* ሳምንታዊ ሙዚቃ ክስተት በዚህ ሳምንት …https://telegra.ph/file/1aa52e1e6cc7b0838…

Reading Time: < 1 minute
* ሳምንታዊ ሙዚቃ ክስተት በዚህ ሳምንት …– የተወዳጁ ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሣሁን(ቴዲ አፍሮ) የሙዚቃ ኮንሰርት በዱባይ እሁድ ሰኔ 23 2016 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ኮንሰርቱ ቀርቧል፡፡ በኮካ ኮላ አሬኔ  17 ሺ ሰው ተመልካቾችን በሚያስተናግደው በዚህ ስታድየም ከ አቦጊዳ ባንድ ጋር በጋራ ሆኖ የአመቱን ታላቅ ኮንሰርት በዝግጅት አቅርበዋል፡፡ የድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በዱባይ በርካታ ተመልካች የመጣበት በኢትዮጲያ የድምፃዊያን ታሪክ ውስጥ የመጀመርያው ድምፃዊ በመሆን ታሪክ ፅፏል፡፡ተወዳጁ ድምፃዊ ቴዎድሮስ አሰፋ( ቴዲ ዮ) ከሞት መትረፉን የተገለፀበት ሳምንት ነበር ፡፡ በቅርቡ ይለያል የተሰኘ ሶስተኛ አልበሙን ለህዝብ አድርሶ በብዙዎቹ ዘንድ አድናቆትን ያተረፈው ድምፃዊ ቴዲ ዮ( ቴዎድሮስ አሰፋ)  በቅርቡ ለሚያቀርበው የሙዚቃ ኮንሰርት አሜሪካ መግባቱ ይታወቃል። ድምፃዊውም በአሜሪካ የጥቁሮች የነፃነት ቀን በሰፊው በሚከበርበት እለት በ june 20 የሙዚቃ ቪዲዬ ቀረፃ ላይ በቦታው ላይ የነበረውን አከባበር በማስገባት እየቀረፀ በነበረበት ሰአት በቦታው ላይ በጋንግስተሮች መሃል በተነሳ ጠብ የሽጉጥ ተኩስ ተነስቶ በቀኑ ቦታው ላይ ከነበሩት ሰዎች 15 ሰዎች ሲቆስሉ 1 ሰው ሞቷል። ድምፃዊ ቴዲ ዮ በቦታው ስለ ነበረ ጉዳት ሊደርስበት እንደነበረ እና ከዚህ አደጋ እንደ ተረፈ ገልጿል፡፡– ባሳለፍነው ሳምንት አንዱ አግራሞት የጫረብት የአንባሰልዋ ንግስት የድምፃዊ ማሪቱ ለገሰ ጉዳይ ነበር ባሳለፍነው እሁድ ለት ሰይፉ በኢቢኤስ ፕሮግራም ቀርባ በፕሮግራሙ የተሰማው ነገር አግራሞትን ፈጥሯል፡፡ ሰይፉ ማሪቱን ለገሰን ጠየቃት ”ታክሲ ተጋፍተሽ ፣ ተሰልፈሽ ነው ምትገቢው ሰዎች በመልዕክት ነግረውኛል እውነት ነው?ሲል ድምፃዊቷ ”አዎ” ነው ብላ መለሰች፡፡ ለብዙሀን የሙዚቃ ሲኦሲ የሆነች ድንቅ ድምፃዊት በዚህ ደረጃ ለምን ? በሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የባህላዊ ሙዚቃ (ፎኪ) ቱባዊ ቃና ካላቸው ድምፃዊያን ጥቂት ተርታ ትሰለፋለች ታክሲ እስከመጠበቅ እና ተጋፍቶ መግባት በዚህ ደረጃ ማየት የለብንም የሳምንቱ ትዝብታችን ይህ ነው ፡፡

* ወርሀዊ የሙዚቃ ምርጫችን በወሩ እንደ ምናደርሳችሁ በዘጠኛው ወር ዘጠነኛ አልበም እንጠቁማችሁ እናመስግናቸዋለን፡፡👇
144130cookie-check* ሳምንታዊ ሙዚቃ ክስተት በዚህ ሳምንት …https://telegra.ph/file/1aa52e1e6cc7b0838…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE