የሙዚቃ ምርጫ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አጥብቀው መከሩ ፡፡https://telegra.ph/file/925fe6a…

Reading Time: 2 minutes
የሙዚቃ ምርጫ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አጥብቀው መከሩ ፡፡



ፋና ላምሮት የመጀመርያው ምድብ አምስት ተወዳዳሪዎችን በሰባተኛ ሳምንት ከኮከብ ባንድ ጋር ሆነው የሙዚቃ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል፡፡

*ምን አዲስ ነገር አለ

-ኮከብ ባንድ እንደ ተለመደው ወደ 10 የሚጠጉ ሙዚቃዎች ከ ተወዳዳሪዎች ጋር አቅርበዋል፡፡



– በቀጣይ ሁለት ሳምንት ከሁለተኛው ምድብ ጋር በአንድ ሆነው አጠቃላይ ስምንት ሆነው ውድድራቸውን ያከናውናሉ፡፡

– አሁን ላይ ከ አስራ ስድስት ተወዳዳሪዎች ውድድሩ ሲጀምር ቆይተው ነበር በዚህም ስድስት ተወዳዳሪዎች እንስካሁንዋ ውድድር ተሰናብተዋል ወደ ዘጠኝ ተወዳዳሪዎች ፍልሚያውስጥ ይገኛሉ፡፡



-ጴጥሮስ ማስረሻ ይህ ብርቱ ተወዳዳሪ ሁሌም በሚያሳየው ብቃት ዳኞች ተመካች ይደመማሉ በተለይ የሙዚቃ አቀናባሪ አማኑኤል ይልማ አስተያየት ተሰቶ ነጥብ በሚያዝበት ሁለተኛው ዙር ላይ ጴጥሮስ የታጫወተውን ሙዚቃ በመውደዱ ነጥብ በሁለተኛው ዙር ሰቶታል፡፡



– ተመልካቶች እንደ ተለመደው በቦታው በመገኘት ውድድሩን በቀጥታ ተከታትለዋል፡፡

* ዳኞች ከስልትም ከስሜትም ሐሳብ ሰተዋል፡፡

-የማይክ አጠቃቀም ፣ ዳናሚክስ ፣ የሙዚቃ አቀራረብ ፣ የሙዚቃ ስሜት መጠበቅ ፣ በራስ ድምፅ ማዜም እና በራስ የሙዚቃ መንገድ ማቅረብ ፣ አይደንቲቲ(ራስን መሆን) ፣ ፍሬዚንግ(የዜማ ሐረጋት) ፣ የዜማ ምርጫ ፣ የሙዚቃ ምርጫ ፣ የድምፅ ጉልበት ምጠና እና አጠቃቀም ፣ የራስ አቅም ፣ የሙዚቃ ሂደቱን ለውጡን ፣ key(ኪ )ምጠና፣  ውበት ቀናሽ የሆነ አቀራረብ ማስወገድ ፣ በራስ ቃና ማቅረብ ፣ሬንጅ ፣ ቫልዩ አድ (አዲስ ነገር ማቅረብ) ፣ በራስ መተማመን እና የመሳሰሉ አስተያየት ተሰቷል፡፡

* ኮከብ ባንድ አስር ሙዚቃዎችን ከተወዳዳሪዎች ጋር ሆነው አቅርበዋል፡፡



ሙሉቀን መለሰ(አንቺ መሳይ ቆንጆ) ፣ ፀጋዬ እሸቱ(ሰው ምላሱ ታስሮ) ፣ ታምራት ሞላ(ፍቅሬን በምን ቋንቋ) ፣ ሚኒልክ ወስናቸው( ደመናው) ፣ቴዎድሮስ ታደሰ(ማለዳ) ፣ ትዕግስት ፋንታሁን(እንደ ማላገኝህ) ፣ መልካሙ ተበጀ( ባር ባር) ፣ ፀሐዬ ዮሀንስ( ምናሉ ስለ እኔ) እና የመሳሰሉት ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል፡፡

* ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት ሰተዋል፡፡

👇

-የሹምነሽ ታዬ:- ጆሮ ላይ ያልገቡ ሙዚቃ ወደ ራስ በማምጣት በራስ ቀለም አርጎ መጫወት ያስፈልጋል፡፡

👇

-አማኑኤል ይልማ:- የሙዚቃ ውበቱ ያለው አናቱ ላይ ነው፡፡

👇

– ብሩክ አሰፋ :- ምስል ከሳች ሙዚቃዎችን መዝፈን በጣም ከባድ ነው ብዙ ነገር ማሰብ ይጠይቃል፡፡

*ያለፉ ተወዳዳሪዎች እና የተሰናባቹን ሙሉ ነጥብ እንግለፅላችሁ፡፡

-ጴጥሮስ ማስረሻ- 59591 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ናሆም ነጋሽ-59511 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ዘላለም ፀጋዬ-58582 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ኤርሚያል ዳኛው- 58574 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡

የሳምንቱ ተሰናባች …ዳኞች ስለ ድምጿ እጅግ ያደንቃሉ በተለይ የብዙ ድምፃዊያንን ሙዚቃ በራስ ድምፅ መዝፈን ሆሌም አስምረው ይነግሯታል ፡፡ በእለቱ ያቀረበችው ሙዚቃ የሙዚቃ ምርጫ ስህተት በመሆኑ ብዙ ስህተቶች ተፈጥረዋል በዛም ዳኞች ቅር ተሰኝተው እየወደዷት ሸኝተዋታል፡፡



ዝንታለም ባዬ አጠቃላይ ነጥብ 58048 አጠቃላይ በማምጣት እና ፋናም በዚህ አብሮነቱን ገልፆ ከ 8000 ሺህ ብር ጋር ሸንተዋታል፡፡



ዝንት አለም ባዬ” ይህ ውድድር ነው ፋና ላምሮ የእለት የሙዚቃ አቀራረብን ይለካል በዛሬ ባቀረብኩት ነገር መሰናበቱ ይገባኛል፡፡ ሁሉም አመሰግናለሁ ዳኞች ፣ ኮከብ ባንዶችን ፣ ሁሉንም ከልብ አመሰግናለሁ አንድ ምዕራፍ ከፍ አርጎኛል እኔን”  ብላለች፡፡

ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት
yenevibe.com ጎብኙን እናመሰግናለን
142580cookie-checkየሙዚቃ ምርጫ ላይ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አጥብቀው መከሩ ፡፡https://telegra.ph/file/925fe6a…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE