ዳኞች በለውጣቸው ተደስተው ግን የሙዚቃ መሰረታዊ ችግር ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡https://telegra.ph/…

Reading Time: 2 minutes
ዳኞች በለውጣቸው ተደስተው ግን የሙዚቃ መሰረታዊ ችግር ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡
ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው ምዕራፍ  በአምስተኛ ሳምንት ስድስት ተወዳዳሪዎችን ይዞ ከኮከብ ባንድ ጋር ውድድሩን አከናውነዋል ፡፡

*ምን አዲስ ነገር ታዬ

– ተወዳዳሪዎች በሁለት ዙር የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ሲያቀርቡ አንደኛው ዙር ዳኞች በመረጡላቸው ሙዚቃዎች ተጫውተዋል እኔን ይመጥነኛል ያሉትን በመድረኩ አቅርበዋል፡፡

– ውድድሩ በሚከናወንበት ቦታ ተመልካች የፋና ላምሮት ወዳጅ ፣የሙዚቃ ሰዎች ፣ በዚህ ውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ ለቀጣዩ ለመዘጋጀት የሚያደርጉ ሰዎች እና ተወዳዳሪዎችን ለመደገፍ የመጡ ሰዎች በቦታው ታድመው ተከታትለዋል ፡፡

– በመድረኩ ከቀረቡ የሙዚቃ ስራዎች መካከል የሰሩት በግጥም በዜማ እንዲሁም በቅንብር የጋሽ ተስፋዬ ለማ ፣  ተመስገን አፈወርቅ ፣ ብስራት ጋረደው ፣ አበበ ብርሀኔ በቅንብሩ የአበጋዝ ፣  ቴዲ ማክ ፣ ዳግማዊ አሊ እኚህ እና የመሳሰሉት በመድረኩ ቀርበዋል፡፡* ዳኞች ለተወዳዳሪዎች ከስልትም ከስሜትም የሰጡትን አስተያየት

ሬንጅ ስፋት ፣ ይበልጥን መስራትን ፣ ለስሜት መጨነቅ ፣ የዜማ ብዛትን መምረጥ ፣ ሪትም ፣ ኪ መረጣ ፣ ውበት የዜማ የድምፅ ፣ የማይክ አጠቃቀም ፣ የባንድ ውህድ ፣ ፍሬዚንግ /የዜማ ሐረጋት ተጀምሮ እስኪያልቅ ያለውን/ ፣ ቅኝት ፣ የድምፅ ከለር ፣ የጉልበት ምጠና እና አጠቃቀም ፣ ትንፋሽ ፣ የድምፅ ቴክኒክ ፣ መረጋጋት ፣ ስሜት ተከትሎ ሙዚቃውን ማቅረብ ፣ ቃላትን አጥብቆ ማለማት ፣ ፍርሀት ፣ አገላለፅ እኚህ እና የመሳሰሉት አስተያየት ተሰንዝረዋል ፡፡

* ኮከብ ባንድ ከተወዳዳሪዎች ወደ 12  ሙዚቃዎች ተጫውተዋል ፡፡– ቀመር ዩሱፍ/ኦሮምያ/ ፣ ተፈራ ነጋሽ/ምን አምኜ/ ፣ ፍቅር አዲስ ነቃ ጥበብ/ አልገባኝም / ፣ ጋሽ ጥላሁን ገሰሰ/ አይ ዘመን/ ፣ ትክለለኛው ሙዚቃ የጥላሁን ገሰሰን ደግማ የተጫወተችሁ የዘሪቱ ከበደ/ ወጣትዋ/ ፣ ሚኒልክ ወስናቸው/በሰው ሃገር/ ፣ ጋሽ ሙሐሙድ አህመድ /ፍቅሬ በመሆንሽ/ ፣ እብስት ጥሩነህ/ከመሸህ መጣህ/ ፣ ነፃነት መለሰ / ሁሉን ትቼ/ ሙዚቃዎች በመድረኩ ቀርበዋል፡፡

*ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት አስተያየት ሰተውናል፡፡

– ብሩክ አሰፋ:- ምን ለማሳየት ነው ዜማ መምረጥ ያለብኝ የሚለውንም ማሰብ ያስፈልጋል፡፡-የሹም ነሽ ታዬ:-እራሳችሁን ድምፃችሁን የሚፈትሽ ሙዚቃ የምትመርጡትን ሁሉ አስቡበት፡፡– አማኑኤል ይልማ:- የድምፅ ውበት እና ቅኝት እጅግ ተጠንቅቆ ማቅረብ ይኖርባችኃል፡* በእለቱ ያለፉ እና አንድ ተወዳዳሪ የተሰናበተውን እንጠቁም፡፡

-ጴጥሮስ ማስረሻ – 59968 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ናሆም ነጋሽ-59489 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ዝንታለም ባዬ-58454 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ኤርሚያስ ዳኛው-58368 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ዘላለም ፀጋዬ-57980 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡

👇

በእለቱ የተሰናበተችሁ ባወፉ በመጡት ዙሮች አስገራሚ እና የተስፋ የተጣለባት በተጨማሪም ከ ዳኞች የተሰጣት ገንቢ አስተያየት በመቀበል በውድድሩ ጥሩ ቆይታ አግርጋለች በስተ መጨረሻ ተናብታለች ተወዳዳሪ ትዕግስት አንተነህ፡፡

https://telegra.ph/file/9fff36b2ff3ab8ec37118.jpg👇

* ትዕግስት አንተነህ:-” በጣም አማመሰግናት ድምፃዊ ታምር ግዛው ዲዴፋትስ ውጪ ሀገር ነው የሚገኘሁ እህቴ መልከ ማርያም ጥላዬ ሁሉንም አመሰግናለሁ፡፡”ብላለች፡፡ ፋና ላምሮት አብሮተቱን ገልፆ ከ 7000 ብር ጋር ሸኝቷቷል፡፡ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት
ቸር ያቆየን ቸር እንሰንብት
141090cookie-checkዳኞች በለውጣቸው ተደስተው ግን የሙዚቃ መሰረታዊ ችግር ጉዳይ ላይ መክረዋል፡፡https://telegra.ph/…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE