በድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲውስ የተደረገው ”መጠርያዬ” አልበም በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል፡፡የድምጻዊት …

Reading Time: < 1 minute
በድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲውስ የተደረገው ”መጠርያዬ” አልበም በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል፡፡

የድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ መጠሪያዬ የተሰኘው የመጀመሪያ አልበም በቀጣይ ሳምንት
23/2016 አመተ እንደሚለቀቅ በዛሬው እለት በማሪዮት ሆቴል በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።



ይህ መጠሪያዬ የተሰኘው አልበም በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የኪነጥበብ ከያኒያን ተሳትፈዋል፡፡በግጥም እና ዜማ አቤል ሙሉጌታ 4 ሙዚቃዎችን ፤አቡዲ ያሲን 7 ያህል ሙዚቃዎችእና ሱራፌል የሺጥላ አንድ ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ ተሳትፈዋል።

በሙዚቃ ቅንብር በኩል ታምሩ አማረ ፣አዲስ ፍቃዱ ፣አብርሃም ኪዳኔ ሮቤል እንዳለ በሚክሲንግ ፣ ማስተሪንግ ሰለሞን ኃ/ማሪያም ሰርተውታል፡፡

አልበሙ ላይ ስለ ፍቅር ፣ ስለ ሀገር ፣ ሰለ ሰላም ፣ ስለ ተስፋእና የመሳሰሉት የተካተቱበት ሲሆን ከራስዋ ጋር እውነተኛ ታሪክ ያጠነጠነ እና ስለ አባቷ አርቲስት አዳነ ተካ ሙዚቃ እንደ ሰራችም ገልጳለች፡፡

መጠሪያዬ አልበም 12 ሙዚቃዎች ያሉት ሲሆን አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 3 ዓመት ፈጅቷል አልበሙ ላይ ሁለት የሙዚቃ ቪዲዮዎች በአሜሪካ አትላንታ ተሰርተዋል፡፡

ይህ አልበም አጠቃላይ ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የወጣበት ሲሆን የአልበሙ ሙሉ በሙሉ ወጪ በድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲዩስ የተደረገ ሲሆን አልበሙን በማኔጅመንት ኪነት ኢንተርቴይመንት ማኔጅ አደርጎቷል፡፡

ይህ መጠሪያዬ አልበም ሰሶት አመት የተለፋበት ብዙ የተደከመበት እና የተለፋት አልበም ስለፍቅር ስለሰላም ስለሀገር ስለተስፋ እና ስለምስጋና የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ተዷሷል ።

ይህ አልበም ዞጃክ ወርልድ ዋይድ የተስኘ አለም አቀፍ የሙዚቃ ካምፓኒ ጋር በ160,000 ዶላር በመላው አለም ለማከፋፈል ከአርቲስቷ ጋር ተስማምተዋል።

በኢትዮጵያ ብር አስራ ሰባት ሚሊየን ብር በላይ ሲሆን ይህም ክፍያ በኢትዮጵያ አልበም ክፍያ ታሪክ ትልቁ ክፍያ እንደሚያደርገው በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።

ዞዳክ ወርልድ ዋይድ መቀመጫውን በአሜሪካ ፍሎሪዳ ያደረገ ሲሆን በተለያዩ አለማት ማለትም ሜክሲኮ ፣ ኢንዶኒዢያ ፣ ጀማይካ እና ኬንያ ቅርንጫፎች ያሉት ሲሆን ይህ ካምፓኒ የኢትዮጵያን አልበም ሲገዛ የመጀመሪያው ነው፡፡

መጠሪያዬ የተሰኘው አልበም የፊታችን ነሀሴ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በቬሮኒካ አዳነ ዩቲዩብ ቻናል ፣ በካሴት የቴሌግራም ቻናል እና በሁሉም አለም አቀፍ የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል፡፡

ድምጻዊት ቬሮኒካ አዳነ ሙዚቃው ነሐሴ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይለቀቅ የነበረ ቢሆንም በህጻን “ሔቨን” ላይ የደረሰውን ጥቃት ምክንያት በማድረግ አንድ ሳምንት መራዘሙን ድምጿዊቷ ገልጻለች።

@biggrs yenevibe.com
151070cookie-checkበድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ ፕሮዲውስ የተደረገው ”መጠርያዬ” አልበም በቀጣይ ሳምንት ይለቀቃል፡፡የድምጻዊት …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE