የአዲስ አመት መዳረሻ ሙዚቃዊ በቅርቡ የሚወጡ ሙዚቃ ሳምንታዊ ሙዚቃ ጉዳይ የምንጋብዛችሁ አልበም እንጠቁማችሁ…

የአዲስ አመት መዳረሻ ሙዚቃዊ
በቅርቡ የሚወጡ ሙዚቃ ሳምንታዊ ሙዚቃ ጉዳይ የምንጋብዛችሁ አልበም እንጠቁማችሁ፡፡

– ያገር ቤት- አፀደ ማርያም ያረጋል – የፋና ላምሮቷ ፈርጥ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ በዚህ ሳምንት ታደርሳለች በፕሮዲውሰር እና በግጥም እና በዜማ አቤል ሙሉጌታ የተሰራው በቅንብር ሮቤል እንዳለ በማስተሪንግ አቤል ጳውሎስ በአቤል ሙሉጌታ ዩትዮብ ቻናል ይለቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

-ሰለሞን ጋሽ አቤ- “ተመቸኸኒ” በህዝብ ዘንድ “ሰው ጠላሽ” በተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ይታወቃል አሁን በአዲስ ነጠላ ሙዚቃ መቷል በግጥም እና ዜማ ሙቁር ወልዱ በቅንብር መሀመድ ራጁ ናቸው በቅርቡ በቢኤም ኢንተርቴመንት በኩል ይለቀቃል፡፡

-ወይንሸት አየነው(ማራኪ):- “ወሎዬ ነው” የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ይዛ እየመጣች ትገኛለች ከተሰራ ረዥም ጊዜ መሆኑንም ድምፃዊቷ ጠብቁማለች በግጥም እና ዜማ ሀብታሙ ተበጄ ቅንብር መስፍን ካሳ(ጁቤ) በአሻም ፊልም ፕሮዳክሽን ሙዚቃው የተሰራ ሲሆን በቅርቡ ይለቀቃል ተብሏል፡፡

-ሙሉ ውበት-“የኩነ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ በቅርቡ ለአድማጭ ለማደረስ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች ለየት ባለ መልኩ እንደሰራችሁ ብዙ አዳዲስ ጉዳዮች ከ አሰራሩ ጀምሮ
እንደሚታይበት ገና ከወዲሁ ያስታውቃል ተብሏል፡፡

-ፒያኒስት ሳሙኤል ይርጋ እና ጓደኞቹ ከታላላቅ ድምፃዊያን ገነት ማስረሻ እና ጌቴ አንለይ ጋር ጃዝ ፣ ባህል ፣ ፍውዥን ፣ ፈንክ ፣ የተለያዩ የሙዚቃ ስልተ ምት ይቀርቡበታል ተብሏል፡፡ ነሀሴ 16/2016 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ በቦሌ ሩዋንዳ ኤንባሲ አለፍ ብሎ ከ ዋሽንግተን ሜዲካል ሴንተር 150M ገባ ብሎ ይገኛሉ ተጋብዛችኃል፡፡

-ቶሮንቶ ካናዳ ተወዳጇ ወጣት ድምጻዊ ራሄል ጌቱ እና ተወዳጁ ድምፃዊ ግርማ ተፈራ “እንቁጣጣሽ” ብለው ወደ ባህ ማዶ ተጉዘው የሙዚቃ  ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ September 7 በከተማችን በካናዳ ቶሮንቶ ተገኝተው የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ የኢትዮጲያን አዲስ አመት አስመልክቶ የማይቀር የአዲስ አመት ኮንሰርት ተብሏል።Address:-1573 Bloor st west (Dundas and bloor

