” ምን ሆኛለሁ ? መጽሐፍ የትዕግስት ዋልተንጉስ አዲስ መፅሐፍhttps://telegra.ph/file/fa8bb…

Reading Time: 2 minutes
” ምን ሆኛለሁ ? መጽሐፍ የትዕግስት ዋልተንጉስ አዲስ መፅሐፍየወራት ድካም ነው ። እኔን በግል ለቀናት ካልተገደድኩ ከቤት እንዳልወጣ ያደረገኝና ብዙ ማህበራዊ ግንኙነቴን ያቋረጠብኝ ስራ ነው ። ድካማችን ለመልካም በመሆኑ ሁለታችንም ደስተኞች ነን ። አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ ፣ ከማለፉ በፊት ከሚሰራቸው ስራዎች መሀል አንዱ ( ለትዕግሥት ዋልተንጉሥ እና ለእኔ ) ይህ ” ምን ሆኛለሁ ? ” ብለን የሰየምነው መጽሐፍ ነው ። ” ምን ሆኛለሁ ? ” ለትዕግሥት ዋልተንጉሥ የመጀመሪያዋ ፣ ለእኔ ደግሞ 7ኛ ስራችን ነው ። የሁለታችን ጥምረት ትልቅ ስራ የፈጠረ ይመስለኛል ።

የስነልቦና ባለሙያዋ ትዕግሥት ዋልተንጉሥ ከ15 ዓመት በላይ በምክክር አገልግሎት ላይ ሰርታለች ። በ” እርቅ ማዕድ ” የሬዲዮ ፕሮግራም እንዲሁም በEBS ቴሌቪዥን ” እንመካከር ” ፕሮግራምን አዘጋጅታለች ። እኔ መጠየቅ ፣ ሀሳቦችን የተቻለኝን ያህል ውስጥ ድረስ ገብቼ ለመረዳት መሞከር ፣ ቀላል እና ልብ ደረስ አማርኛን መጻፍ እችላለሁ ። ሁለታችን ” ምን ሆኛለሁ ? ” ን ከማንም ቀድመን ራሳችን ወደነዋል ። እኔ በግሌ እስካሁን በጽሑፍ ከሰራኋቸው መጻሕፍትም ፣ ድራማዎችም ሁሉ የእኔ ለምለው ሕዝብ የማበረክተው ትልቁ ስራ ይህ በቅርቡ የሚወጣው መጽሐፍ እንደሚሆን አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ ። በቀላሉ የምማልል እና በራሴ ስራ የምመሰጥ ሰው አይደለሁም ። ” ምን ሆኛለሁ ? ” ግን እንደዚያ አይነት ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል ። ይሄ ስሜት ነገ እናንተ ላይ እንደሚጋባ አምናለሁ ።” ምን ሆኛለሁ ? ” ን በመስራቱ ሂደት ለእኔ ትልቁ የስነልቦና ት/ቤት የገባሁ ያህል ተሰምቶኛል ። የራሴን ፣ የቤተሰቤን ፣ የወዳጆቼን ፣ በቅርብም በርቀትም የማያቸውን ኢትዮጵያውያን ፣ ዝነኛ ሰዎችን ፣ ፖለቲከኞችን ፣ የእውቀት ሰዎችን ለየት ያሉ ባህርያት ለመረዳት ፣ ምክንያታቸውን ለመገመት ፣ ሰውን በሚመለከት ፈራጅ ላለመሆን ፣ ሰው ማለት አሁን አብሮን የሚኖረው ወይም የሚሰራው ብቻ ሳይሆን የእስከዛሬውን – ይበልጡንም ልጅነቱንና አስተዳደጉን እንደሆነ እንድገነዘብ ረድቶኛል ።” ይህን መጽሐፍ የሚያነቡ ሰዎች ራሳቸውንና የሚያውቋቸውን ሁሉ እንዲፈትሹ ፣ እንዲረዱና እንዲያግዙ እጅጉን ይረዳቸዋል ። ፖሊሲ አውጪዎች ለፖሊሲ ጥናት ይጠቅማቸዋል ብዬ አምናለሁ ። ” ይህን ያለው አንድ የአዕምሮ ሀኪም ነው ። ይህን አስተያየቱን በመጽሐፉ ላይ ታገኙታላችሁ ። ዛሬ ላይ ከሚታይ የሰው ባህሪ ተነስተን ” እገሌ ማለት እንዲህ ነው ። ይህን ያደረገው ሆን ብሎ እኛን /እገሌን ለመጉዳት ነው ” እንላለን ። ከሂደቱ ይልቅ የመጨረሻ ውጤቱ ያሳስበናል ። ማንም ከባዶ ሜዳ ተነስቶ ምንም እንደማያደርግ ነው የስነልቦና ሰዎች የሚያምኑት ።በተለይ አሁን ባለንበት ጊዜ ” ምን ሆኛለሁ ? ” መጽሐፍ እጅጉን ያስፈልጋል ። መንግሥት ወይም ሌሎች መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት በሚሊዮን ቅጂ አባዝተው በየቤቱ ቢያዳርሱና ልክ አሽከርካሪዎች የአሽከርካሪ ቀበቶ ተገደው አስረው ለሕይወታቸው ጠቃሚ እንደሆነው ከዚያ በላይ ፋይዳ ያለው ስራ እንደሆነ አምንበታለሁ ። አሁን ጉዳዩ የራስን ስራ ማስተዋወቅ ፣ ብዙ ቅጂ መሸጥና ከዚያ ገንዘብ ማግኘት አይደለም ዋናው ዓላማ ። እርግጥ ነው ብዙ ሲሸጥ በዚያው ልክ የገንዘብ ጥቅሙም አለ ። ይሁንና ግን ሰዎች መጽሐፉን ከገዛ ወዳጃቸው ተውሰው አንብበው ” በቀጣይም ቤቴ ሊኖር የሚገባ መጽሐፍ ነው ” ብለው ሲያምኑ ቢገዙ እሱም ይስማማናል ። ብቻ ” ምን ሆኛለሁ ? ” ከማንም ቤት ባይጠፋ ምኞታችን ነው ።ትዕግሥት ዋልተንጉሥ እና ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

በብር 1,000.0 ሦስት መጻሕፍት መግዛት የሚቻል ሲሆን ከዚያ በላይ የምትገዙ እያንዳንዱን ሺህ በሦስት በማባዛት የምታገኙትን መጻሕፍት ቁጥር ማግኘት ይቻላል ። ወዳጅ ዘመዶች በዚህ ዘመቻ በትጋት እንድትሳተፉ እንጠይቃለን ። የብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ፣ ፌስቡከሮችና ቲክቶከሮች መጽሐፉን በማስተዋወቅ አግዙን ። የምታግዙት መልካም ስራን እንደሆነ እኛን እመኑ ። ከታች ባለው የባንክ ሂሳብ ገንዘቡን ገቢ ካደረጋቾሁ በኋላ ያስገባችሁበትን ‘ ስክሪን ሾት ‘ አድርጋችሁ እንድትልኩልኝ እጠይቃለሁ ። መግዛት የቻላችሁም ያልቻላችሁ መልዕክቱን በማጋራት ቸባበሩን ።1000183007592
Tewodros Teklearegay
CBE

#SHARE በማድረግ ዘመቻውን ይደግፉ !!!
138340cookie-check” ምን ሆኛለሁ ? መጽሐፍ የትዕግስት ዋልተንጉስ አዲስ መፅሐፍhttps://telegra.ph/file/fa8bb…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE