አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ሙዚቃዊ ጉዳዩች እንደ ገና በየሳምንቱ አልበም የምታዳምጡትን እንጠቁማችሁ፡፡
-ልዑል ሀይሉ-“እስኪ አሙቁላት” የተሰኘ ሙዚቃ ከአልበሙ ስር /እሳቱ ሰዓት/ያለ በቪዲዮ አልብሶ አርብ እለት በናሆም ሪከድስ በኩል ያደርሰናል ግጥም ፣ ዜማ ፣ ቅንብር ፣ሚክሲትግ፣ማስተሪንግ በኤልያስ መልካ ተሰርቷል፡፡ሁለተኛ አልበሙንም በማገባደድ ላይም ይገኛል፡፡
-እመቤት ጌትነት-”አሻሜ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ይዛ ስትመጣ ግጥም እና ዜማ ምስክር ምንዳዬ (ባራቼ)ቅንብር ሳሙኤልዳንኤል(ሳምዋካ)በዳንስ ያገዙትጋሞ የዳንስ ቡድን አግዘዋታል ሐሙስ ምሽት በ ናሆም ሪከድስበኩል ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
-ተወዳጅዋ ድምፃዊ ራሄል ጌቱ ባህር ማዶ ተጉዛ ካናዳ የሙዚቃ ስራዎቿን ለማቅረብ እየተዘጋጀች ትገኛለች እንደ እናዎቹ አባል የሆነችድምፃዊቷ የተለያዩ ነጠላ ዜማ ሲኖራት ሁለት አልበም ወረት እና እቴሜቴ ሲሆን ለአድማጮች ለመጨረሻ ጊዜ ያደረሰችሁ “ዋርካ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ በሰዋሰው በኩል አድርሳ ነበር፡፡
-ዘ አማን ግርማይ – ”ኮቱሜ” ስድስት መቶ ሺህ ብር የወጣበት ነጠላ ሙዚቃ መላው ዓለም የምትገኙ የሙዚቃ አፍቃሪዎችበሙሉ ከዚህ በፊት በተለያዩ የትግርኛ ሰራዎቹ በሕዝብ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ዘ-ኣማን ግርማይ አሁን ደሞ ብዙ የተደከመበት ከ 40 በላይ የጥበብ ባለሞያዎችን ያሳተፈ ከ 7ወር በላይ ግዜን የወሰደ እና ከ600,000 ብር በላይ ወጪ የተደረገበት #ኮቱሜ_የተሰኘ በአይነቱ ለየት ያለ የሙዚቃ ክልፕ በቅርብ ቀን ወደ እናንተ ሊያደርስ ዝግጅቱን ጨርሷል።ኮቱ ሜ ዘ-ኣማን ግርማይ በቅርቡ ይወጣል ተብሏል፡፡
– ተወዳጁ ድምፃዊ ፍቃዱ ትዛዙ በተለያዩ ነጠላ ሙዚቃዎች ይታወቃል ተዛዘብን ፣ ሲያዴ በተሰኙ የራሱ ነጠላ ሙዚቃዎች ከዛም ባለፈ የቀድሞ ድምፃዊ ተፈራ ነጋሽ ሁሉት ያህል ሰርቶ ነበር ምነው ቀዘቀዘ እና አብሮ አደጌ በራሱ ከለር ለህዝብ አድርሷል፡፡የተፈራ ነጋሽ በርከት ካሉ ስራዎች ውስጥ የተመረጡ አስራ ሶስት የሙዚቃ ክርበተጨማሪም አንድ የክሊፕ ስራ እንደ ጨረሰ ገልጿል፡፡ በአልበሙ ግጥም ዜማ ላይ በፊቶች የተሳተፉበት ይልማ ገብርዓብ ፣ የኔው አካሉ ፣ ተመስገን ተካ ፣ ሞገስ ተካ የመሳሰሉንት ሲኖሩ በማስተሪንጉ ተወዳጁ አበጋዝ ክብረወቅ ሽዎታ እንዳለቀ ገልጿል፡፡ በቅርብ ቀንም ለአድማጮች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ድምፃዊውም ፍቃዱ ትዛዙ አክሎም የቀድሞ ድምፃዊ ተፈራ ነጋሽ መብቱን እንደ ሰጠው እና አልበሙን በጥንቃቄ እንደሰራው ገልጿል፡፡
-ራፐር ፖንፋሎን ”beats and vibes fest’‘ በሐምሌ 27/2016 ዓም በthe venue warehouse የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል የመግቢያ ትኬት መደበኛ 400 በር ላይ 500 ቪአይፒ 800 ብር መሆኑንም ተገልጿል፡፡
– ዳግም አዳነ”በቃ” ሁለተኛ አልበሙን ለቋል በውስጡ አስራ ሶስት ክር ሲኖሩት የቤት ልጅ ፣ ወይ ነዶ ፣ ፍቅር ይሻላል የመሳሰሉት ይገኛሉ በዳግም አዳነ ዩትዮብ ቻናል ገብታችሁ ሙዚቃውን አጣጥሙ አበረታቱት፡፡
*በዚህ ሳምንት ከተነሱት ሙዚቃዊ ጉዳይ እንመልከት::
-ድምፃዊት ብስራት ኃ/ማርያም (ቤሪ)ከረጅም ጊዜ በኃላ የሙዚቃ ስራዎቿን አቅርባለች “በቃና ዌርሐውስ” በተዘጋጀው የሙዚቃ ዝግጅት ባሳለፍነው ሐምሌ 13/2016 ማቅረቧ ይታወሳል፡፡ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈላት አልበም ማውጣትዋ አይዘነጋም ”ከምን ነፃ ልውጣ” አልበም የዚህ አልበም ሰሪው ሙሉ ለሙሉ በታላቁ ኤልያስ መልካ የተሰራ ነው፡፡
-አነጋጋሪው ”የኦሎፒክ ኮንሰርት” ጉዳይ አትሌቶቹን ለመደገፍ ሲባል የታሰበው ኮንሰርት ሳይደረግ ቀረ፡፡ በርካታ ድምፃዊያንን ይዞ በመስቀል አደባባይ ሊቀርብ የነበረው ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙን ታውቋል ሐምሌ 6/2016 ይቀርባል ቢባልም እንደ ገና ወደ ሐምሌ 13/2016 እንደ ተራዘመ ተገልፆ ነበር ኮንሰርቱ ይደርጋል ቢባልይ ሳይደረግ ቀርቷል፡፡ይህ ኮንሰርት በሌቭል ዋን እና በላላ ፕሮዳክሽን በመተባበር የቀረበ ነበር፡፡
-ድምፃዊት መና ወረደ ከ ያምሉ ሞላ ጋር በጋራ በመሆን አምስት ሙዚቃዎች ወይም ep አልበም አድርሰውናል ተው ተው ፣ ኤክትሪክ ፣ ማዕዘን ፣ አንድ ለሞን ፣ በግጥም በዜማ እና በቅንብር ተወዳጁ ያልተነገረለት አቀናባሪ ያምሉ ሞላ ነው በማሲንቆ አዲስ አለማየሁ/አዲንቆ/ ፣ ከበሮ አገረሰላም ሻፊ ፣ ፋሲካ ሐይሉ በክራር ሲሳተፉ ድምፃዊት መናወረደን ያገዝዋት አማኑኤል ሙሴ ፣ ናርዶስ ተሻለ ይገኙበታል፡፡ያምሉ ሙላ ዩትዮብ ቻናል በመግባት ሙዚቃዎቹን አጣጥሙ፡፡
– የዚህ ሳምንት ይበልጥ አነጋጋሪው”የጉማ አዋርድ ሽልማት በምን አለሽ ተራ” በመገኘቱ በርካቶች በማህበራዊ ገፃቸው ስለ እዚህ ጉዳይ የራሳቸውን ሐሳብ እና ይንን የሚገልፀውን ፎቶ በመጠቀም ሲያዘዋውሩት ነበር፡፡ ይንን በማየት የለዛ ሽልማት አዘጋጁ ብርሀኑ ድጋፎ በዚህ ጉዳይ ምላሽ ሰቷል ከሀገር ወጣ ብሎ እውነታን በመከተል የተለያዩ ምሳሌዎችን በመጥቀስ ስለ ኦስካር መሰረቅ አብራርቶ የሰሞንኛ ጉዳይ ጉማ አዋርድ በምን አለሽ ተራ ተገኘ ተብሎ የተወራውን ሁሉ ብዥታዎች አጥርቶ ገልጿል፡፡ ይህ አጋጣሚ የተፈጠረው ቤታቸው ለልማት ተብሎ ሲፈርስ በዛ ወቅት የተፈጠ አጋጣሚ አስታውሶ ሽልማቱ ተሸላሚውን ሸላሚውም ተገኝቷል ሲል ስለ ሸላሚው እና ስለ ተሸላሚው ሰፊ ማብራርያ በመስጠት የሰሞንን አነጋጋሪውን ወሬ ገልጿል፡፡
* በየኔ ቫይብ በዚህ ሳምንት የመረጥንላችሁ አልበም፡፡
የተወዳጁን ሙዚቀኛ ሐይልዬ ታደሰ”ሁሌ ሁሌ” የተሰኘውን የሙዚቃ አልበም ነው በውልጡ 11 ክር በውልጡ ሊኖር ሁሌ ሁሌ ፣ መጥቻለሁ ፣ ያበደ ማን ነው ፣ እንዴት ብዬ ፣ ሲኖር ፣ እመኛለሁ ፣ እንሷን ብቻ እና የመሳሰሉት በውስጡ ሲኖር ታላላቅ ከያኒያን ተሳትፈል በግጥም በዜማ ሳምሶን ማሞ ፣ ቴዎድሮስ ካላሁን ፣ አለማየሁ ደመቀ፣ ሞገስ ተካ ፣ ታመነ መኮንን ፣ ይልማ ገብረዓብ ፣ ጎሳዬ ተስፋዬ ሰርተውታል በቅንብሩ ፣ ሚክሲንግ ፣ በማስተሪንግ ኤልያስ መልካ በኪቦርድ እና ሊድ ጊታር ኤልያስ መልካ ቤዝ ዳዊት አበራ በሳክስፎን ዮሐንስ አክሊሉ /ጆኚ) ናቸው፡፡ከዚህ የሙዚቃ አልበም ውስጥ ድምፃዊ ሐይልዬ ታደሰ እንደ ገለፀው በእናቱ ለወ/ሮ አልማዝ በየነ ”መጥቻለሁ” የተሰኘችዋን ሙዚቃ እናቴ ማልታወሻ መታሰብያ ይሁን ብሏል፡፡የማይረሳ በልባችን ያለ አልበም ስለ ሰጣችሁን የኔ ቫይብ ምን ጊዜም ያመሰግናችኃል፡፡
አዘጋጅ እና አቅራቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
yenevibe.com ይጎብኙን