ፈታ ሾው በአዳዲስ ጉዳዮች ፈታ ሊያረገን ተመልሷል፡፡https://telegra.ph/file/8289eb55df9…

ፈታ ሾው በአዳዲስ ጉዳዮች ፈታ ሊያረገን ተመልሷል፡፡



ፈታ ሾው ከአምስት አመት ቆይታ በኋላ “ፈታ በአባይ” በሚል ስያሜ ተመልሷል

ፈታ ሾዎ ከአምስት አመት ቆይታ በኋላ በአባይ ቴሌቪዥን በቀጣይ አዲስ አመት መስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም “ፈታ በአባይ ” በሚል ስያሜ ዳግም መመለሱን እና የፈታ ሙዚቃ አዋርድ የፊታችን ነሀሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ከ1200 በላይ ታዳሚዎች በሚገኙበት የሸልማት መርሐግብር እንደሚያዘጋጅ አሳወቀ።

የፈታ ሾዎ ኘሮግራም አቅራቢ እና አዘጋጅ አርቲስት ጌታነህ ፀሐዬ የፈታ ሙዚቃ አዋርድ እና የቴሌቪዥን ኘሮግራሙ ዳግም መመለሱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንገለጹት የፈታ ሾው ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሳምንታዊ ተከታታይ የቴሌቪዥን መዝናኛ ዝግጅት ሲሆን ዝግጅቱ ባለው አሳታፊ ይዘት እንዲሁም አሰመሰሎ በመዝፈን አዝናኝ ውድድሮቹ በተወዳጅነቱ ላለፉት አምሰት አመታት መቆየቱ ገልጸው ዳግም ከአምስት አመት በኋላ በአባይ ቴሌቪዥን በቀጣይ አዲስ አመት “ፈታ በአባይ ” በሚል ስያሜ ዳግም መመለሱን ገልጸዋል።

ከቴሌቪዥን ኘሮግራሙ ጅማሮ ባሻገር ድምጻዊያንን እውቅና የሚያሰጥ ልዩ ሽልማት መርሐግብር በያዝነው ወር መጨረሻ መዘጋጀቱን አርቲስት ጌታነህ ፀሐዬ ገልጸዋል።

“ጥበብ አትዳኝም ” በሚል ሐሳብ በተዘጋጀው የፈታ ሙዚቃ አዋርድ ላይ የፈታ ሙዚቃ አዋርድ መነሻ ፅንሰ ሀሳቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ያለምንም ቀጥተኛ ውድድር ላበረከቱት አስተዋጾ ለሰራቸው እውቅናን የሚያገኙበት ሁሉን ያካተተ እና አሳታፊ መድረክ ለመፍጠር መታሰቡን እና ዝግጅቱ የኢትዮጵያን ባህል ፤ ባህላዊ እና ዘመናዊ ገፅታዎች ለማንፀባረቅ በትኩረት የታቀደ የሽልማት ትእይንት ብቻ ሳይሆን የባህል አከባበርም ጭምር መሆኑን ገልጸዋል።

የፈታ ሙዚቃ አዋርድ በ2016 ዓም የኢትዮጵያውያን አርቲሰቶችን ሰኬት ከማክበር ባለፈ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን እንደያዘ የማክበር እና የመጠበቅን ስርዓት በማስቀጠል የሙዚቃውን ብሎም ሙዚቀኛውን ማስከበር ነው።
150740cookie-checkፈታ ሾው በአዳዲስ ጉዳዮች ፈታ ሊያረገን ተመልሷል፡፡https://telegra.ph/file/8289eb55df9…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE