ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደሙዚቃ ልኳ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ   ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ “የኢትዮጵያ የሙዚቃ አቀ…

Reading Time: < 1 minute
*
ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ

ሙዚቃ ልኳ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ  

ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ “የኢትዮጵያ የሙዚቃ አቀናባሪ” እስከመባል የደረሱ በዚህም  የተነሳ በ1959 ዓ.ም. የቀዳማዊ ኃ/ሥላሴ በጎ አድራጎት ድርጅት ሽልማትን የተቀዳጁ ስመጥር ባለሙያ እንደሆኑም ይገልጻሉ ምሁራኑ፡፡

“ባላ ዋሽንቱ እረኛ” ወይም “The Shepherd Flutist” የተሰኘው ስራቸው በሀገራችን ኢትዮጵያ በስፋት ይታወቃል፡፡ በተጨማሪም ፕሮፌሰሩ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1982 ደግሞ  “Roots of Black Music” የተሰኘ መጽሐፍ ለህትመት አብቅተዋል፡፡

ከሀገራችን የሙዚቃ እድገት አስተዋጿቸው ባሻገር በጎረቤት ሀገር ሱዳን የዳንስና ደራማ ኢንስቲትዩት በማቋቋም ላበረከቱት ጉልህ አበርክቶ ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፤ የሳይንስና ባህል ተቋም ከፍተኛ እውቅናን ማግኘት መቻላቸውን ታሪካቸው ያሳያል፡፡

እልፍ የዘመናዊ ሙዚቃ ስራዎችን ያበረከቱት ፕሮፌሰር አሸናፊ በአሜሪካ፤ ካናዳና በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ስራዎቻቸውን በማቅረብ አንቱታን ማትረፍ ከመቻላቸው ባሻገር ገና በ26 አመታቸው በሀንጋሪ ርዕሰ መዲና በሆነቸው ቡዳፔስት አስደማመሚ የሙዚቃ ኦርኬስትራን አስመልክተዋል፡፡ አሜሪካ በነበራቸው ቆይታ ከመኖሪያቸው ፍሎሪዳ ባሻገር በተለያዩ ግዛቶች በመዘዋወር የሙዚቃ እውቀታቸውን ለትውልድ ማጋራታቸው ይጠቀሳል፡፡

በ1960ዎቹ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ በተከታታይ የማስትሬትና  የፒ.ኤች.ዲ ትምህርታቸውን ማሳካታቸው  እንዲሁም በዘመናቸው የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎችን ለዓለም ማበርከታቸው ከብዙ በጥቂቱ ይታወሳል፡፡
140440cookie-checkፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደሙዚቃ ልኳ ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ   ፕሮፌሰር አሸናፊ ከበደ “የኢትዮጵያ የሙዚቃ አቀ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE