* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት …https://telegra.ph/file/67eb481f566d8eb97b9b2….

Reading Time: 2 minutes
* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት …



– መሳይ ተፈራ- ”የልቤን” የመጀመርያ የበኩር አልበሙን አምስት አመት የለፋበትን በሰኔ ወርሀ መጀመርያ ሴኔ 1/2016 በራሱ ዩትዮብ ቻናል እንደ ሚለቅ አስታውቋል፡፡ ድምፃዊ መሳይ ተፈራ “የልቤን አልበም እንደ ልቤ የሰራሁት አልበም ነው “ሲል ገልጿል፡፡



-በዚህ ሳምንት ከሰማነው ሙዚቃዊ ጉዳይ አንዱ ቤዝ ጊታር ተጫዋች የተፊት የጂጂ ማናጀር “ቶማስ ጎበና” የኢትዮጲያ የሙዚቃ ጉዞውን አድንቋል፡፡ቶማስ ጎበና እንዲህ ሲል ገልጶ አስተያየቱን ገልጿል “አሁን ብዙ ወጣቶችን ነው የምሰማው እውነት ለመናገር ምክንያቱም ለየት ያለ ነገር ይዘው የመጡትም እነሱ ናቸው። ወግዳዊት ፣ ጀንበሩ ፣ ሮፍናን እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ስራ ነው እየሰሩ ያሉት፡፡”የማ” የምትባል ከእዮኤል ጋር አሁን የለቀቁት አንድ አልበም አለ። ከተማ ውስጥ የሚገርሙ ሙዚቀኞች ናቸው ያሉት። ስንሻው ሰገሰ በሰሞኑን አዲስ አልበም አውቷል። እነ ሌሉ ፣ እነ ማህሌት ፣ እነ ዮሃና እነዚህ ሁሉ የሚገሩሙ ወጣት ሙዚቀኞች ናቸው”ሲል ሐሳቡን አቀብሏል፡፡



-“መሆን ሪከርድስ” የተባሉ ዩትዮበሮች ለየት ያለ አዲስ ነገር አስመልክተውናል፡፡ Salon Music Show !( የቤት ውስጥ ሾው )በማቅረብ በክብር በሥርዓት በልፍኞቻቸው በዓይነ ህሊና ላፍታ እንታደመናለን።’ Salon music show ‘  እንዲገማሸሩበት በ”መሆን ሪኮርድስ “ አዘጋጅተዋል። በዚህ የቤት ውስጥ ኮንሰርት ( Home Concert ) የተለያዩ ወጣት እና ታዋቂ ድምፃውያን የሚሳተፉበት ሲሆን ‘ Mehon Records Official you tube channel ላይ የተለያዩ ሙዚቃ ክንውኖች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡



– ከ አዲስ አበባ የቀጠለው አቀናባሪ እና የዜማ ግጥም ደራሲ ሮፍናን የሙዚቃ ስልጠና በሐዋሳ ቀጠሮውን ይዟል፡፡” ROPHNAN’S MASTERCLASS ” ሙዚቀኛ ሮፍናን “በሙያዬ የማውቃትን ለማካፈል እንቅፋቶቼን ሌሎች እንዳትመቱ እንድትሻሉም እግዚአብሔር እንደፈቀደላችሁም በሙያችሁም ከእኔ በብዙ ርቀት ተሽላችሁ እንድትሄዱ ሀገርንም በሙያችሁ በልፋታችሁ የተሻለ እንድታገለግሉ እንድታስጠሩም በሚል መነሻ ለ150 ሰዎች በኤሊያና ሆቴል በሚገኘው ሲኒማ ውስጥ ከጥር 27 እስከ 29/ 2016 ዓ.ም መስጠቱ የሚታወቅ ነው።ሙዚቀኛ  ሮፍናን ኑሪ  ” ነፀበራቅ ”  ፣ ” ስድስት ” ፣ ” ዘጠኝ ‘- ሐራምቤ እና ኖር ” የተሰኙ አለበሞችን ከዚህ በፊት ማውጣቱ የሚታወቅ ነው።



ወጣቱ ድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ኮንሰርት ለማቅረብ ቀን መቁረጡ ይታወሳል አሁን ደሞ ቦታን እና አብረውት የሚሰሩት ድምፃዊያንን ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህ መሰረት ድምፃዊያን ሚካኤል በላይነህ ፣ ሳሙኤል ብርሀኑ (ሳሚ ዳን)፣ ልዑል ሲሳይ የሙዚቃ ዝግጅታቸውን ያቀርባሉ ቦታው  በሚሊኒየም አዳራሽ ጊቢ ውስጥ ይቀርባል፡፡

* በዚህ ሳምንት አልበም የምንጋብዛችሁ

በዚህ ዘመን ጥንቅቅ ተደርገው ከተሰሩት የሙዚቃ አልበሞች መካከል የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ “ልዑል” አልበም በርካታ ከያኒያን የተሳተፉበት ይህ አልበም ብዙ ጉዳዮችን ዳስሷል፡፡ በቅንብር ኪሩቤል ተስፋዬ፣ ኤክስፕረስ ባንድ በግጥም እና ዜማ ምረት አብ ደስታ ፣ ወንደሰን ይሁብ ፣ ደጎል መኮንን ፣ ሞገስ ተካ ፣ እሱባለሁ ይታየው( የሺ) ፣ ወንደሰን ይሁብ ናቸው፡፡ አልጣልሽ ፣ የኔ ዓመል ፣ መልኬ በቃኝ ፣ ባያት ተካትተዋል፡፡



@biggrs @yenevibe Yenevibe.com ጎብኙን፡፡
139880cookie-check* ሙዚቃዊ ክስተት በዚህ ሳምንት …https://telegra.ph/file/67eb481f566d8eb97b9b2….

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE