የዛሬ ባለ ልደቷ ድምፃዊ ኤደን አይሸሹም ፈራ ተባን ሙዚቃን ቃኘን፡፡
ክብረአብ ጣሳው እና ኤደን አሸሹም ጥምረት
(በተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)
ይህ ሙዚቃ በብዙ የተፈተነ የፍቅር ውጣ ውረዶችን ይነግረናል ትረካ ወይም ታሪካዊ አዘል ያለው ድንቅ ሙዚቃ ከ ርዕሱ ስናነሳ ፈራ ተባ ሄድ መልስ ወይ ገባ ወጣ ያለ አካሄድ ነው፡፡
ድምፃዊት ኤደን አይሸሹም ይንን ሙዚቃ( በአኩስቲክ ፊል) ያለው ለስለስ ባለ መልኩ የተዘፈነ ግን በውስጡ አንድ ያልተፈታ ጥያቄ በልብዋ ሲብሰለሰል ያለ ግና መልሱ ለመስማት ያለ ማዘጋጀት ያስመልክታል ምክንያቱም ዓላማ ፣ ጊዜ ፣ እቅድ ሁሉ አከ አንተ መዝለቅ ነው እንዴት ችላለሁ እንደ ትናንቱ እንዳልሆን ምን ማስተማመኛ አለኝ?
“እያልኩ ፈራ ተባ ቃሌን እየያዝኩ
ደፍሬ ያንተ አርገኝ የኔ ሁን ያላልኩ
ልቤን አንድ ነገር እጅግ አሳስሮታል?
ከ አንተ እኩል አይደለም ልቤን ቀን ሰብሮታል “
መብሰልሰል በጥርጣሬ ውስጥ ያለ እርግጠኝነትን የሚፈታተን መጨነቅን በመላምት የተሞላ ይህ ሁሉ የመጣው በመፍራት ነው ከዚህ በፊት የደረሰውን ታሪክ ስሜቷን ሲፈታተነው እናያለን ፡፡
“ቢሆንልኝ እኔ ቢሳካ የምለው
ብዙ ነገር አለ ልኖር የምወደው
ትናንቴ ዛሬ ላይ አሸነፈኝ እና
እኔም መውደድ አልቻልኩም እምነት ጠፋኝ እና ?“
ጉዳቴን የሚጠግንልኝ ባገኝም ግን በጣም ብዙ ጊዜ ያስፈልገኛል እምነቴን ለመጣል እቸገራለሁ የቀደመው የፍቅር ሕይወቴ በልቤ ሰምሯል ብዬ ግን ሳይሰምር ስመለከት አዝኛለሁ እመሜን የሚሽረው ሰው ማን ይሁን ሳይሆን እንዴት ይሁንን መርጣለሁ ፡፡
“አንተህ እዚህ በመሀል ቤት
እኔም ሳላገኝ መድሐኒት
የኔም ሳትሆን ወይ የሌላ
ጊዜ እንዳሄድብህ ኃላ…“
መንገድህ አላስጠብቅህ ፣ ወደ ሌላ መሄድ ትችላለህ በመሀል ቤት እንዳትቀር ስትል ለሁለተኛው ጓደኛዋ ትነግረዋለች እኔ ቁስሌ እስዲርቅ ድረስ ሰፊ ጊዜ ጠብቃለሁ የጠፋው መድሀኒቴን እስኪገኝ ድረስ ፡፡
“ጊዜ ሁሉንም ይፈታል ሲሉኝ ሰምቻለሁ
እኔ የድኩኝ ይመስላል ግን ዝቻለሁ
ወግ ደርሶ ባየሁት የኔ እና የልቤን እቅድ
ያንተን ሕይወት ከኔ ጋር በጊዜ እንዳስታርቅ“
መለስ ትልና እራሧን ፣ ልቧን ፣ የፍቅር ጉዞዋን ትጠይቃለች በመቆዘም ውስጥ ምንም አመጣም እያሉ ሰዎች ይመክሯታል አዲስ ሕይወት ጀምሪ ነገ ሌላ ቀን ነው ሲሉ ከራስ ጋር ተማክራ እድል ለመስጠት ትሞክራለች ይህ ፈራ ተባ እስከ መጨረሻው ለመሻር እና በሙሉ ልብ ለማፍቀር ውስኔ ለመወሰን ትሻለች ፡፡ለ አልበም የሚናፈቅ ድምፅ ኤደን አይሸሹህም ፡፡
ክብአብ ጣሳው በቅንብሩ ግጥም እና ዜማ ኤደን አይሸሹም፡፡

- See also: ዜና ዕረፍት የድምፃዊ ሚካኤል በላይነህ…