲስቶች እንዳሉት  “የበኩላችንን አስተዋጸኦ በማድረግ ሐገራዊ ግዴታችንን እንድንወጣ እናሳስባለን “ብለዋል። 

አርቲስት በርካታ ፊልሞች ላይ ተውኗል አስደናቂ ትወና ፣ የታሪክ የሚቀመጥ ብቃት አሳይቶናል ፡፡
54590cookie-checkየዛሬ ስምንት ዓመት የተመሰረተው ሕብረት ለበጎ ወደ ስራ ገብቷል

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE