በጋርዱላ ዞን ደራሼ ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህልና ፊላ የሙዚቃ ቅኝት ዙሪያ ጥናት እየተካሄደ ነው።****ht…

Reading Time: < 1 minute
በጋርዱላ ዞን ደራሼ ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህልና ፊላ የሙዚቃ ቅኝት ዙሪያ ጥናት እየተካሄደ ነው።

****የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነ-ጥበብ ዘርፍ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከጋርዱላ ዞን ጋር በመተባበር <<ክውን ጥበባት ከመገኛ ምንጩ>> በሚል ሀሳብ በጋርዱላ ዞን በደራሼ ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህል እና ፊላ የሙዚቃ ቅኝት ዙሪያ ላይ ቦታው ድረስ በመገኘት ጥናት እያደረገ ይገኛል።

የጋርዱላ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ አዳነ ለገሠ የሙዚቃ አጥኚ ቡድኑን ከአርባ ምጭ ተቀብለው እስከ ጋርዱላ ዞን ደራሼ ማህበረሰብ ያለውን ተፈጥሯዊ መልክአ ምድር፣ ባህልና ታሪክ ለአጥኚ ቡድኑ ገለፃ አድረገዋል።የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የሙዝቃ አጥኚ ቡድን የታሪክ፣ የባህልና የኪነ-ጥበብ አምባ ወደ ሆነችው ጋርዱላ ዞን ጊዶሌ ከተማ ሲገቡ የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ ኩናሎን፣ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ግንኙነት ኪታሞ፣ የደራሼ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አጥናፉ ተስፋዬ ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና “የፊላ” ቡድን  ተጨዋቾች ደማቅ አቀባበል አድረገውላቸዋል።የጋርዱላ ዞን ዋና አስተዳደር አቶ ብርሃኑ ኩናሎን የእንኳን ደህና መጣቹህ መልዕክት አስተላልፈው ስለ ጋርዱላ ዞን ምድር በአንድነት መዋብ፣ በጋራ ማንፀባረቅ፣ በህብረት መድመቅና ከጥንት ጀምሮ የሚታወቁበት መለያቸው ስለ ሆነው ”ፊላ” የተሠኘ የትንፋሽ የሙዚቃ መሣሪያ መሆኑን እና “የፊላ” ጨዋታ ለደራሼ ማህበረሰብ ልዩ  መገለጫ እንደሆነ በመግለጽ የጨዋታውን ታሪካዊ  አመጣጥ ሰፊ ማብራሪያና ትንታኔ ለሙዚቃ አጥኚ ቡድኑ ገልፀዋል።አክለውም ”ጣዕሜ መረዋ” ብቸኛው ባለ 7 ኖታ የሆነው የጋርዱላ ዞን  ባህላዊው የትንፋሽ የሙዝቃ መሣሪያ የሆነው “የፊላ” ጨዋታ በመሠረቱ ሙዚቃንና ዳንስን የያዘ ሲሆን የፊላ ጨዋታ ያለ አንዳች ጥላቻና ንትርክ ሴትና ወንድ ያለ እድሜ ልዩነት በእኩልነትና በወዳጅነት ስሜት ተሠባስበው እየተቀባበሉ የሚጫወቱበት መሣርያ መሆኑን ገልፀዋል ።የሙዝቃ አጥኝ ቡድን በዞኑ በሚኖረው  ቆይታም  ጋርዱላ ዞን የደራሼ ማህበረሰብ “የፊላ” ጨዋታን ከምንጩ ለይቶ ለማጥናትና የሙዚቃ ቅኝቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ በመሰነድ የብሔረሰቡን የኪነ-ጥበብ ሀብት በቅርስ መልክ በማስቀመጥ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ እንደሆነ የገለፁት የአዲስ አበባ ባህል ፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነ-ጥበብ ሀብቶች ልማት መድረኮችና ኩነቶች ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ደኑ ናቸው።ዘገባው የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ነው።
140570cookie-checkበጋርዱላ ዞን ደራሼ ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህልና ፊላ የሙዚቃ ቅኝት ዙሪያ ጥናት እየተካሄደ ነው።****ht…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE