“በ1.5 ሚሊዮን ብር ቤት እንሸጣለን አላልንም” ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ

Reading Time: < 1 minute

«በ1.5 ሚሊዮን ብር ቤት እንሸጣለን አላልንም፣ በ1.5 ሚሊዮን ብር ሼር ለሚገዛ ካለምንም ተጨማሪ ክፍያ ከምንገነባው ባለ 115 ወለል ግዙፍ ህንፃ 100 ካሬ ባለ 3 መኝታ አፓርትመንት ቤት እንሰጣለን ነው ያልነው።» – የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ

ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ በከገበሬው የተቀናጀ ግብርና ማስፋፊያ መርሐግብር ላይ የታቀዱትን የኩታ ገጠም እርሻዎች ትግበራ እውን ከማድረግ አንጻር የኩባንያውን የገንዘብ አቅም ለማደርጀት የሚያስችሉ ልዩ ልዩ አጋዥ ፕሮጀክቶችን አስተዋውቆ በመንቀሳቀስ እንደሆነ ገልፆ 115 ወለል ካለው የከገበሬው ታወር በተጨማሪ ሌሎች፣ ለመኖሪያ፣ ለመዝናኛ፣ ለገበያ፣ እንዲሁም ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውሉ ግንባታዎችን ለማከናወን 60 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልገው Tower Shareholder Model (TSM) የተሰኘው የታወር ባለአክሲዮን ሥርዓት በኩታ ገጠም እርሻ ለሚከናወነው ሥራ ካፒታል ማንቀሳቀሻነት የተጀመረ ግዙፍ ፕሮጀክት መሆኑም ኩባንያው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ላይ ተብራርቷል።

Tower Shareholder Mode (TSM) የተሰኘው ፕሮጀክት እውን ሲሆን ኩባንያው ለተሰማራባቸው የግብርና መርሐግብሮች የካፒታል ምንጭ ከመሆኑም ባለፈ በየዓመቱ ከ5 እስከ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ በማስገኘት ለተቋሙ ባለአክሲዮኖች ትርፍ መክፈል የሚቻልበትን መልካም አጋጣሚ የሚፈጥር እንደሚሆን የፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ፍስሐ እሸቱ ተናግረዋል።
54510cookie-check“በ1.5 ሚሊዮን ብር ቤት እንሸጣለን አላልንም” ፐርፐዝብላክ ኢትዮጵያ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
Surafel

Surafel

Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly. Share a little biographical information to fill out your profile. This may be shown publicly.

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE