የቴሌቪዥን ሾዉ አቅራቢዋ ቀደም ሲል በኢትዮጲያ ብሮድካስቲግ (Ebc) እንዲሁም በሽገር ኤፍ.ኤም 102.1 ሬዲዮ በሚተላለፈዉ ታዲያስ አዲስ እንዲሁም በኢትዮ ኤፍ.ኤም 107.8 ታዲያስ አዲስ በአሁን በራሷ ምሳሌ የሬዲዮ ኘሮግራም ከባልደረባዋ ሰመረ ባሪያዉ ጋር በመሆን የሬዲዮና የቴሌቪዥንበዜናና በኘሮግራም አቅራቢነት ትታወቃለች ተወዳጅነት ባገኘችዉ ኢ.ቢ.ኤስ ቴሌቪዥን (EBS Tv) ቅዳሜን በኢ.ቢ.ኤስ ኘሮግራም አዘጋጅነትና አቅራቢነት ጋዜጠኛ እፀገነት ይልማ የኢትዮ ኦርጋኒክ ፉድ ኢምፖርተር ብራንድ አምባሳደር ሆነች።
ኢትዮ ኦርጋኒክ ፉድ ኢምፖርት የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢ ጋዜጠኛ የሆነችውን እፀገነት ይልማን የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛሬው እለት ዛሬ በሳፋየር አዲስ ሆቴል በተከናወነ መርሐግብር ላይ ተገለጸ።
ኢትዮ ኦርጋኒክ ፉድ ኢምፖርተር ካለፈው ዓመት ጀምሮ በዓለማችን ላይ እጅግ ጠቃሚ የሆነውን የቺያ ዘር ከውጪ አገር አስመጥቶ በማከፋፈል ላይ የሚገኝ ሲሆን የቺያ ዘር ወይም ቺያ ሲድ ለጤና ባለው ከፍተኛ ጥቅም እጅግ ተፈላጊ መሆኑን በማንሳት ኢትዮ ኦርጋኒክ ፉድ ኢምፖርተር
ኦርጋኒክ የሆነውን የቺያ ዘር ቀጥታ ከአምራች ገበሬዎች ጋር ትስስር በመፍጠር እያቀረበ ይገኛል፡፡
ከቺያ ሲድ የደም ውስጥ ስኳርን ለመቆጣጠር፣ ለአእምሮ ጤንነትና ብቃት፣ ለልብ እና ሴሎች ጤንነት ፣ ከካንሰር ራስን ለመጠበቅ፣ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር፣ ለክብደት መቀነስ፣ ለአጥንት እና የጥርስ ጤና፣ ለወሊድ (ፈርቲሊቲ)፣ ለቆዳ ጤንነትና ውበት፣ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት፣ ድባቴንና ጭንቅትን ለመቀነስ፣ ለእርጉዝ እናቶች እና ለፅንስ ዕደገት ጠቀሜታ እንዳለው በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።