የዕብነ ሐኪም ” ብራና ” የተሰኘ ገሚስ አልበም ተለቀቀ

Reading Time: < 1 minute
የዕብነ ሐኪም ” ብራና ” የተሰኘ ገሚስ አልበም ተለቀቀ



ከአለም ዓቀፉ ሶኒ ኢንተርቴይመንት አፍሪካ (Sony Entertainment Africa) ጋር አብሮ በመስራት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የሆነው ወጣቱ ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም “ብራና ” የተሰኘ ገሚስ (ኢፒ) አልበሙ በይፋ ተመርቋል።

አልበሙ በባና ሪከርድስ የቀረበ ሲሆን፤ አቀናባሪ ኑሂ በአቀናባሪነት ፣ ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም በሙዚቃ ግጥም ጻሀፊነት እንዲሁም ሌሎች ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች ተሳትፈውበታል።



የኢትዮጵያ የሙዚቃ ስልትን ከዘመናዊ ስልቶች ጋር በማጣመር የተዘጋጀው ይህ አልበም፤ ሙዚቀኛው የሚያዘነብልበትን የኢትዮ- ፊዩዥን ስልት ያካተተ ሲሆን ፤ በውስጡ ስድስት የሀሳብ እና የታሪክ ተከታታይነት ያላቸው ሙዚቃዎችን መያዙ ተነግሯል።



ሙዚቃዊ ጭብጦቹን በቅኔያዊ ትረካዎች አማካኝነት የሚዳስሰው አልበሙ ፤ የዘፋኙ የሕይወት እና የሙዚቃ ጉዞ ጥልቅ ስሜቶች የተንፀባረቁበት መሆኑንም ተገልጿል።

ሙዚቀኛ ዕብነ ሐኪም ስለ አልበሙ ለጋዜጦኞች በሰጠው ማብራሪያ “ብራና ለልቤ በጣም የቀረብ ሥራ ነው። ሙዚቃውን የሚያደምጥ ሁሉ ተመሳሳይ ስሜት እንደሚሰማው ተስፋ አደርጋለሁ” ብሏል።

አልበሙ በቆሎ ተማሪነት በሚጀምረውና ” የኔታ” የሚል ስያሜ በተሰጠው ሙዚቃ ጀምሮ ” ብራና ” እስከተሰኘው ስድስተኛ ሙዚቃው ድረስ የሀሳብ እና የታሪክ ተከታታይነት ይዞ እንደሚቀጥልም አስረድቷል።



ለሁሉም ሙዚቃዎች ስድስት የሙዚቃ ቪዲዮዎች የተሰራላቸው ሲሆን፤ አልበሙን ሰርቶ ለማጠናቀቅ በአጠቃላይ አራት ዓመት ገደማ መፍጀቱንም ገልጿል።

ከተመሰረተ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው የባና ሪከርድስ መስራች እና ዋና ሥራ አስኪያጅ ብሌን መኮንን ‘’ባና ሪከርድስ የተመሰረተው የኢትዮጵያን ሙዚቃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ነው።” ያለች ሲሆን፤ ይህም “የብራና” አልበም የመጀመሪያ ፕሮጀክቱ መሆኑን ተናግራለች።

የሙዚቃ አቀናባሪው ኑሂ በበኩሉ፤ “ብራና” ሙሉ ዓለም ነው። ከልብ የተሰሩ ግጥሞችን፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ ትረካዎችን እና በስሜት ልዩ የሆኑ የሙዚቃ ቅንብሮችን አስተሳስሮ የሚሄድ የሕይወት መንገድ ነው።” ሲል ስለ አልበሙ ስሜቱን አጋርቷል።



ይህ “ብራና ” የተሰኘው ገሚስ አልበም ” EBNE HAKIM ” በተሰኘው የሙዚቀኛው የዩቲዩብ ቻናል እና በዓለምአቀፍ የሙዚቃ ማሰራጫ መተግበሪያዎች በኩል ትናንት በይፋ ተለቋል።

Musics, New Releases, Music Videos
136260cookie-checkየዕብነ ሐኪም ” ብራና ” የተሰኘ ገሚስ አልበም ተለቀቀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE