#ስብሐቲዝም እና ጋዜጠኝነት!Journalist should be responsible for the unseen co…

Reading Time: < 1 minute
*
#ስብሐቲዝም እና ጋዜጠኝነት!

Journalist should be responsible for the unseen corner of the society ይባላል።

ትክክለኛው እውነት ያለው ጸጥ ካለው ሥፍራ፣ ካልተነገረው ቃል ውስጥ ነው ይባላልና ያንን the unseen የሚያይ ዓይን ያለው እርሱ ጋዜጠኛ ነው። በጋዜጠኝነት ውስጥ ግን የሚፈለገው ፍጹም የሆነው እውነት (absolute truth) አይደለም። ከሚታየውና ከሚሰማው እውነት ውስጥ የትኛው ይጨበጣል? የትኛው ተጽእኖ ፈጥሯል ወይም ይፈጥራል? የትኛው ቢነገርና ቢታይ ተፈላጊ ነው የሚባለው ነገር የበለጠ ትኩረት ሊሰጠው ይችላል። ጋዜጠኝነት ያልነገሩንን መንገር፣ የሸፋፈኑትን መግለጥ ነው።

ነገሩ ምንም ያህል እውነት ቢሆንም ካልጠቀመ ይጣላል፤ ፋይዳው ሲመዘን ከቀለለ ላያስፈልግም ይችላል። ለዚህ ነው እውነት ሁሉ የማይግበሰብሰው።

#እውነትና ጊዜ!

ጋዜጠኝነቱ የሚፈልገው እውነት መሆኑን ብቻ ሳይሆን ወቅቱን የጠበቀ ቢሆን ይመረጣል። በደል ካለ፣ ስርቆሽ ካለ፣ ነውር ካለ፣ ፋይዳ ካለ፣ ከጠቀመ ወዘተ… ነገሮችን በጊዜው መዘገብ ይበጃል። በጋዜጠኝነት ተግባር ‘ነበር’ የሚል ነገር ዋጋ አይሰጠውም። ታሪክ፣ ተዝናኖታዊና መሠል ጉዳዮች ካልሆኑ በስተቀር ያለፈ ወሬ ፋይዳቢስ ነው።

#ግርማ

ለዚህ ነው በየማለዳው የማኅበረሰብን በደል፣ ቢነገር የሚጠቅምን እውነት በመፈለግና ተደራሽ በማድረግ ትልቅ አበርክቶ ያለው ጋዜጠኛ በአድማጭና ተመልካች ዘንድ ቦታ የሚኖረው – እንደ ግርማ።

“ማንን ምን እንጠይቅልዎ?” እያለ ይጠይቃል፤ መልስ ያፈላልጋል፤ እንቅጭ እንቅጯን በቻለው መጠን ያደርሳል።

#እነሆ ብርቱና መልካም ሥራን ደጋግመን እናወራለን!

ስብሐቲዝምም ጋዜጠኝነት ግድ ይለዋል።

#በዚህ ሳምንት ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሃን ጋብዘናል!

ስብሐቲዝም
#ሐሳብ፣ ንብብ፣ ውይይት!
158970cookie-check#ስብሐቲዝም እና ጋዜጠኝነት!Journalist should be responsible for the unseen co…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE