*በዚህ ሳምንት የሰማናቸው ሙዚቃዊ ክስተት ጉዳይ፡፡https://telegra.ph/file/3883a036e531…

Reading Time: < 1 minute
*በዚህ ሳምንት የሰማናቸው ሙዚቃዊ ክስተት ጉዳይ፡፡



– የኦሮምኛ የሙዚቃ አቀንቃኝ ድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ያረፈበት አራተኛ አመት ሙት አመት መታሰብያ በሱ ስም የተሰየመው ሶስተኛም የሀጫሉ ሁንዴሳ ሀዋርድ በሰኔ 22/2016 ይከናወራል ተብሏል፡፡ በውስጡ አስራ አንድ ዘርፍ ያለው ሲሆን የአመቱ ምርጥ አቀናባሪ ፣ የአመቱ ግጥም እና ዜማ ደራሲ እና የመሳሰሉት በውስጡ ተካተዋል ተብሏል፡፡



– “ዮቶር ድግስ “የተሰኘ ልዩ የሙዚቃ ኮንሰርት  ሰኔ 15/2016 ቅዳሜ ከምሽቱ 12 ሰአት ጀምሮ ሊካሄድ  እንደሆነ አዘጋጆቹ ሰኔ 10/2016 በማርዮት ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል። ተወዳጁ ግጥም ዜማ ደራሲ እና ፕሮዲውሰር አለማየሁ ደመቀ ለማክበር በርካታ ድምፃዊያን ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ፡፡ጎሳዬ ተስፋዬ ፣ ኃይልዬ ታደሰ ፣ አብነት አጎናፍር ፣ ግርማ ተፈራ ፣ ሀሊማ አብዱራህማን ፣ ሄለን በርሄ ፣ ዳዊት ፅጌ ፣ ብስራት ሱራፌል ፣ አዲስ ለገሰ ፣ አንተነህ ምናሉ ፣ አበባው ጌታቸው ፣ዳግማዊ ታምራት ፣ መስከረም ኡስማንን ጨምሮ ከ ኢትዮ ለዛ ፣ ሻኩራ ባንድ ፣ኩርማንባንድ ሆነው ያቀርባሉ ፡፡የግጥም ዜማ ደራሲ አለማየሁ ደመቀ 250 በላይ የግጥም ስራዎችን ለተለያዩ ድምፃዊያን ያበረከተ ሲሆን በማህበራዊ ጉዳይ ላይም የሰራቸው ስራዎች አሉ፡፡የኮንሰርቱ አላማ  ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ ከ20 በላይ የሆኑ የሙዚቃ ሥራዎችን፣ለ15 ጊዜያት ያህል ተደጋግሞ የታተመውን “ዮቶር 1,ኮብላዩ ” ካሕን እና በቅርቡ ለንባብ ያበቃውን “ዮቶር 2,ቶ” ለሥነጽሁፍ አፍቃሪያን ያበረከተውን ላለፉት 25 አመታት በሙያው ፣በክህሎቱ እና በተሰጥኦው አገር እና ወገንን ሲያገለግል የቆየው ደራሲ፣የግጥምና ዜማ ደራሲ፣ፕሮዲዩሰር እና ድምፃዊ ዓለማየሁ ደመቀን የሚከበርበትና ሁለተኛ መፅሐፉን “ዮቶር 2:ቶ”ን የሚመረቅበት ቀን እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልፀዋል ። የኮንሰርቱ መግቢያ ዋጋ፡ 3000 ነው ተብሏል፡፡

የኔ ቫይብ በዚህ ሳምንት እንድታዳምጡ የመረጥንላችሁ የሙዚቃ አልበም ፡፡



የተወዳጁ ድምፃዊ ግጥም እና ዜማ ደራሲ ብስራት ጋረደው ”ሳላምንበት” የተሰኘ አልበም ነው ይህ አልበም 1997 የተሰራ ሲሆን በውስጡ ወደ አስራ አንድ የሙዚቃ ክሮች ሲኖሩት እኔ አንገቴን ልድፋ ፣ አለሁ ፣ ቃና ዘገሊላ ፣ ያለጥርጥር ፣ ግልግል ነው እና የመሳሰሉት አሉበት ይንን አልበም በግጥም በዜማ በራሱ በድምፃዊ ብስራት ጋረደው ሲሰራ ቅንብር ፣ ማስተሪንግ ፣የድምፅ ቅጂ ፣ በድምፅ አጃቢነት ተወዳጁ ዳግማዊ አሊ ሙሉ አልበሙን አበጅቶታል፡፡

yenevibe.com ገብታችሁ ጎብኙን እናመሰግናለን፡፡
ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
141400cookie-check*በዚህ ሳምንት የሰማናቸው ሙዚቃዊ ክስተት ጉዳይ፡፡https://telegra.ph/file/3883a036e531…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE