ፋና ላምሮት በዕንባ የታጀበ ሽኝት ቤተሰባዊነት

Reading Time: 2 minutes
ፋና ላምሮት በዕንባ የታጀበ ሽኝት ቤተሰባዊነት



ከ አራት ሳምንት እረፍት በኃላ አስራ ሰባተኛ ምዕራፍ በአዲስ መልክ በአዲስ አቀራረብ ፋና ላምሮት ተጀምሯል፡፡

* ምን አዲስ ነገር ታየ

– ከሌሎች ምዕራፎች ለየት ያለ አቀራረብ በአስራ ሰባተኛ ምዕራፍ ተወዳዳሪዎች በዛ አድርገው ተሳትፎአቸው ወደ 16 ከፍ በማድረግ ዝግጅቱን መጀመራቸው ነው ፡፡



– የዳኝነት ለውጥ የታየበት ነበር የዜማ ግጥም ደራሲ የሙዚቃ ባለሞያ እና መምህርት ብሌን ዮሴፍ ከምዕራፍ ሁለት እስከ ምዕራፍ አስራ ስድስት በዳኝነት መርታለች ሌላኛው ድምፃዊ የግጥም ዜማ ደራሲ አቤል ሙሉጌታ ከምዕራፍ አምስት እስከ ምዕራፍ አስራ ስድስት በዳኝነት መርቷል የሁለቱ እንቁ ዳኞች ተሸኝቶ በሁለት እንቁ ዳኞች ተተክቷል ፡፡ የተተኩት የግጥም ዜማ ደራሲ እንዲሁም አቀናባሪ አማኑኤል ይልማ እና የፍሉት የሙዚቃ መሳርያ ተጫዋች በርካታ ስራዎች በጥበብ መንገድ የሰራች የፋና ላምሮት የጀርባ አጥንት የሹምነሽ ታዬ ተተክተዋል ፡፡

– እንደ ወትሮ ሁሉ ተመልካች በቦታው በመታደም የቀጥታ ስርጭት የሙዚቃ ስራዎች ተከታትለዋል ፡፡

* ዳኞች ከስልትም ከስሜትም አስተያየት ሰተዋል ፡፡

…ተዝናኖት ፣የሙዚቃ ምርጫ ፣ ሪትም አረዳድ ፣  ጉልበት ቁጥጥር ፣ ጉልበት አጠቃቀም ፣ ከቅኝት መፍረስ ፣ የድምፅ ውበት ፣ የማይክ አያያዝ ፣ የዜማ ፍሬዚን/የዜማ አረጋት / ፣ ትንፋሽ ቁጥጥር ፣ ኪ (key ) ፣ ቀለም ፣ የራስ አቅም ፍተሻ ፣ ሬንጅ ፣ ዲክሽን ፣ ስሜት ፣ ሀሳብ መሰብሰብ እና የመሳሰሉት ተነስተዋል… ፡፡

* ኮከብ ባንድ አስራ ስድስት መዚቃዎችን ተጫውተዋል ፡፡

– ሀና ሸንቁጤ(ዘው በል) ፣ ሙሉቀን መለሰ(ሄደች አሉ) ፣ ቴዎድሮስ ታደሰ( በመዋደዳችን) ፣ ማሪቱ ለገሰ( አንባሰል) ፣ ሚኒልክ ወስናቸው (እኔ ውሸቴ ነው) ፣ ፀሐዬ ዮሐንስ( የት ነበርሽ) ፣ ጋሽ ሙሃሙድ አህመድ ( ቆንጂት) ፣ ማዲንጎ አፈርቅ(አንቺን) ፣ጋሽ ጥላሁን ገሰሰ(ኢትዮጲያ /ለመድረክ ) ፣ ሐመልማል አባተ(መሄድህ ነው ወይ) ፣ ዳዊት መለሰ(ዘመዴ) ፣ አቤል ሙሉጌታ(ነፍሴ ተይ) ፣ መልካሙ ተበጀ( ደሀ በመሆኔ) ፣ ራሄል ጌቱ(ነበር) ፣ አለማየሁ እሸቴ(በጋዜጣ ይውጣ) ይህኝ በውድድሩ ቀርበዋል ፡፡



* ዳኞች ለሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት ሰተውናል

ብሩክ አሰፋ :- ውብ ዜማ ይዞ መምጣት ብቻ ሳይሆን ውብ አርጎ መጫወትም ያስፈልጋል ፡፡



የሹምነሽ ታዬ :- የድምፅ ጉልበት ሙሉ ለ ሙሉ መጠቀም ውበቱን ወይም ቀለሙን  ይጎዳዋል ፡፡



አማኑኤል ይልማ:- የማንችለውን ዘፈን ይዘን ከምንመጣ ይልቅ የምንችለውን ትንሿን ነገር ይዞ መምጣት ያስልጋል ፡፡



* ያለፉ ተወዳዳሪዎች እና በእለቱ የተሰናበተውን ውጤታቸውን ጭምር እንጠቁም…



-59,727- ጴጥሮስ ማስረሻ
-59,321- ናሆም ነጋሽ
-59,091-ኤርሚያስ ዳኛው
-57,567-ዘላለም ፀጋዬ
-57,561-ጌታነህ ስመኘው
-57,106-ዝንት ዓለም ባዬ
-57,057-ትዕግስት አንተነህ

የእለቱ ተሰናባች ፀጋሰጠኝ ሰይፊ በእለቱ 57,038 በማምጣት የመጀመርያ ሳምንት ተሰናባች ፋና ላምሮት ቤተሰባዊነቱን ገልፆ ከ5000 ብር ጋር አሰናትቶታል ፡፡



ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
የሳምንት ሰው ይበለን…
136400cookie-checkፋና ላምሮት በዕንባ የታጀበ ሽኝት ቤተሰባዊነት

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE