
ኦማር ዘይት የክብር ስፖንሰር የሆነበት «ስለ ሰላም ባዛር» ሊካሄድ እንደሆነ ተገለፀ።
ኦማር ዘይት የክብር ስፖንሰር የሆነበት «ስለ ሰላም ባዛር»ሊካሄድ እንደሆነ አዘጋጁ ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ ዛሬ ነሐሴ 3/2016 ዓ.ም በሚኒሊየም አዳራሽ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል ።
ባሮክ ኢቨንት ኦርጋናይዘር አ.ማ በሀገራችን የተለያዩ ሁነቶችን (ኤቨንቶችን) በማዘጋጀት ሕጋዊ እውቅና ያለው ተቋም ነው፡፡ ሥራውን በይፋ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ
በተለያዩ አመታዊ በዓላት እና ሀገር አቀፍ ቀናትን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ኢግዚቢሽን እና ባዛሮችን እንዲሁም የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት ተመራጭ ለመሆን እና ተቀባይነት ያለው ድርጅት ነው፡፡
ከዚሁም ጋር በተያያዘ የ2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ አስመጪዎች እና አምራቾች ከሸማች ሕብረተሰቡ ክፍል ጋር እየተዝናና የሚገበያይበትን የአዲስ አመት ባዛር እና ኤክስፖ ከነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አመት ዋዜማ በደማቅ ሁኔታ በታላቁ በሚሊኒየም አዳራሽ ያካሂዳል፡፡
በዚህም የአዲስ አመት ባዛር እና ኤክስፖ ሸማቹ የህብረተሰብ ክፍል በአልን ምክንያት አድርጎ ከሚገጥመው የዋጋ ንረት በተመጣጣኝ እና በቅናሽ ዋጋ ከራሱ ከአምራቹና ከአስመጪው የሚገበያይበት ሲሆን አምራች ከሸማቹ ከፍተኛ የገበያ ሽያጭ በማግኘት ተጠቃሚ የሚሆንበት ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የተለያዩ የመዝናኛ የምግብ እና የመጠጥ ፕሮግራሞች የሚገኙበት ባዛር እና ኤክስፖ ነው፡፡ይህ ልዩና ደማቅ የሆነ ባዛር እና ኤክስፖ የፊታችን ነሃሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ሚኒስትሮች፣ ባለሀብቶች፣የሚዲያ ባለሙያ እና ቲዋቂ ሰዎች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት በይፋ ይከፈታል፡፡
በዝግጅቱም ላይ አልባሳት፣የስጦታ እቃዎች፣ አቅራቢና አስመጪ፣ የምግብና መጠጥ ሻጮች የቤት ዕቃ አስመጪና አቅራቢዎች በአጠቃላይ ከበዓል ጋር ተያይዞ የሚቀርበው ማንኛውም ግብዓቶች በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርብበት ሲሆን በአጠቃላይ ከ2,000 በላይ አስመጪና ሻጮች የሚሳተፉበት ሲሆን በዚህም ዝግጅት በቀን ከሰባት ሺህ (7,000) እስከ
አስር ሺህ (10,000) ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይታሰባል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በየቀኑ ለሀገራችን የሚገኙ ባህላዊ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ባለሙያዎች በየቀኑ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በተወዳጅ ባንዶቻቸው በመታጀብ
ያቀርባሉ፡፡
የዚህን ዝግጅት በክብር እስፖንሰር በማድረግ የዘወትር አጋራችን የሆኑትኦማር ዘይት፣ እናት ባንክ BJI ኢትዮጵያ(በስንቅ ማልት) እንዲሁም ቡና ባንክ እና ሌሎች አጋሮች ይገኙበታል ።
👉የባዛሩ ሰአት ከጠዋቱ 3:00 ሰአት- ምሽቱ 3:00 ሰአት
👉የመግቢያ ዋጋ እንደ እለቱ100-150 ብር
በባዛሩ የሚገኙ ሙዚቀኞች
👉ዚጊ ዛጋ
👉አህመድ ተሾመ(ዲንቢ)
👉ሚኪያስ ንጉሴ
👉ሳሚ በየነ
👉ሃይማኖት ግርማ
👉ጌዲዮን ዳንኤል
👉ኤልያስ ተባባልና ሌሎችም ሙዚቀኞች ወደ 35 የሚጠጉ ስመ -ጥር ድምፃዊያን
ለበለጠ መረጃ
👉0911247800
👉0911430310
👉0911221753
ይደውሉ፡፡ Abreham GizaAbreham Gizaw