ይድረስ ለድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ

ይህ አልበም እንደ ተሰራው ልክ ያልተደመጠ ለድምፃዊት ሄዋን ገብረወልድ ማስተርፒስ የሆነ አልበም፡፡ እኔ በግሌ ይህ አልበም ከጥግ እስከ ጥግ ጥንቅቅ ተደርጎ የተሰራ አልበም ነው፡፡
ሄዋን ገብረወልድ “ሄዋን” አልበም በስሟ የሰየመችሁ የብኩር አልበሟን ሐሙስ ግንቦት 25/2014 ነበር የተለቀቀው በዚህ አልበምዋ በውስጡ 11 ክሮች የያዘ ሲሆን ምን ይጠቅምሀል ፣ ሄዋን ፣ እንደኔ እንደኔ ፣ ትፈለጋለህ ፣ ሼሙና ፣ አለም ፣ አስብበት እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ በዛ ያሉ ስልተ ምቶች ሲኖሩት ሂፕሆፕ ፣ አፍሮ ቢት ፣ ጉራጌ ቢት ፣ ውሎ ቢት ፣ ዋልዝ ፣ ሬጌ-ሮክ ፣ አር ኤንቢ እና የመሳሰሉት ተሰርተዋል፡፡ የተለያዩ ስሜቶች በአልበሙ ተንፀባርቀዋል ፍቅርን ፣ ታሪክን ፣ የውስጥ ህመምን ፣ መወደድን ፣ አብሮነትን ፣ መተሳሰብን ፣ ትውስታን ፣ ትዝታ ፣እነዚህን እና የመሳሰሉት ተንፀባርቀዋል፡፡
#ምን ይጠቅምሀል…
“ሸርተት አለ ጎኔም ከዳው
ጎዳኝ መምሰል እንዳልተጎዳው
ሸፋፈንኩት እየተቀጣው
አንተን ላተርፍ ብዬ እኔን አጣው”፡፡
የራስን ህመም ደብቆ ለሌላው ድህሎት መመኘት በጉዳት ውስጥ ሌላን የማፍቀር ጥበብ ይገለጣል፡፡ ግጥም ናትናኤል ግርማቸው ዜማ አንተነህ ወራሽ ቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) የሙዚቃ ስልቱ ዋልዝ የተረጋጋ ቀልብን ሰብሰብ የሚያደርግ ነው፡፡
#ሔዋን…
“ያጣሁት ያን ጎብል የገፋኝ ወጣቱ
ከፍቶ አይደለም በኔ ነው በልጅነቱ
ዞር በይ ዞር በይ ያለኝ የገፋኝ ከቤቱ
ማደጉን ፈርቶ ነው ወዶ ልጅነቱ”
ይህ የሙዚቃ ክር ሁለት ነገሮችን ተሸክሟል የመጀመርያው በአልበም ደረጃ የኔ ያለችውን በስሟ ሰይማ መምጣትዋ ነው ፡፡ ሁለተኛው 1830 ዓ.ም በአፄ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት በጉራጌ ብሔረሰብ ትልቅ ገድል የፈፀመችሁ “ቃቄ ውርዶት” በሴቶችን ላይ የሚፈፀመው ጭቆና እና ግፍ ነፃ ያወጣች ድንቅ ሴት እሷን ታሳቢ ተደርጎ የተሰራ እንደሆነም ድምፃዊቷ ገልፃለች፡፡ የሙዚቃው ገጣሚ ዮሐና አሸናፊ ዜማ ሄዋን ገብረ ወልድ ቅንብር ዲጄ ሚላ በጉራጌ ቢት ከሽኖ ሰርቶታል፡፡
#ያምራል #ልጁ
ስመኝ ኖሬ እንኳን ስመኝ
በዓመት በዓል አገጣጥመኝ
ይህ ሙዚቃ ክር አንድን በህላዊ ስሜትን ይዞ አመት በአልን የሚያስታው ትውስታ ይዞ የመጣ ሲሆን የድምፃዊትን አስናቀች ወርቁን የሚያስታውስ የሙዚቃ ቅንብር አሰምታናለች የሙዚቃ መግቢያ እንደ እየሩስአሌም የተሰኘ የሙዚቃ ቅንብር ቅንጭቡን ወስደዋል፡፡ አንድም ታሪክን ለመግለፅ ባህላዊ የሙዚቃ ስልት ማስተዋወቅን የያዘ ነው፡፡ ግጥም ወንደሰን ይሁብ ዜማ አንተነህ ወራሽ ቅንብር ዲጄ ሚላ፡፡
በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን ታሪካዊ አልበም ላይ ተሳትፈዋል፡፡ አብዛኛውን ግጥም በናትናኤል ግርማቸው የተሰሩ ሲሆን በቅንብሩ በኩል ዲጄ ሚላ አብዛውን ሰርቷል፡፡ ለመጥቀስ ያህል በቅንብሩ ዲጄ ሚላ ፣አቤል ጳውሎስ ፣ ሚካኤል ኃይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ ተቀባ እና ታምሩ አማረ (ቶሚ) ተሳትፈዋል፡፡ በግጥም ዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ ዮሐና ፣ ምረት አብደስታ ፣ ሄዋን ገብረወልድ ፣ አንተነህ ወራሽ ፣ ወንደሰን ይሁብ ፣ ይልማ ገብረዓብ ፣ በማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ ናቸው፡፡
አዘጋጅ እና አቅራቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