-ተወዳጁ ድምፃዊ መሳይ ተፈራ ካሳ “የልቤን” የተሰኘ አልበም በርካታ አንጋፋ እና ወጣት ድምፃዊንን ያካተተ ማድረሱን አይዘነጋም አሁን ደሞ ነሃሴ 18/2016 በማሪዮት ሆቴል የአልበም ምረቃ ያደርጋል፡፡የአልበም ምረቃው ወቅት አብረውት የሚያጅቡት ድምፃዊያኖች ተዓምር ግዛው ፣ አዲስ ለገሰ፣ ግዛቸው ተሾመ ፣ ሄኖክ አበበ ፣ ሐይለ እየሱስ እሸቱ እና ሄዋን ገብረ ወልድ ናቸው ፡፡የሙዚቃ አልበሙን በራሱ መሳይ ተፈራ በተሰኘ የዩትብ ቻናል ላይ ተለቋል ገብታችሁ ሙዚቃውን መስማት ትችላላችሁ፡፡

– ድምፃዊ አህመድ ሁሴን(ማንጁስ)-“አልጣሽ” በመስከረም ወር ውስጥ ይደርሳል ብሏል፡፡ የተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎች ለአድማጭ አድርሷል በተለይ  እንደ ገና የሰራው “ደሴ ላይ ቤቷ” በህዝብ ዘንድ በይበልጥ ይታወቃል፡፡ አሁን ደሞ የበኩር አልበሙን “አልጣሽ” የተሰኘ ስያሜ ያለው ሲሆን ወደ 11 የሙዚቃ ክሮች ተካተዋል፡፡በዚህ አልበም ተወዳጅ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን በግጥም ይልማ ገብረዓብ ፣ ናትናኤል ግርማቸው ፣ መሰለ ጌታሁን ፣ ተስፋ ብርሀን በዜማው አበበ ብርሀኔ ፣ አቤል ሙሉጌታ ፣ አህመድ ተሾመ(ዲንቢ) በቅንብር አበጋዝ ክብረ ወርቅ ሽዎታ አብዛኛው ያቀናበረ ሲሆን ቀሪውን አቤል ጳውሎስ በጋራ ሰርተውታል፡፡  በማስተሪን እና ሚክስ በታላቁ አበጋዝ ክብረ ወርቅ እንደ ተሰራም ተጠቁሟል፡፡በቅርብ ቀን የሙዚቃ አድማጮች ለሁሉ ይደርሳል ተብሏል፡፡



-“One Love Music Festival”(ዋን ላቭ ሚውዚክ ፌስቲቫል በአድዋ ሙዚየም ይካሄዳል aug 30-sep 1 ለሁለት ቀን የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ጆኒ ራጋ ፣  ሔኖክ መሀሪ ፣ ራስ ጃኒ ከ ማሃሪ ብራዘርስ ባንድ ጋር ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ “back To Your origin ”

-“በMHL LOUNGE” ታላቁ የጥም እና ዜማ ደራሲ “ታምራት አበበ” የማክበር ምሽት በአንጋፋ እና በወጣት ድምፃዊያን በመድረኩ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በማቅረብ ሊወደስ ነው በመድረኩ አንተነህ ወራሽ ፣  ግርማ ተፈራ ፣ ፀጋዬ እሸቱ ፣ ጌራ ወርቅ ነቃ ጥበብ ፣ ፍቃዱ ግርማ ሲሆኑ የክብር እንግዳዎች ጋሽ ሙሐሙድ አህመድ እና ጋሽ ግርማ በየነ ናቸው፡፡ ቀኑ ማክሰኞ ነሀሴ 22/2016 ይቀርባል ተብሏል እንዳያመልጣችሁ፡፡

– አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያና  ከሮሃ ባንድ መስራቾች መካከል አንዱ የሆነው የሊድ ጊታር  ተጫዋች ስላም ስዩም ( ስላሚኖ)  በሙዚቃ  ኢንዱስትሪ ዘርፍ ላበረከተው የረዥም አመታት አገልግሎት ልዩ የክብር ተሽላሚ ሆኗል፡፡
6ኛው ዙር የጳጉሜ የሽልማት ስነስርዓት  Saturday September 7/2024 ( ጳጉሜ 2/2016  Hilton hotel 2100 E Mariposa Ave  Los Angeles California) ይካሄዳል፡፡
ጳጉሜ  የኢትዮጵያውን መዝናኛና ባህል ማዕከል
በሎስ አንጀለስ ካሊፎርኒያ እንደ ሚደረግም ተገልጿል ፡፡ እንደ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት እጅጉ ተደስቷል እንዲህ አየነቶቹን ሲያይ ፍሬአማነቱ መሆኑን ይሰማዋል እንኳን ደስ አለህ ሰምላሚኖ ባለህበት ረዥም እድሜ ከጤና ጋር ይመኝልሀል፡፡

በዚህ ሳምንት ከ ሰማናቸው ሙዚቃዊ ጉዳይ መካከል፡፡

– ድምፃዊት “ቬሮኒካ አዳነ ተካ”የመጀመርያ አልበምዋን (መጠርያዬ) የተሰኘውን የአልበም የመውጫ ቀን ያራዘመችበት ነበር ምክንያቱም ከሰሞኑ በብዙዎች ዘንድ መነጋገርያ የሆነው ህፃን ሄቨን ላይ የደረሰው እጅግ አሰቃቂ ድርጊት ምክንያት በማድረግ አልበሙ በሚቀጥለው ሳምንት በ23/2016 ዓ.ም እንደምታወጣው ገልፃለች፡፡በመግለጫውም ለየኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት በጋዜጣዊ በመግለጫው ለጠየቃት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሰታናለች ከጠየቅነው ጥያቄ መካከል በአልበሙ ውስጥ እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ አለ ወይ? ምላሽዋም ሁለት ስራዎች አሉ አንዱ ለ አባቴ አንድ ደሞ በፍቅር ህይወቴ የሚያጠነጥን ያጋጠመኝን ነው የዘፈንኩት ብላለች፡፡

-“ፈታ ሾው” ከአምስት አመት በኃላ ወደ ቴሌቪዥን መስኮት ተመልሷል ስያሜውን “ፈታ በአባይ” በማለት በአባይ ቲቪ በወርሀ መስከረም አንድ በአዲሱ አመት የመጀመርያ የፕሮግራም ስርጭቱን ያቀርባል ከዛ በፊት በነሀሴ 27/2016 አመተምህረት “ፈታ ሚውዚክ አዋርድ” በኢትዮጲያ ቢሄራዊ ትያትር ከ1200 በላይ ታዳሚያን ባሉበት ዝግጅቱ ይቀርባል ተብሏል፡፡ በመድረኩም ምንም አይነት መስፈርት የሌለው ሲሆን ለድምፃዊያን እውቅና እና ምስጋና የሚደረግ የሽልማት መርሀ ግብር ነው “ጥበብ አትዳኝም”፡፡ለየኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ ዝግጅት ክፍል፡፡ እንደገለፁልን መስፈርት የለውም ግን የእውቅና እና የምስጋና የሽልማት መርሀ ግርብር ነው ብለውናል፡፡

-ተወዳጅዋ ድምፃዊት ቤቴልሄም ሸርፈዲን የአፍሪ ክለብ ኦቨርሲስ ብራንድ አምባሳደር ሆነችበት በዚህ ሳምንት የሰማናቸው ጉዳዮች አንዱ ነበር፡፡አፍሪ ክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙን ነሃሴ 08/2016 ዓ.ም በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተከናወነ ፕሮግራም ላይ ታውቋል፡፡አፍሪ ክለብ ኦቨርሲስ ኮንሰልተንሲ ሼር ካምፓኒ የሚሰራቸውን ስራዎች ድምፃዊ ቤተልሔም ሸረፈዲን እንድታሰተዋወቅለት በወቅቱ የፊርማ ስምምነትም አድርገዋል ።
151240cookie-checkየአዲስ አመት መዳረሻ ሙዚቃዊ በቅርቡ የሚወጡ ሙዚቃ ሳምንታዊ ሙዚቃ ጉዳይ የምንጋብዛችሁ አልበም እንጠቁማችሁ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE