አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እና ሙዚቃዊ ክስተት በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንጠቁማችሁ፡፡https://t…

Reading Time: 2 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እና ሙዚቃዊ ክስተት በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንጠቁማችሁ፡፡

– ሐመልማል አባተ- “ራያ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ከረጅም ጊዜ በኃላ ለማውጣት ተዘጋጅታለች ይህንን ሙዚቃ በግጥም በዜማ የተሳተፈው ቢንያም ረዳኢ(ሀ ግዕዝ) በቅንብር ፣ በሚክሲንግ ፣በማስተሪንግ አሌክስ ይለፍ ሰርቶታል፡፡ በቅርብ ቀን ለአድማጮች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡– አቡሽ ዘለቀ- “ሀገር እና ሰው” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ከረጅም ጊዜያት ይዞ እየመጣ ይገኛል በግጥም በዜማ ድምፃዊው አቡሽ ዘለቀ ሲሰራው በቅንብር ፣በድምፅ ፣ ሚክስ ፣ ማስተሪንግ ቤካ ግራፊክስ እና ኢትዮ ማጂክ ፒክቸር ሪፍ ሪከርድ ናቸው፡፡አርብ እለት በሁሉም የሙዚቃ መተግበርያ ይለቀቃል፡፡– ቃል ኪዳን- “ሎጋው” የተሰኘ ነጠላ ዜማ በቅርብ ታደርሰናለች የዚህን ሙዚቃ ግጥም እና ዜማ ድምፃዊ እሱባለሁ ይታየው( የሺ) ሲሆን በቅንብሩ ታምሩ አማረ( ቶሚ) ሰርተውታል፡፡-ቴዎድሮስ አብርሀም- “የሎሚ ሽታ” የተሰኘ አዲስ ነጠላ ሙዚቃ ይዞ እየመጣ ይገኛል፡፡ግጥም እና ዜማ ድምፃዊ ቴዎድሮስ አብርሀም  በቅንብር ቻፒ እና ቢንአንዴ ማስተሪንጉን ቢኒ አንዴ መሆኑንም ድምፃዊው ለየኔ ቫይብ የመዝናኛ የሙዚቃ ዝግጅት ስለ ሙዚቃ ገልፆልናል፡፡– ይድነቃቸው ብርሀኑ -” ከኔ በላይ” ሐሙስ ምሽት የወጣ ነጠላ ሙዚቃ ነው ግጥም እልፍ አገድ አምሻው እና አዱዲ ያሲን ዜማ አቡዲ ያሲን ቅንብር እና ሚክስ ዓብይ አርካ ማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ፡፡ ድምፃዊው ይድነቃቸው ብርሀኑ ከ ዜና አንባቢነት በተጨማሪ በሙዚቃው ውስጥ የራሱን አሻራ እያስቀመጠ ይገኛል፡፡-ሳሙኤል ፍቃዱ- ”በሺህ አማላጅ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ በአዲስ አቀራረብ እየመጣ ይገኛል፡፡ ግጥም እና ዜማ በድምፃዊ ሳሙኤል ፍቃዱ የተሰራ ሲሆን ቅንብሩን ሮቤል ዳኜ እንደሰራው የኔ ቫይብ የሙዚቃ እና የመዝናኛ ዝግጅት ከ ድምፃዊው ሳሙኤል ፍቃዱ ሰምቷል፡፡ በቅርቡ ለ አድማጮች ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡– ኦሎፒክ ኮንሰርት- በመስቀል አደባባይ ኮንሰርቱ ቅዳሜ ሐምሌ 13 /2016 አመተ ምህረት ይከናወናል በዝግጅቱም 17 በላይ ዝነኛ ድምፃዊያን በመድረኩ ያቀርባሉ ላፎንቴን ፣ ዳዊት መለሰ ፣ ንዋይ ደበበ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ አንድዋለም ጎሳ ፣ ዲዲ ጋጋ ፣ ታደለ ገመቹ ፣ ዳግማዊ ታምራት እና የመሳሰሉት ታዋቂ ድምፃዊያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡– ብሩክ ፀጋዬ-“ጉዳቴ” የተሰ ሙዚቃ በቅርቡ ሙዚቃ ለአድማጮች ደርሷል ይህ ሙዚቃ በድምፃዊ እና የግጥም ዜማ ደራሲ ብስራት ሱራፌል የተሰራ ሲሆን ቅንብር ፣ ሚክስ ፣ ብሩክ ተቀባ ማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ይገኝበታል፡፡ አዳዲስ እና ወጣት ድምፃዊ ወደ ሙዚቃ ኢንደስትሪ እየቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡– ሐይሌ ሩት- ሐይሌሩት (ሐይለሚካኤል ጌትነት) አዲስ እና ሶስተኛ አልበሙን በቅርቡ ለአድማጮች ለማድረስ እንተዘጋጀ ይገኛል የመጀመርያ አልበሙ ቺጌ እና የታመነ አልበም ማድረሱ አይዘነጋም፡፡-ተወዳጁ ግጥም እና ዜማ ደራሲ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ሐምሌ 7/2016 48 ዓመቱን ይደፍናል፡፡ የኔ ቫይብ የመዝናኛ እና የሙዚቃ በተለያዩ ዝግጅቶች ቴዲ አፍሮን ልደት በደመቀ ዝግጅት እስቱዲዮ እናከብራለን፡፡

* በዚህ ሳምንት ካለፉት የሙዚቃ ጉዳዮች መካከል፡፡– ተወዳጁ ድምፃዊ የግጥም ዜማ ደራሲ እንዲሁም ዲጄ ሮፍናን ኑሪ እና ከተወዳጁ የአርኤድ ቢ አቀንቃኝ እና ዳንሰኛ ክሪስብራውን የሙዚቃ ስራዎቻቸውን በአትላታ ያቀርባሉቢ ቢባልም ሮፍናን ኑሪ ብቻ የሙዚቃ ስራዎችን አቅርቦ በሰዓት መጣበብ ምክንያት በቦታው የተገኘው ክሪስ ብራው ስራውን ሳያቀርብ ቀርቷል ተብሏል፡፡– አመታዊ የስፖርት ባህል ዝግጅት በማስመልከት አጠቃላይ የመዝግያ ምሽት ከ ባህር ማዶ አትላንታ ቅዳሜ በ29/2016 ደማቅ ኮንሰርት አቅርበዋል፡፡ ታላላቅ ድምፃዊያን በዝግጅቱ ሲሳተፉበት ድምፃዊት አስቴር አወቀ ፣ ፀጋዬ ስሜ ፣ጌትሽ ማሞ ፣ አረጋኸኝ ወራሽ እና የመሳሰሉት ከራስ ባንድ እና ከዲጄ ማሙሽ ጋር ሆነው ዝግጅቱን አድምቀው አምሽተዋል፡፡

* የኔ ቫይብ በዚህ ሳምንት የመረጥንላችሁ አልበም እንጠቁማችሁ፡፡– ሄዋን ገብረወልድ “ሄዋን” አልበም በስሟ የሰየመችሁ የብኩር አልበሟን ሐሙስ ግንቦት 25/2014 ነበር የተለቀቀው በዚህ አልበምዋ በውስጡ 11 ክሮች የያዘ ሲሆን ምን ይጠቅምሀል ፣ ሄዋን ፣ እንደኔ እንደኔ ፣ ትፈለጋለህ ፣ ሼሙና ፣ አለም ፣ አስብበት እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ላይ በርካታ የሙዚቃ ከያኒያን ተሳትፈዋል በቅንብሩ ዲጄ ሚላ ፣አቤል ጳውሎስ ፣ ሚካኤልሀይሉ (ሚኪ ጃኖ)፣ ብሩክ ተቀባ እና ታምሩ አማረ (ቶሚ) ተሳትፈዋል፡፡ በግጥም ዜማ ናትናኤል ግርማቸው ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን ፣ ዮሐና ፣ ምረት አብደስታ ፣ ሄዋን ገብረወልድ ፣ አንተነህ ወራሽ በማስተሪንግ አበጋዝ ክብረወርቅ ሽዎታ ናቸው፡፡

አዘጋጅ እና አቅራቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ ሐሳብ አስተያየት @temuela መስጠት ትችላላችሁ እናመሰግናለን

yenevibe.com ጎብኙን
145900cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች እና ሙዚቃዊ ክስተት በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንጠቁማችሁ፡፡https://t…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE