-ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛ ምዕራፍ በአስራ ሶስተኛው ሳምንት ፍፃሜውን ያገኘበት ነበር ፡፡ በሶስት ወራት ሙ…

Reading Time: < 1 minute
-ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛ ምዕራፍ በአስራ ሶስተኛው ሳምንት ፍፃሜውን ያገኘበት ነበር ፡፡ በሶስት ወራት ሙሉ አስራ ስድስት ተወዳዳሪዎችን ሲያፋልም የነበረው በስተመጨረሻ አራት ምርጦችን ለፍፃሜ አብቅቷል፡፡ በዚህም መሰረት ጴጥሮስ ማስረሻ ፣ ናሆም ነጋሽ ፣ ሱራፌል ደረጄ እና አብርሀም ማርልኝ አንድ ሚልየን ብሩን በየደረጃቸው ልክ ተከፋፍለዋል፡፡ በቀጣይም የአምስተኛ የአሸናፍዎች አሸናፊ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል፡፡

-ማርዳ ሳውንድ ወደ ሃያ ምስት የሚጠጉ የሳውንድ ተማሪዎች  እሁድ ለት በRO-V ሆቴል በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል አመስርቋል፡፡ በቦታው የተማሪ ቤተሰቦች እና ጓደኛ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ረ/ፕ አክሊሉ ዘውዴ ፣ መምህርት የሙዚቃ ባለሞያ የሹምነሽ ታዬ የአክሱማይት ባንድ ዳዊት ፅጌን ጨምሮ ሌሎች አንጋፍ ሰዎች ተገኝተዋል ፡፡ የሙዚቃ ባለሞያ እና መምህር ክሩክ አሰፋ እንገለፁት” ማርዳ ሳውንድን ሲቋቋም በተለያዩ ከተሞች ያለውን የሳውንድን/ የድምፅን ችግር እንቀርፋለን ብለን ነው” ፡፡ “ሞያው በፍላጎት በፍቅር የሚሰራ ሲሆን በትምህርት ቤት ውስጥ የተለያየ ሞያ ያላቸው ግን የድምፅን ሁኔታ ለማጥናት በፍላጎት የመጡ ናቸው ብሏል፡፡ ማርዳ ሳውንድ አራት ወራት የትምህርት ጊዜ ያለው ሲሆን በሳምንት ሁለት ሲሰጥ ማርዳ በሳምንት ሁለት ክፍል ከፍሎ ተማሪዎችንን እያሰለጠነ ይገኛል፡፡



*በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ አልበም፡፡

63 የአልበም ጥቆማችን በቮካል ሪከርድስ በኩል የታተመው የተወዳጁ ድምፃዊ ዳና አድማሱ “ዘበናይ” አልበምን እንጠቁማችሁ እጅግ ከሚወደዱ አልበም ተርታ የሚሰለፍ እና በቅንብር በዜማ በግጥም እጅግ የተወጣለት ግና ግን በስፋት ሲሰማ አንመለከትም “ዘበናይ” አልበም አንጋፋዎች የሙዚቃ ከያኒያን የሰሩት ሲሆን በቅንብሩ ስድስቱን ያህል ሚካኤል ሀይሉ (ሚኪ ጃኖ) ሲሰራው በአንድ ሙዚቃ “ልኬን አየሁት” በተሰኘው ዜማ ሰርቷል፡፡ ቀሪውን በታላቁ ኤልያስ መልካ የተቀናበሩ ናቸው አምስት የሆኑትን ሙዚቃዎች ላይ በግጥም ሲሳተፍ በዜማ ደግሞ ሁለት ስራዎችን ሰርቷል፡፡በውስጡ 13 ክሮች ያሉት ሲሆን ንገሪኝ ኢትዮጲያ ፣ሰሚ ላላገኝ ፣ ከፍቶሽ እንዳላይ ፣ ወደ ኃላ ፣አባይ ፣ጴጥሮስ የመሳሰሉት ሲገኙ በፊውቸር “አብተ ሚካኤል ደምሴ” አጅበው ተጫውተዋል፡፡ ተወዳጁ ሰው የዚህ አልበም ሙሉ ለሙሉ ማስተሪንግ የሰራው ታላቁ አበጋዝ ክብረ ወርቅ “ቮጋል ሪከርድስ አሳትሞታል”፡፡ በዚህ ሳምንት እንድታጃምጡ መረጥን፡፡

አዘጋጅ እና አቅራቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ሐሳብ አስተያየት @temuela አድርሱኝ በተጨማሪ yenevibe.com ገብታችሁ ጎብኙ እናመሰግናለን፡፡
151210cookie-check-ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛ ምዕራፍ በአስራ ሶስተኛው ሳምንት ፍፃሜውን ያገኘበት ነበር ፡፡ በሶስት ወራት ሙ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE