ስላለፈው ውሳኔያችሁ በጸጸት አትኑሩ!

Reading Time: < 1 minute
  • ከዚህ በፊት የወሰናችሁትን ውሳኔ አሁን ስትመለከቱት፣ “ምነው ባልወሰንኩት!” የሚያሰኝ ውሳኔ ከሆነ በዚህ ውሳኔ መሰረት እየተጸጸቱ መኖር ምንም አያዋጣም፡፡ በታትነን እንመልከተው፡፡

1. ምናልባት ትክክለኛውን ውሳኔ እያወቃችሁ የተሳሳተ ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

2. ምናልባት በወቅቱ የነበራችሁን እውቀት፣ መረጃም፣ የኑሮ አቅምም ሆነ የስሜት ሁኔታ አሰባስባችሁ በተቻለ መጠን ትክክለኛ ነው ብላችሁ ያመናችሁበትን ውሳኔ ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

3. ምናልባት በሰው ተታላችሁ ወይም በሁኔታዎች ተወዛግባችሁ ምኑንም ሳታውቁት ወስናችሁ ሊሆን ይችላል፡፡

ዛሬ ለጸጸት የዳረጋችሁ ያለፈው ውሳኔ መንስኤ ከላይ ከተዘረዘሩት መካከልም ሆነ ከዚያ ውጪ፣ ዋናው ነገር ያለፈው ውሳኔ ዛሬ ያመጣባችሁን የጸጸት ስሜት አልፋችሁ ለመሄድ ያላችሁ ቁርጠኝነት ነው፡፡

መፍትሄዎች፡-

1. በትናንትናው ውሳኔ ዛሬ፣ በዛሬ ውሳኔ ደግሞ ነገ የመጸጸት ነገር እድሜ ልክ የሚከተል እውነታ መሆኑን አትዘንጉ፡፡

2. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ማስተካከል የምትችሉትን የውሳኔውን ውጤት ለማስካከል ሞክሩ፡፡

3. በውሳኔያችሁ ስትጸጸቱ፣ እንደገና ለማስተካከል የማትችሉትን የውሳኔ ውጤት ተቀበሉት፣ ትምህርታችሁን አግኙ፣ ብሰሉበት . . . እና ወደፊት ተራመዱ፡፡

4. በውሳኔው ምክንያት ስለመጣው ችግር ከማሰላሰል ላይ ሃሳባችሁን አንሱና ስለወደፊት ራእያችሁና እቅዶቻቸው ማሰብ ጀምሩ፡፡
ፈጣሪ ጤና ይስጣችሁ!

Dr Eyob

 
54070cookie-checkስላለፈው ውሳኔያችሁ በጸጸት አትኑሩ!

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE