የሮፍናን የኔ ትውልድ ወደ አሜሪካ “USA” ተጉዞ የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው ፡፡ዲጄ ፣ የዜማ የግጥም ደ…

Reading Time: < 1 minute
*
የሮፍናን የኔ ትውልድ ወደ አሜሪካ “USA” ተጉዞ የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው ፡፡

ዲጄ ፣ የዜማ የግጥም ደራሲ ፣ የድምፅ ኦድዮ ኢንጅነር  እንዲሁም ድምፃዊ ሮፍናን ኑሪ ከምነው ሸዋ ጋር አንድ ላይ በመሆን በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው፡፡

ሮፍናን ኑሪ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉለት አልበሞች  የመጀመርያ አልበሙ ነፀብራቅ በኤክትሮኒስ ዳንስ ሚውዚክ በመጠቀም አድርሶን ነበር በመቀጠል  ሶስት እና ስድስት ከዛም ባለፈ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ወደ አድማጭ አድርሷል፡፡

ስድስት የተሰኘው አልበም ስለ ተስፋ፣ ስለ ፍቅር የዳሰሰ ሲሆን በውስጡ 15(አስራ አምስት) ትራኮችን ይዟል፡፡

በዚህ ዓመት “ዘጠኝ” ሲል በውስጡ ወደ ሁለት አልበም የተሰሩለት ሲሆን ”ሐራንቤ ” እና “ኖር” የተሰኙ የሙዚቃ ስራዎንች ሲሆኑ ወደ 21 የሚጠጉ የሙዚቃ ክሮች ይዘዋል ፡፡

ሐራንቤ – ማለት ሕብረት ዩኒቲን የሚገልፅ አንድነትን የሚሽት ሲሆን “ኖር ” ማለት ደግሞ አዲስ ሐሳብ የሚፈልቅበት አዲስ አስተሳሰብ የሚነፍስበት መሆኑን ገልጿል ፡፡

በሙዚቃ አብሮአቸው ከሰራቸው መካከል ሐይለሚካኤል ጌትነት ፣ መሲዋኒ ፣ደረጄ ዘመዱ ፣ ሸዊት መዝገቡ ፣ የልጅ ተመስገን ልጆች በጋራ አልበሙን አድምቀውታል ፡፡

ከአለም አቀፍ የሙዚቃ ካንፖኒ ከሆነው ከ ዩንቨርሳል ጋር ስራዎቹን ለማቅረብ መፈራረማቸው አይዘነጋም፡፡

via:- Yenevibe
140490cookie-checkየሮፍናን የኔ ትውልድ ወደ አሜሪካ “USA” ተጉዞ የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው ፡፡ዲጄ ፣ የዜማ የግጥም ደ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE